ክፍል 1 ክለሳ
ከአስተማሪህ ጋር በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ከሚሰጣቸው ተስፋዎች መካከል ትኩረትህን የሚስበው የትኛው ነው?
(ምዕራፍ 02ን ተመልከት።)
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ብለህ እንድታምን ያደረገህ ምንድን ነው?
ይሖዋ የሚለውን የአምላክ ስም መጠቀም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
(ምዕራፍ 04ን ተመልከት።)
መጽሐፍ ቅዱስ “የሕይወት ምንጭ” አምላክ እንደሆነ ይናገራል። (መዝሙር 36:9) በዚህ ታምናለህ?
(ምዕራፍ 06ን ተመልከት።)
ምሳሌ 3:32ን አንብቡ።
ይሖዋ ከማንም የተሻለ ወዳጅ ይሆነናል የምንለው ለምንድን ነው?
ይሖዋ ከወዳጆቹ ምን ይጠብቃል? እነዚህን ነገሮች የሚጠብቅ መሆኑ ምክንያታዊ ይመስልሃል?
መዝሙር 62:8ን አንብቡ።
ወደ ይሖዋ የጸለይክባቸው አንዳንድ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው? ሌላስ ስለ ምን ነገር ልትጸልይ ትችላለህ?
ይሖዋ ለጸሎታችን መልስ የሚሰጠው እንዴት ነው?
(ምዕራፍ 09ን ተመልከት።)
ዕብራውያን 10:24, 25ን አንብቡ።
በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘትህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?
በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት የምትከፍለው መሥዋዕትነት የሚያስቆጭ ይመስልሃል?
(ምዕራፍ 10ን ተመልከት።)
መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረህ ማንበብህ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን የምታነብበት ፕሮግራም አለህ? ካለህ ለዚህ የመደብከው የትኛውን ሰዓት ነው?
(ምዕራፍ 11ን ተመልከት።)
እስካሁን ካደረግነው የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት በጣም ያስደሰተህ የትኛው ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን መማር ከጀመርክ ወዲህ ምን ተፈታታኝ ሁኔታ አጋጥሞሃል? መማርህን እንድትቀጥል የሚረዳህ ምንድን ነው?
(ምዕራፍ 12ን ተመልከት።)