በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ማጽናኛ

ማጽናኛ

ተስፋ ለሚያስቆርጡ አንዳንድ ችግሮች ቅዱስ ጽሑፋዊ ማጽናኛ

ሌሎች እንደጠበቅናቸው ሳይሆኑ ሲቀሩ፣ ሲጎዱን ይባስ ብሎም ሲከዱን

የጠበቅነው ሳይሆን ሲቀር” የሚለውን ተመልከት

ሌሎች ያደረሱብን በደል የፈጠረብንን ቅሬታ መርሳት ሲያቅተን

በደል” የሚለውን ተመልከት

ምሬት፤ ቁጣ

አንዳንዶች የኑሮ ፈተና ሲገጥማቸው ወይም ችግሮች ሲደራረቡባቸው ምሬት ያድርባቸዋል

መክ 9:11, 12

በተጨማሪም መዝ 142:4፤ መክ 4:1፤ 7:7⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሩት 1:11-13, 20—ናኦሚ ባሏንና ሁለት ልጆቿን በሞት ባጣችበት ወቅት ይሖዋ እንደተዋት ተሰምቷታል

    • ኢዮብ 3:1, 11, 25, 26፤ 10:1—ኢዮብ ሀብቱን፣ አሥር ልጆቹንና ጤናውን ሲያጣ ተመርሯል

  • የሚያጽናኑ ጥቅሶች፦

  • የሚያጽናኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሩት 1:6, 7, 16-18፤ 2:2, 19, 20፤ 3:1፤ 4:14-16—ናኦሚ ወደ አምላክ ሕዝብ ለመቅረብ እርምጃ ወስዳለች፣ የተሰጣትን እርዳታ ተቀብላለች፣ እሷም በፍቅር ተነሳስታ ሌሎችን ረድታለች፤ ይህም ምሬቷ በደስታ እንዲተካ አድርጓል

    • ኢዮብ 42:7-16፤ ያዕ 5:11—ኢዮብ በእምነት ጸንቷል፤ ይሖዋም አትረፍርፎ ባርኮታል

አንዳንዶች በደል ሲደርስባቸው ይመረራሉ

መክ 4:1, 2

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 1:6, 7, 10, 13-16—ሐና፣ ፍናና በምታደርስባት በደል በጣም ተጎድታለች፤ ሊቀ ካህናቱ ኤሊም በተሳሳተ መንገድ ተረድቷታል

    • ኢዮብ 8:3-6፤ 16:1-5፤ 19:2, 3—የኢዮብ አጽናኝ ተብዬዎች ራሳቸውን የሚያመጻድቁና ነቃፊዎች ነበሩ፤ ኢዮብ ስሜቱ የባሰ እንዲደቆስ አድርገዋል

  • የሚያጽናኑ ጥቅሶች፦

  • የሚያጽናኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 1:9-11, 18—ሐና ለይሖዋ የልቧን አውጥታ ከነገረችው በኋላ ሥቃይዋ ቀለል አለላት

    • ኢዮብ 42:7, 8, 10, 17—ኢዮብ ወዳጆቹን ይቅር ካለ በኋላ ይሖዋ ጤንነቱንና ደስታውን መልሶለታል

ስደት

ስደት” የሚለውን ተመልከት

ቅናት፤ ምቀኝነት

ቅናት” የሚለውን ተመልከት

በሕመም ወይም በእርጅና ምክንያት አቅማችን ሲገደብ

መዝ 71:9, 18፤ መክ 12:1-7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ነገ 20:1-3—ንጉሥ ሕዝቅያስ የማይድን በሽታ እንደያዘው ሲያውቅ ስቅስቅ ብሎ አልቅሷል

    • ፊልጵ 2:25-30—አፍሮዲጡ፣ መታመሙን ጉባኤው ስላወቀ በጭንቀት ተውጧል፤ ‘ኃላፊነቱን መወጣት አልቻለም’ ብለው እንዳያስቡም ሰግቷል

