በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምክር

ምክር

ምክር መቀበል

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ምክር መፈለግ ያለብን ለምንድን ነው?

ምክር ሲሰጠን ለድርጊታችን ሰበብ ከመደርደር ይልቅ ምክሩን መስማታችን የተሻለ የሆነው ለምንድን ነው?

ምሳሌ 12:15፤ 29:1

በተጨማሪም ምሳሌ 1:23-31፤ 15:31⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 15:3, 9-23—ነቢዩ ሳሙኤል ለሳኦል እርማት ሲሰጠው፣ ንጉሡ ድርጊቱን ትክክል ለማስመሰል ሰበብ አስባብ ደረደረ፤ ምክሩንም ሳይቀበል ቀረ፤ በዚህም የተነሳ ይሖዋ ትቶታል

    • 2ዜና 25:14-16, 27—ንጉሥ አሜስያስ ኃጢአት በሠራበት ወቅት አንድ የይሖዋ ነቢይ የሰጠውን ምክርና እርማት አልተቀበለም፤ ይህም የይሖዋን ሞገስና ጥበቃ አሳጥቶታል

ምክር ለሚሰጡ የበላይ ተመልካቾች አክብሮት ማሳየት ያለብን ለምንድን ነው?

1ተሰ 5:12፤ 1ጢሞ 5:17፤ ዕብ 13:7, 17

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 3ዮሐ 9, 10—ዲዮጥራጢስ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ አመራር የሚሰጡ ወንድሞችን አክብሮት በጎደለው መንገድ በመያዙ አረጋዊው ሐዋርያ ዮሐንስ አውግዞታል

በዕድሜ የገፉትን መስማት ያለብን ለምንድን ነው?

ዘሌ 19:32፤ ምሳሌ 16:31

በተጨማሪም ኢዮብ 12:12፤ 32:7፤ ቲቶ 2:3-5⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 23:16-18—ንጉሥ ዳዊት በ30 ዓመት ገደማ የሚበልጠው ዮናታን ሲመክረው ሰምቷል፤ ምክሩም አበረታቶታል

    • 1ነገ 12:1-17—ንጉሥ ሮብዓም፣ ሽማግሌዎች የሰጡትን ምክንያታዊ ምክር ትቶ ወጣቶቹ የሰጡትን መጥፎ ምክር ሰማ፤ ይህም መዘዝ አስከትሏል

ታማኝ ሴቶችና በዕድሜ አነስ ያሉ የይሖዋ አገልጋዮች ጠቃሚ ምክር መስጠት እንደሚችሉ የሚያሳየው ምንድን ነው?

ኢዮብ 32:6, 9, 10፤ ምሳሌ 31:1, 10, 26፤ መክ 4:13

በተጨማሪም መዝ 119:100⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 25:14-35—አቢጋኤል ለንጉሥ ዳዊት የሰጠችው ምክር የብዙዎችን ሕይወት አትርፏል፤ እሱንም ከደም ዕዳ ጠብቆታል

    • 2ሳሙ 20:15-22—በአቤል ከተማ የምትኖር ብልህ ሴት በምክሯ መላውን ከተማ አትርፋለች

    • 2ነገ 5:1-14—አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጅ የሰጠችው ጥቆማ አንድ ኃያል ተዋጊ ከሥጋ ደዌ በሽታው እንዲፈወስ ምክንያት ሆኗል

ይሖዋን የማያከብሩና ቃሉን የማይሰሙ ሰዎች የሚሰጡትን ምክር መቀበል የሌለብን ለምንድን ነው?

መዝ 1:1፤ ምሳሌ 4:14

በተጨማሪም ሉቃስ 6:39⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ዜና 10:13, 14—ንጉሥ ሳኦል ይሖዋን ከመጠየቅ ይልቅ መናፍስት ጠሪ አማክሯል፤ በዚህ መንገድ ታማኝነቱን በማጉደሉ ሕይወቱን አጥቷል

    • 2ዜና 22:2-5, 9—ንጉሥ አካዝያስ መጥፎ አማካሪዎች መምረጡ ሕይወቱን አሳጥቶታል

    • ኢዮብ 21:7, 14-16—ኢዮብ ይሖዋን የማያከብሩ ሰዎችን ሐሳብ አልተቀበለም

ምክር መስጠት

ምክር ከመስጠታችን በፊት ማዳመጣችን፣ ስለ ጉዳዩ የተሟላ መረጃ ማግኘታችንና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ወገኖች የሚሉትን መስማታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ምሳሌ 18:13, 17

በተጨማሪም ምሳሌ 25:8⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 1:9-16—ሊቀ ካህናቱ ኤሊ፣ ታማኟ ሐና እንደሰከረች ስለተሰማው ሁኔታውን ሳያጣራ ሻካራ የሆነ ምክር ሰጣት

    • ማቴ 16:21-23—ሐዋርያው ጴጥሮስ ምንም ሳያመዛዝን ኢየሱስን ወቀሰው፤ የሰጠው ምክር የይሖዋን ሳይሆን የሰይጣንን ዓላማ የሚያሳካ ነበር

ምክር ከመስጠታችን በፊት ይሖዋ እንዲመራን መጸለይ ያለብን ለምንድን ነው?

