በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ማበረታቻ

ማበረታቻ

የአምላክ አገልጋዮች እርስ በርስ መበረታታታቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ኢሳ 35:3, 4፤ ቆላ 3:16፤ 1ተሰ 5:11 ዕብ 3:13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 32:2-8—ንጉሥ ሕዝቅያስ ኃይለኛ ጠላት ሲመጣባቸው ሕዝቡን አበረታቷል

    • ዳን 10:2, 8-11, 18, 19—አረጋዊው ነቢይ ዳንኤል ኃይሉ በተሟጠጠበት ወቅት አንድ መልአክ አበረታቶታል እንዲሁም አጠናክሮታል

ኃላፊነት ያላቸው ወንድሞች ማበረታቻ ከመስጠት ጋር በተያያዘ ምን ግዴታ አለባቸው?

ኢሳ 32:1, 2፤ 1ጴጥ 5:1-3

በተጨማሪም ማቴ 11:28-30⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘዳ 3:28፤ 31:7, 8—ነቢዩ ሙሴ፣ ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ተተኪውን ኢያሱን አበረታቶታል እንዲሁም አደፋፍሮታል

    • ሥራ 11:22-26፤ 14:22—ሐዋርያቱ ጳውሎስና በርናባስ በስደት ወቅት የአንጾኪያ ክርስቲያኖችን አበረታተዋል

ማበረታቻ ለመስጠት ከልብ ማመስገን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ምሳሌ 31:28, 29፤ 1ቆሮ 11:2

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መሳ 11:37-40—የእስራኤል ሴቶች የመስፍኑን ዮፍታሔ ልጅ በየዓመቱ እየሄዱ ይጠይቋታል፤ ሕይወቷን ለይሖዋ አገልግሎት በመስጠቷ ያመሰግኗታል

    • ራእይ 2:1-4—ኢየሱስ የኤፌሶን ክርስቲያኖችን ማረም ቢያስፈልገውም መልካም ጎናቸውን ጠቅሶላቸዋል

ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች እርስ በርስ መበረታታት የሚችሉት እንዴት ነው?

ምሳሌ 15:23፤ ኤፌ 4:29፤ ፊልጵ 1:13, 14፤ ቆላ 4:6፤ 1ተሰ 5:14

በተጨማሪም 2ቆሮ 7:13, 15, 16⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 23:16-18—ዮናታን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለውን ዳዊትን ፈልጎ አገኘው፤ እንዲሁም በዕድሜ የሚያንሰውን ወዳጁን አበረታታው

    • ዮሐ 16:33—ኢየሱስ ምሳሌ በመሆን ተከታዮቹን አበረታቷቸዋል፤ የእሱን ምሳሌ ከተከተሉ አሸናፊዎች እንደሚሆኑ አረጋግጦላቸዋል

    • ሥራ 28:14-16—ሐዋርያው ጳውሎስ ይግባኙ እንዲታይለት ወደ ሮም በተጓዘበት ወቅት እሱን ለማግኘትና ለማበረታታት ሩቅ መንገድ ተጉዘው የመጡ ታማኝ ወንድሞቹን ሲያይ ተበረታታ

አክብሮት የማጣት ወይም የማጉረምረም መንፈስ እንዳያድርብን መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ፊልጵ 2:14-16፤ ይሁዳ 16-19

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘኁ 11:10-15—ነቢዩ ሙሴ፣ አሉታዊና ዓመፀኛ በሆነው ሕዝብ የተነሳ ተስፋ ቆርጧል

    • ዘኁ 13:31, 32፤ 14:2-6—አሥሩ ሰላዮች የነዙት መጥፎ ወሬ ሕዝቡን ተስፋ አስቆረጠ፤ ወደ ዓመፅም መራቸው

ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ጊዜ ማሳለፍ የሚያበረታታን ለምንድን ነው?