  • የሚያጽናኑ ጥቅሶች፦

  • የሚያጽናኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ሳሙ 17:27-29፤ 19:31-38—ታማኙ ቤርዜሊ በንጉሡ ዘንድ ትልቅ ቦታ የተሰጠው ሰው ነው፤ ሆኖም ልኩን የሚያውቅ ሰው ስለሆነ በዕድሜው ምክንያት ከአቅሙ በላይ እንደሆነ የተሰማውን ኃላፊነት አልተቀበለም

    • መዝ 41:1-3, 12—ንጉሥ ዳዊት በጠና ቢታመምም ይሖዋ እንደሚደግፈው እርግጠኛ ነው

    • ማር 12:41-44—አንዲት ድሃ መበለት ያላትን ሁሉ መዋጮ አድርጋ በመስጠቷ ኢየሱስ አድንቋታል

በራሳችን ድክመት ወይም ኃጢአት የተነሳ የጠበቅነው ሳይሆን ሲቀር

የጠበቅነው ሳይሆን ሲቀር” የሚለውን ተመልከት

በፍርሃት መራድ፤ መሸበር

ፍርሃት” የሚለውን ተመልከት

አዳጋች የሆነን ችግር ወይም የአገልግሎት ምድብ ለመወጣት ብቁ አይደለሁም የሚል ስሜት ሲሰማን

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፀ 3:11፤ 4:10—ነቢዩ ሙሴ፣ ፈርዖንን ፊት ለፊት እንዲያነጋግረውና የአምላክን ሕዝብ እየመራ ከግብፅ እንዲያወጣ ሲነገረው ብቁ እንዳልሆነ ተሰምቶታል

    • ኤር 1:4-6—ኤርምያስ ግትር በሆኑ ሰዎች መካከል የይሖዋ ነቢይ ሆኖ እንዲያገለግል ሲሾም ገና ልጅ እንደሆነና ተሞክሮ እንደሌለው ተናግሯል

  • የሚያጽናኑ ጥቅሶች፦

  • የሚያጽናኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፀ 3:12፤ 4:11, 12—ይሖዋ፣ ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንደሚረዳው ለነቢዩ ሙሴ ደጋግሞ አረጋግጦለታል

    • ኤር 1:7-10—ይሖዋ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ከፊቱ የሚጠብቁትን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዲወጣ እንደሚያግዘው ነግሮታል

ከባድ የጥፋተኝነት ስሜት

ዕዝራ 9:6፤ መዝ 38:3, 4, 8፤ 40:12

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ነገ 22:8-13፤ 23:1-3—ንጉሥ ኢዮስያስና ሕዝቡ የሙሴ ሕግ ከተነበበላቸው በኋላ የበደላቸው ክብደት ስለገባቸው የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቷቸዋል

    • ዕዝራ 9:10-15፤ 10:1-4—በካህኑ ዕዝራ ዘመን አንዳንዶች የይሖዋን ሕግ በመጣስ የባዕድ አገር ሴቶች በማግባታቸው ዕዝራና ሕዝቡ በጥፋተኝነት ስሜት ተደቁሰዋል

    • ሉቃስ 22:54-62—ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ ኢየሱስን አላውቀውም ብሎ ሦስት ጊዜ ከካደው በኋላ ጥልቅ የጸጸት ስሜት ተሰምቶታል

  • የሚያጽናኑ ጥቅሶች፦

  • የሚያጽናኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 33:9-13, 15, 16—ምናሴ በይሁዳ ከተነሱት እጅግ ክፉ ነገሥታት አንዱ ነው፤ ሆኖም ንስሐ በመግባቱ ምሕረት አግኝቷል

    • ሉቃስ 15:11-32—ኢየሱስ የጠፋውን ልጅ ምሳሌ በመናገር ይሖዋ በደግነትና ሙሉ በሙሉ ይቅር እንደሚል አሳይቷል

ዋጋማነታችንን ስንጠራጠር

ጥርጣሬ፤ በራስ አለመተማመን” የሚለውን ተመልከት

ጭንቀት

ጭንቀት” የሚለውን ተመልከት