በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መግቢያ

መግቢያ

ያጋጠመህ ተፈታታኝ ሁኔታ አለ? ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት፣ አሁን ላለህበት ሁኔታ የሚሠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንና ታሪኮችን በቀላሉ ፈልገህ ለማግኘት ይረዳሃል። እንዲሁም ሌሎችን ማበረታታትና ይሖዋን የሚያስከብር ውሳኔ እንዲያደርጉ መርዳት ስትፈልግ ለሁኔታው ተስማሚ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች ለማግኘት ያስችልሃል። ከአንተ የሚጠበቀው የምትፈልገውን ርዕሰ ጉዳይ መምረጥ ነው፤ እያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ ጥያቄዎችና በአጭሩ የተቀመጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ይዟል። (“ በዚህ ጽሑፍ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) በዚህ መንገድ ከአምላክ ቃል ላይ የሚያስፈልግህን ጠቃሚ ምክር፣ መመሪያና ማጽናኛ ታገኛለህ። ለሌሎች የምታካፍላቸው መንፈሳዊ ዕንቁዎችም ታገኛለህ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ተጠቅመህ መንፈሳቸውን ማደስ፣ ችግራቸውን እንዲወጡ መርዳት እንዲሁም ምክርና ማበረታቻ መስጠት ትችላለህ።

ይህ ጽሑፍ ለአንድ ርዕሰ ጉዳይ የሚሠሩ ጥቅሶችን ሁሉ ይዟል ማለት አይደለም። ሆኖም ለምታደርገው ምርምር ጥሩ መነሻ ይሆንልሃል። (ምሳሌ 2:1-6) ጠለቅ ብለህ ማጥናት ከፈለግህ አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙትን የኅዳግ ማጣቀሻዎች እና ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች ተመልከት። ስለ አንድ ጥቅስ ትርጉም ወይም ተግባራዊ ስለሚሆንባቸው አቅጣጫዎች ይበልጥ የተሟላ ግንዛቤ ለማግኘት፣ የምርምር መርጃ መሣሪያ ለይሖዋ ምሥክሮች እና የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ (እንግሊዝኛ) ተጠቀም። የምታገኘው መረጃ ወቅታዊ እንዲሆን ቅርብ ጊዜ የወጣውን ማመሣከሪያ ጽሑፍ ተመልከት።

ጥቅሶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የሚገኘውን የጥበብ፣ የእውቀትና የማስተዋል በር እንዲከፍትልህ ምኞታችን ነው። ይህን ጽሑፍ በተጠቀምክበት ቁጥር “የአምላክ ቃል ሕያውና ኃይለኛ” እንደሆነ ያለህ እምነት እየጨመረ እንደሚሄድ እንተማመናለን። —ዕብ 4:12