በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ብቃቱን አሟላለሁ?

ብቃቱን አሟላለሁ?

ከጉባኤው ጋር ለመስበክ ብቃቱን አሟላለሁ?

የሚከተሉትን ነገሮች ካሟላህ ያልተጠመቀ አስፋፊ ለመሆን ብቁ ልትሆን ትችላለህ፦

  • አዘውትረህ መጽሐፍ ቅዱስን የምታጠና፣ የምትጸልይና በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ የምትገኝ ከሆነ

  • የምትማረውን ነገር የምትወደውና የምታምንበት እንዲሁም ለሌሎች መናገር የምትፈልግ ከሆነ

  • ይሖዋን የምትወድ እንዲሁም እሱን የሚወዱ ሰዎችን ጓደኛ አድርገህ የምትመርጥ ከሆነ

  • የየትኛውም የፖለቲካ ወይም የሐሰት ሃይማኖት ድርጅት አባል ካልሆንክ

  • ከይሖዋ መሥፈርቶች ጋር ተስማምተህ የምትኖርና የይሖዋ ምሥክር መሆን የምትፈልግ ከሆነ

ከጉባኤው ጋር ለመስበክ ዝግጁ እንደሆንክ ከተሰማህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስተምርህ ሰው ከጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር ተገናኝተህ ስለ ጉዳዩ እንድትነጋገር ዝግጅት ሊያደርግልህ ይችላል።

ለመጠመቅ ብቃቱን አሟላለሁ?

የሚከተሉትን ነገሮች ካሟላህ ለመጠመቅ ብቁ ልትሆን ትችላለህ፦

  • ያልተጠመቅክ አስፋፊ ከሆንክ

  • አቅምህ በፈቀደው መጠን በስብከቱ ሥራ አዘውትረህ የምትካፈል ከሆነ

  • “ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚሰጠውን አመራር የምትደግፍና የምትከተል ከሆነ—ማቴዎስ 24:45-47

  • በጸሎት አማካኝነት ራስህን ለይሖዋ ከወሰንክና እሱን ለዘላለም ማገልገል የምትፈልግ ከሆነ

ለመጠመቅ ዝግጁ እንደሆንክ ከተሰማህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስተምርህ ሰው ከጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር ተገናኝተህ ስለ ጉዳዩ እንድትነጋገር ዝግጅት ሊያደርግልህ ይችላል።