በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 2 ክለሳ

ክፍል 2 ክለሳ

ከአስተማሪህ ጋር በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  1. አምላክ በሐሰት ሃይማኖቶች ላይ ምን እርምጃ ይወስዳል?

    (ምዕራፍ 13ን ተመልከት።)

  2. ዘፀአት 20:4-6ን አንብቡ።

    •   ይሖዋ ሰዎች ምስሎችን ለአምልኮ ሲጠቀሙ ምን ይሰማዋል?

      (ምዕራፍ 14ን ተመልከት።)

  3. ኢየሱስ ማን ነው?

    (ምዕራፍ 15ን ተመልከት።)

  4. ከኢየሱስ ባሕርያት መካከል አንተን የሚማርኩህ የትኞቹ ናቸው?

    (ምዕራፍ 17ን ተመልከት።)

  5. ዮሐንስ 13:34, 35ን እንዲሁም የሐዋርያት ሥራ 5:42ን አንብቡ።

    •   በዛሬው ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖች እነማን ናቸው? እውነተኛ ክርስቲያኖች ናቸው ብለህ እንድትደመድም ያደረገህ ምንድን ነው?

      (ምዕራፍ 18ን እና 19ን ተመልከት።)

  6. የጉባኤው ራስ ማን ነው? ጉባኤውን የሚመራውስ እንዴት ነው?

    (ምዕራፍ 20ን ተመልከት።)

  7. ማቴዎስ 24:14ን አንብቡ።

    •   ይህ ትንቢት በዛሬው ጊዜ እየተፈጸመ ያለው እንዴት ነው?

    •   እስካሁን ምሥራቹን የነገርካቸው ሰዎች አሉ?

      (ምዕራፍ 21ን እና 22ን ተመልከት።)

  8. ጥምቀት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ እንደሆነ ይሰማሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

    (ምዕራፍ 23ን ተመልከት።)

  9. ሰይጣንና አጋንንቱ ከሚያሳድሩት ተጽዕኖ ራስህን መጠበቅ የምትችለው እንዴት ነው?

    (ምዕራፍ 24ን ተመልከት።)

  10. አምላክ ለእኛ ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

    (ምዕራፍ 25ን ተመልከት።)

  11. ሰዎች ችግርና መከራ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው?

    (ምዕራፍ 26ን ተመልከት።)

  12. ዮሐንስ 3:16ን አንብቡ።

    •   ይሖዋ እኛን ከኃጢአትና ከሞት ለማዳን ምን አድርጓል?

      (ምዕራፍ 27ን ተመልከት።)

  13. መክብብ 9:5ን አንብቡ።

    •   የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?

    •   ኢየሱስ በሞት ላንቀላፉ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ምን ያደርግላቸዋል?

      (ምዕራፍ 29ን እና 30ን ተመልከት።)

  14. የአምላክ መንግሥት ከሌላ ከየትኛውም መንግሥት የተሻለ የሆነው በየትኞቹ መንገዶች ነው?

    (ምዕራፍ 31ን እና 33ን ተመልከት።)

  15. የአምላክ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ እየገዛ እንደሆነ ታምናለህ? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው? መግዛት የጀመረውስ መቼ ነው?

    (ምዕራፍ 32ን ተመልከት።)