መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጀምር
መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ አስደሳች ሊሆንልህ ይችላል! ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ለመጀመር የሚረዱህን አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦች ይዟል። ትኩረትህን የሚስበውን አንድ ርዕሰ ጉዳይ ምረጥ፤ ከዚያም የተጠቀሱትን ጥቅሶች አንብብ።
ታዋቂ ሰዎችና ታሪኮች
-
ኖኅ እና የጥፋት ውኃው፦ ዘፍጥረት 6:9–9:19
-
ሙሴ በቀይ ባሕር፦ ዘፀአት 13:17–14:31
-
ሩት እና ናኦሚ፦ ሩት ምዕራፍ 1-4
-
ዳዊት እና ጎልያድ፦ 1 ሳሙኤል ምዕራፍ 17
-
አቢጋኤል፦ 1 ሳሙኤል 25:2-35
-
ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ፦ ዳንኤል ምዕራፍ 6
-
ኤልሳቤጥ እና ማርያም፦ ሉቃስ ምዕራፍ 1-2
ለዕለት ተዕለት ሕይወት የሚጠቅሙ ምክሮች
-
የቤተሰብ ሕይወት፦ ኤፌሶን 5:28, 29, 33፤ 6:1-4
-
ወዳጅነት፦ ምሳሌ 13:20፤ 17:17፤ 27:17
-
ጸሎት፦ መዝሙር 55:22፤ 62:8፤ 1 ዮሐንስ 5:14
-
የተራራው ስብከት፦ ማቴዎስ ምዕራፍ 5-7
የሚከተሉትን ሁኔታዎች ለመቋቋም እርዳታ ሲያስፈልግህ፦
-
ተስፋ መቁረጥ፦ መዝሙር 23፤ ኢሳይያስ 41:10
-
የጥፋተኝነት ስሜት፦ መዝሙር 86:5፤ ሕዝቅኤል 18:21, 22
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
-
ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት፦ ማቴዎስ 24:3-14፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:1-5
-
ስለ ወደፊቱ ጊዜ፦ መዝሙር 37:10, 11, 29፤ ራእይ 21:3, 4
ጠቃሚ ምክር፦ ከላይ የተዘረዘሩትን ጥቅሶች አውድ ለመረዳት ጥቅሶቹ የተወሰዱበትን ምዕራፍ በሙሉ አንብብ። እያንዳንዱን ምዕራፍ አንብበህ ስትጨርስ በዚህ ጽሑፍ መጨረሻ ላይ ባለው “የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን መዝግብ” በሚለው ሰንጠረዥ ላይ ምልክት አድርግ። በየዕለቱ የተወሰነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለማንበብ ግብ አውጣ።