ምሳሌ 27:17፤ ሮም 1:11, 12 ዕብ 10:24, 25፤ 12:12

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 20:1-19—ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ታላቅ ሠራዊት ሲመጣበት አንድ ላይ ሆኖ ለመጸለይ ሕዝቡን ሰብስቧል

    • ሥራ 12:1-5, 12-17—ሐዋርያው ያዕቆብ በተገደለበትና ሐዋርያው ጴጥሮስ በታሰረበት ወቅት በኢየሩሳሌም ያለው ጉባኤ አንድ ላይ ተሰብስቦ ጸልዮአል

አዎንታዊ አመለካከት አስቸጋሪ ጊዜን በጽናት ለማለፍ ብርታት የሚሰጠን እንዴት ነው?

ሥራ 5:40, 41፤ ሮም 8:35-39 1ቆሮ 4:11-13፤ 2ቆሮ 4:16-18፤ 1ጴጥ 1:6, 7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 39:19-23፤ 40:1-8—ዮሴፍ በሐሰት ተወንጅሎ በግፍ እስር ቤት ተጥሏል፤ ያም ሆኖ ታማኝነቱን ጠብቋል፤ ሌሎችን መርዳትም ያስደስተው ነበር

    • 2ነገ 6:15-17—ነቢዩ ኤልያስ ታላቅ ሠራዊት ሲመጣበት አልፈራም፤ አገልጋዩም የእሱ ዓይነት አመለካከት እንዲኖረው ጸልዮአል

ከይሖዋ ቃል ማበረታቻ ማግኘት

ይሖዋ ምን ማረጋገጫ ሰጥቶናል?

በይሖዋ ትዕግሥትና ምሕረት ላይ ማሰላሰላችን የሚያበረታታን እንዴት ነው?

ይሖዋ ጉልበታቸው እንደተሟጠጠ ለሚሰማቸው ሰዎች ምን ሊያደርግላቸው ይችላል?

መዝ 46:1፤ ኢሳ 12:2፤ 40:29-31 ፊልጵ 4:13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 1:10, 11, 17, 18—ይሖዋ በጭንቀትና በምሬት የተዋጠችው ሐና ወደ እሱ ስትጸልይ ሰምቷታል፤ ሥቃይዋ ቀለል እንዲልላትም አድርጓል

    • 1ነገ 19:1-19—ነቢዩ ኤልያስ ተስፋ በቆረጠበት ወቅት ይሖዋ ተግባራዊ እርዳታ ሰጥቶታል። ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ በመስጠት አበረታቶታል እንዲሁም አጽናንቶታል

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚሰጠው ተስፋ የሚያበረታታን እንዴት ነው?

2ዜና 15:7፤ መዝ 27:13, 14፤ ዕብ 6:17-19፤ 12:2

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 14:1, 2, 7-9, 13-15—ኢዮብ ስሜቱ እጅግ በተደቆሰበት ወቅትም እንኳ በትንሣኤ ተስፋ ተጽናንቷል

    • ዳን 12:13—ነቢዩ ዳንኤል 100 ዓመት ገደማ ሳለ አንድ መልአክ ስለ ወደፊት ሽልማቱ በመንገር አበረታቶታል

ወደ ይሖዋ መጸለይና ስለ እሱ ማሰላሰል የሚያበረታታን ለምንድን ነው?

መዝ 18:6፤ 56:4, 11፤ ዕብ 13:6

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 30:1-9—ንጉሥ ዳዊት ከባድ ችግር በገጠመው ወቅት ወደ ይሖዋ ዘወር በማለት ብርታት አግኝቷል

    • ሉቃስ 22:39-43—ኢየሱስ በምድራዊ ሕይወቱ እጅግ ተፈታታኝ በሆነ ወቅት ላይ አጥብቆ ጸልዮአል፤ ይሖዋም የሚያበረታታው መልአክ በመላክ መልስ ሰጥቶታል

ጥሩ ዜና መስማትና ለሌሎች ማጋራት የሚያበረታታን እንዴት ነው?

ምሳሌ 15:30፤ 25:25፤ ኢሳ 52:7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 15:2-4—ሐዋርያቱ ጳውሎስና በርናባስ የጎበኟቸውን ጉባኤዎች በእጅጉ አበረታተዋል

    • 3ዮሐ 1-4—አረጋዊው ሐዋርያው ዮሐንስ፣ እውነትን ያስተማራቸው ሰዎች በታማኝነት እየተመላለሱ እንዳሉ መስማቱ በጣም አበረታቶታል