በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እዚህ ጽሑፍ ላይ ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

እዚህ ጽሑፍ ላይ ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

በመጀመሪያ የመጽሐፉን ይዘት የሚያሳየውን ይህን ክፍል አንብብ፤ ከዚያም ቪዲዮውን ተመልከት

የመጀመሪያው ክፍል

እያንዳንዱን ምዕራፍ ለመዘጋጀት የመጀመሪያውን ክፍል አንብብ። በደማቅ የተጻፉት ጥያቄዎችና (ሀ) ጥቅሶቹ (ለ) ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ያጎላሉ። ከአንዳንዶቹ ጥቅሶች አጠገብ “አንብብ” የሚል መመሪያ እንደሚገኝ ልብ በል።

ሁለተኛው ክፍል

ጠለቅ ያለ ጥናት በሚለው ሥር ያለው አጠር ያለ መግለጫ (ሐ) ቀጥሎ የሚብራራውን ሐሳብ ይገልጻል። ንዑስ ርዕሶቹ (መ) ዋና ዋና ነጥቦቹን ይዘዋል። ከአስተማሪህ ጋር ጥቅሶቹን አንብብ፣ በጥያቄዎቹ ላይ ተወያይ እንዲሁም ቪዲዮዎቹን ተመልከት።

ቪዲዮ የሚሉት ሣጥኖች የጽሑፉን ሐሳብ የሚያጠናክሩ ቪዲዮዎችን ማግኘት ወደምትችልበት ቦታ ይመሩሃል። አንዳንዶቹ ቪዲዮዎች እውነተኛ ታሪኮች ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ እውነተኛ ታሪክ ባይሆኑም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሁኔታዎችን በድራማ መልክ ያሳያሉ።

ሥዕሎቹንና የሥዕሎቹን መግለጫዎች (ሠ) ትኩረት ሰጥተህ ተመልከት፤ በተጨማሪም አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ (ረ) በሚለው ሥር የቀረቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር።

የመጨረሻው ክፍል

ማጠቃለያ እና ክለሳ (ሰ) የሚሉት ክፍሎች የምዕራፉን ሐሳብ ጠቅለል አድርገው ይገልጻሉ። ምዕራፉን አጥንተህ የጨረስክበትን ቀን ጻፍ። ግብ (ሸ) የሚለው ክፍል በሥራ ላይ ልታውል የምትችላቸውን አንዳንድ ነጥቦች ይጠቁምሃል። ምርምር አድርግ (ቀ) የሚለው ክፍል ደግሞ ልታነብ ወይም ልትመለከት የምትችላቸውን ተጨማሪ ርዕሶች ወይም ቪዲዮዎች ይዟል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማውጣት የምትችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ 66 ትናንሽ መጻሕፍትን ይዟል። በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም የዕብራይስጥና የአረማይክ ቅዱሳን መጻሕፍት (“ብሉይ ኪዳን”) እንዲሁም የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት (“አዲስ ኪዳን”) ናቸው።

ጥቅሶች በሚጠቀሱበት ጊዜ መጀመሪያ የመጽሐፉ ስም (ሀ)፣ ቀጥሎ ምዕራፉ (ለ) ከዚያ በኋላ ደግሞ ቁጥሩ ወይም ቁጥሮቹ (ሐ) ይጻፋሉ።

ለምሳሌ ያህል፣ ዮሐንስ 17:3 ሲባል ዮሐንስ ምዕራፍ 17 ቁጥር 3 ማለት ነው።