በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሐዘን

ሐዘን

መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ሲሞትብን ማዘን ምንም ስህተት እንደሌለበት የሚያሳየው እንዴት ነው?

ይሖዋ ሐዘን የደረሰባቸውን ሰዎች ማጽናናት እንደሚፈልግ የሚያሳየው ምንድን ነው?

የሞቱ ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ማወቃችን የሚያጽናናን እንዴት ነው?

መክ 9:5, 10፤ 1ተሰ 4:13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 20:37, 38—ትንሣኤ በእርግጠኝነት የሚፈጸም ተስፋ ከመሆኑ የተነሳ የሞቱ ሰዎች በአምላክ ዓይን አሁንም ሕያው የሆኑ ያህል እንደሆነ ኢየሱስ ተናግሯል

    • ዮሐ 11:5, 6, 11-14—ኢየሱስ የቅርብ ወዳጁ አልዓዛር በሞተበት ወቅት ሞትን ከእንቅልፍ ጋር አመሳስሎታል

    • ዕብ 2:14, 15—ሐዋርያው ጳውሎስ የሞት ፍርሃት ባሪያ ሊያደርገን እንደማይገባ ተናግሯል

አንድ ሰው በሕይወቱ ከሚያተርፈው ስም አንጻር ከልደት ቀኑ ይልቅ የሞተበት ቀን የሚሻለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን ምን ብሎ ይገልጸዋል? አምላክ ሞትን ምን ያደርገዋል?

ወደፊት ትንሣኤ እንደሚኖር እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?

ኢሳ 26:19፤ ዮሐ 5:28, 29፤ ሥራ 24:15

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዘጠኝ ትንሣኤዎች ተጠቅሰዋል፤ ስምንቱ ከሞት ተነስተው የኖሩት ምድር ላይ ነው። እያንዳንዱ ዘገባ ሐዘን ለደረሰባቸው ሰዎች መጽናኛና ተስፋ ይሰጣል

      • 1ነገ 17:17-24—ነቢዩ ኤልያስ በሲዶና ከተማ፣ በሰራፕታ መንደር የምትኖርን የአንዲት መበለት ልጅ አስነሳ

      • 2ነገ 4:32-37—ነቢዩ ኤልሳዕ በሹነም፣ አንድን ልጅ ከሞት አስነስቶ ለወላጆቹ ሰጣቸው

      • 2ነገ 13:20, 21—ከሞተ ብዙም ያልቆየ የአንድ ሰው አስከሬን የነቢዩ ኤልሳዕን አፅም እንደነካ ሰውየው ሕያው ሆነ

      • ሉቃስ 7:11-15—በናይን ከተማ ኢየሱስ ለቀብር የሚሄዱ ሰዎችን አስቁሞ የአንዲትን መበለት ልጅ አስነሳ

      • ሉቃስ 8:41, 42, 49-56—ኢየሱስ የምኩራብ አለቃ የሆነውን የኢያኢሮስን ሴት ልጅ ከሞት አስነሳ

      • ዮሐ 11:38-44—ኢየሱስ የቅርብ ወዳጁን አልዓዛርን ከሞት አስነሳው፤ ከእህቶቹ ከማርታና ከማርያም ጋርም አገናኘው

      • ሥራ 9:36-42—ሐዋርያው ጴጥሮስ በደግነቷ በጉባኤው ውስጥ ተወዳጅ የነበረችውን ዶርቃን ከሞት አስነሳት

      • ሥራ 20:7-12—ሐዋርያው ጳውሎስ ከመስኮት ወድቆ የሞተውን አውጤኪስ የተባለ ወጣት ከሞት አስነሳው

    • ኢየሱስ ክርስቶስ የማይሞት መንፈሳዊ አካል ይዞ ከሞት ተነስቷል፤ ይህም ተስፋችን ሁሉ እንደሚፈጸም ዋስትና ይሆናል

    • ኢየሱስ ትንሣኤ አግኝቶ ወደ ሰማይ ለመሄድና የማይሞት መንፈሳዊ አካል ለማግኘት የመጀመሪያው ነው፤ ሆኖም የመጨረሻው አይደለም፤ 144,000 ቅቡዓን ተከታዮቹም ተመሳሳይ ትንሣኤ ያገኛሉ

የሚወዱትን ሰው በሞት አጥተው በሐዘን የተደቆሱትን ማጽናናት የምንችለው እንዴት ነው?