መዝ 32:8፤ 73:23, 24፤ ምሳሌ 3:5, 6

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፀ 3:13-18—ነቢዩ ሙሴ፣ ከእስራኤላውያን ወገኖቹ ለሚነሱለት ጥያቄዎች ምን መልስ መስጠት እንደሚችል ይሖዋን ጠይቋል

    • 1ነገ 3:5-12—ወጣቱ ንጉሥ ሰለሞን በራሱ ከመመካት ይልቅ ጥበብ እንዲሰጠው ይሖዋን ጠይቋል፤ ይህም የይሖዋን በረከት አስገኝቶለታል

ምክራችንም ሆነ የምንሰጠው መልስ ምንጊዜም በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ መሆን ያለበት ለምንድን ነው?

መዝ 119:24, 105፤ ምሳሌ 19:21 2ጢሞ 3:16, 17

በተጨማሪም ዘዳ 17:18-20⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 4:1-11—ኢየሱስ፣ ሰይጣን ላቀረበለት ፈተና መልስ የሰጠው በራሱ ጥበብ በመመካት ሳይሆን በአምላክ ቃል ላይ በመመሥረት ነው

    • ዮሐ 12:49, 50—ኢየሱስ፣ ትምህርቱ ሁሉ የተመሠረተው አምላክ ባስተማረው ነገር ላይ እንደሆነ ተናግሯል፤ ይህም ለእኛ ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል

ምክር ስንሰጥ የገርነት መንፈስ ማሳየት እንዲሁም ከልባችን ለማመስገን መጣር ያለብን ለምንድን ነው?

ገላ 6:1፤ ቆላ 3:12

በተጨማሪም ኢሳ 9:6፤ 42:1-3ማቴ 11:28, 29⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 19:2, 3—ይሖዋ፣ ነቢዩን በመላክ ለንጉሥ ኢዮሳፍጥ እርማት የሰጠው ቢሆንም ላደረጋቸው መልካም ነገሮችም አመስግኖታል

    • ራእይ 2:1-4, 8, 9, 12-14, 18-20—ኢየሱስ ለተለያዩ ጉባኤዎች ምክር ከመስጠቱ በፊት፣ ላደረጉት መልካም ነገር አመስግኗቸዋል

አንድ ክርስቲያን ሌላ ወንድም እንዳጭበረበረው ወይም ስሙን እንዳጠፋ ቢነግረን፣ እንደበደለው ከተሰማው ወንድም ጋር ጉዳዩን በግል እንዲነጋገርበት ማበረታታት ያለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 18:15-17፤ ሉቃስ 17:3

በተጨማሪም ዘሌ 19:17⁠ን ተመልከት

እንደተበደለ የሚሰማውን አንድ ክርስቲያን መሐሪ፣ ታጋሽና ይቅር ባይ እንዲሆን ማበረታታት የምንችለው እንዴት ነው?

ማቴ 18:21, 22፤ ማር 11:25፤ ሉቃስ 6:36፤ ኤፌ 4:32፤ ቆላ 3:13

በተጨማሪም ማቴ 6:14፤ 1ቆሮ 6:1-81ጴጥ 3:8, 9⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 18:23-35—ኢየሱስ፣ ይቅር ባይ መሆናችን በጣም አስፈላጊ መሆኑን የሚያስረዳ ግሩም ምሳሌ ተናግሯል

ምክር ስንሰጥ ትክክል ለሆነው ነገር ጥብቅ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

መዝ 141:5፤ ምሳሌ 17:10፤ 2ቆሮ 7:8-11

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 15:23-29—ነቢዩ ሳሙኤል ንጉሥ ሳኦልን ፈርቶ ምክር ከመስጠት ወደኋላ አላለም

    • 1ነገ 22:19-28—ነቢዩ ሚካያህ፣ ማስፈራሪያም ሆነ ጥፊ ለንጉሥ አክዓብ የሚናገረውን የማስጠንቀቂያ መልእክት እንዲያለዝብ አላደረገውም

አንድን ሰው በመንፈሳዊ ሳናሰናክለው ምክር ልንሰጠው የምንችለው እንዴት ነው?

ዕብ 12:11-13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 22:31-34—ኢየሱስ፣ ሐዋርያው ጴጥሮስ ከባድ ስህተት ቢሠራም በኋላ ላይ ከስህተቱ ታርሞ ሌሎችን ለማበረታታት እንደሚበቃ እንደሚተማመንበት ነግሮታል

    • ፊልሞና 21—ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ፊልሞና የተሰጠውን አምላካዊ ምክር ይከተላል ብሎ እንደሚተማመንበት ገልጿል

ለተጨነቁ ወይም ስሜታቸው ለተደቆሰ ሰዎች በደግነት ምክር መስጠት የምንችለው እንዴት ነው?

ምክር ስንሰጥ ዓላማችን ስህተት የሠራውን ሰው ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲመለስ መርዳት መሆኑን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ወንድም ሆነ ሴት፣ ወጣትም ሆነ አረጋዊ የምንመክረውን ሰው እንደምናከብረው ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ሽማግሌዎች በተደጋጋሚ የተሰጠውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክር ችላ ለሚል ሰው ጠንከር ያለ እርማት የሚሰጡት ለምንድን ነው?

1ቆሮ 5:9, 11, 13፤ 1ጢሞ 5:20፤ ቲቶ 3:10

በተጨማሪም “ውገዳ” የሚለውን ተመልከት