በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይቅር ባይነት

ይቅር ባይነት

ይሖዋ ይቅር ለማለት ምን ያህል ፍላጎት አለው?

መዝ 86:5፤ ዳን 9:9፤ ሚክ 7:18

በተጨማሪም 2ጴጥ 3:9⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 78:40, 41፤ 106:36-46—ዓመፀኛ የሆኑት እስራኤላውያን ብዙ ጊዜ ቢያሳዝኑትም ይሖዋ በተደጋጋሚ ይቅር ብሏቸዋል

    • ሉቃስ 15:11-32—ኢየሱስ የይሖዋን ይቅርታ የሚያጎላ አንድ ምሳሌ ተናግሯል፤ ምሳሌው አንድ መሐሪ አባት፣ ከመጥፎ አካሄዱ የተመለሰውን ልጁን እንዴት እንደያዘው ይተርካል

ይሖዋ ኃጢአታችንን ይቅር የሚለው ምንን መሠረት በማድረግ ነው?

ዮሐ 1:29፤ ኤፌ 1:7፤ 1ዮሐ 2:1, 2

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዕብ 9:22-28—ሐዋርያው ጳውሎስ፣ የክርስቶስ ደም የኃጢአት ይቅርታ የሚገኝበት ብቸኛው መንገድ እንደሆነ አስረድቷል

    • ራእይ 7:9, 10, 14, 15—ሐዋርያው ዮሐንስ፣ በፈሰሰው የክርስቶስ ደም አማካኝነት በአምላክ ዘንድ ንጹሕ ተደርገው የተቆጠሩ “እጅግ ብዙ ሕዝብ” በራእይ ተመልክቷል

ይሖዋ ይቅር እንዲለን ከፈለግን ሌሎች ሲበድሉን ምን ማድረግ አለብን?

ማቴ 6:14, 15፤ ማር 11:25፤ ሉቃስ 17:3, 4፤ ያዕ 2:13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 42:7-10—ይሖዋ የኢዮብ መከራ እንዲያበቃ እንዲሁም ጤንነቱና ብልጽግናው እንዲመለስለት ከማድረጉ በፊት፣ ስህተት ለሠሩት ወዳጆቹ እንዲጸልይ ነግሮታል

    • ማቴ 18:21-35—ኢየሱስ፣ ይቅር መባል ከፈለግን ሌሎችን ይቅር ማለት ያለውን አስፈላጊነት ሕያው በሆነ ምሳሌ አስረድቷል

ኃጢአትን መናዘዝና ከልብ ንስሐ መግባት ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

ሥራ 3:19፤ 26:20፤ 1ዮሐ 1:8-10

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 32:1-5፤ 51:1, 2, 16, 17—ንጉሥ ዳዊት በሠራቸው ከባድ ኃጢአቶች የተነሳ ተደቁሷል እንዲሁም ልቡ ተሰብሯል፤ ደግሞም ለኃጢአቱ ከልቡ ንስሐ ገብቷል

    • ያዕ 5:14-16—ያዕቆብ ከባድ ኃጢአት ከሠራን ለሽማግሌዎች መንገር እንዳለብን ተናግሯል

ይሖዋ ይቅር እንዲለን ከፈለግን ምን ለውጥ ማድረግ አለብን?

ምሳሌ 28:13፤ ኢሳ 55:7፤ ኤፌ 4:28

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ነገ 21:27-29፤ 2ዜና 18:18-22, 33, 34፤ 19:1, 2—ንጉሥ አክዓብ የተላለፈበትን ፍርድ ሲሰማ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ ይሖዋም በተወሰነ መጠን ምሕረት አደረገለት፤ ሆኖም እውነተኛ የንስሐ ፍሬ ስላላሳየ ይሖዋ እሱን ክፉ አድርጎ መመልከቱን አልተወም፤ እንዲሞትም አድርጓል

    • 2ዜና 33:1-16—ምናሴ በጣም ክፉ ንጉሥ ነበር፤ ንስሐ ሲገባ ግን ይሖዋ ይቅር አለው። ምናሴ ጣዖት አምልኮን በማስወገድና እውነተኛውን አምልኮ በማስፋፋት ከልቡ እንደተለወጠ አሳይቷል

ይሖዋ ንስሐ የገቡ ኃጢአተኞችን ይቅር የሚለው እስከ ምን ድረስ ነው?

መዝ 103:10-14፤ ኢሳ 1:18፤ 38:17 ኤር 31:34፤ ሚክ 7:19

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ሳሙ 12:13፤ 24:1፤ 1ነገ 9:4, 5—ንጉሥ ዳዊት በጣም ከባድ ኃጢአቶች ቢፈጽምም ንስሐ በመግባቱ ይሖዋ ይቅር ብሎታል፤ ከጊዜ በኋላ ስለ እሱ ሲናገር ንጹሕ አቋሙን እንደጠበቀ መሥክሮለታል

ኢየሱስ ይቅር ለማለት ፈቃደኛ በመሆን ረገድ ይሖዋን ፍጹም በሆነ መንገድ የመሰለው እንዴት ነው?

መዝ 86:5፤ ሉቃስ 23:33, 34

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 26:36, 40, 41—ኢየሱስ የቅርብ ተከታዮቹን እርዳታ በጣም በሚፈልግበት ወቅት እነሱ እንቅልፍ ወስዷቸው ነበር፤ ሆኖም ኢየሱስ ድካማቸውን ተረድቶላቸዋል

    • ማቴ 26:69-75፤ ሉቃስ 24:33, 34ሥራ 2:37-41—ጴጥሮስ፣ ኢየሱስን አላውቀውም ብሎ ሦስት ጊዜ ክዶታል፤ ንስሐ በመግባቱ ግን ክርስቶስ ይቅር ብሎታል፤ ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለጴጥሮስ በግል ተገልጦለታል፤ በኋላ ላይ ደግሞ በጉባኤው ውስጥ ለየት ያሉ ኃላፊነቶች ሰጥቶታል

የይሖዋ ይቅርታ ገደብ እንዳለው እንዴት እናውቃለን?

ማቴ 12:31፤ ዕብ 10:26, 27፤ 1ዮሐ 5:16, 17

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 23:29-33—ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በቡድን ደረጃ የገሃነም ፍርድ ማለትም ዘላለማዊ ጥፋት እንደሚጠብቃቸው ኢየሱስ አስጠንቅቋል

    • ዮሐ 17:12፤ ማር 14:21—ኢየሱስ የአስቆሮቱ ይሁዳን ‘የጥፋት ልጅ’ ሲል ጠርቶታል፤ ይህ ከሃዲ ባይወለድ ይሻለው እንደነበረም ተናግሯል

ክርስቲያኖች ይቅር ለማለት እንዲነሳሱ ምን ሊረዳቸው ይችላል?