በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትሕትና

ትሕትና

ይሖዋ ለትሑታን ምን አመለካከት አለው? ለትዕቢተኞችስ?

መዝ 138:6፤ ምሳሌ 15:25፤ 16:18, 19፤ 22:4፤ 1ጴጥ 5:5

በተጨማሪም ምሳሌ 29:23፤ ኢሳ 2:11, 12⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 26:3-5, 16-21—ንጉሥ ዖዝያ ታበየ፤ የአምላክን ሕግ የጣሰ ከመሆኑም ሌላ ምክር ሲሰጠው ተቆጣ፤ በዚህም የተነሳ አምላክ በሥጋ ደዌ መታው

    • ሉቃስ 18:9-14—ይሖዋ ትዕቢተኞች ስለሚያቀርቡት ጸሎትና ትሑታን ስለሚያቀርቡት ጸሎት ምን እንደሚሰማው ኢየሱስ በምሳሌ አስረድቷል

አንድ ሰው ራሱን ዝቅ አድርጎ ከልቡ ንስሐ ሲገባ ይሖዋ ምን ምላሽ ይሰጣል?

2ዜና 7:13, 14፤ መዝ 51:2-4, 17

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 12:5-7—ንጉሥ ሮብዓምና የይሁዳ መኳንንት በይሖዋ ፊት ራሳቸውን ዝቅ በማድረጋቸው ከጥፋት ድነዋል

    • 2ዜና 32:24-26—ጥሩው ንጉሥ ሕዝቅያስ ታበየ፤ ሆኖም ራሱን ዝቅ በማድረጉ ይሖዋ ይቅርታ አደረገለት

ትሕትና ከሌሎች ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሻሻል የሚረዳን እንዴት ነው?

ኤፌ 4:1, 2፤ ፊልጵ 2:3፤ ቆላ 3:12, 13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 33:3, 4—ኤሳው ወንድሙን ያዕቆብን ይጠላው ነበር፤ ያዕቆብ ግን ወንድሙን ባገኘው ወቅት ታላቅ ትሕትና በማሳየቱ በመካከላቸው ሰላም ሊወርድ ችሏል

    • መሳ 8:1-3—መስፍኑ ጌድዮን የኤፍሬም ሰዎችን ከእሱ እንደሚሻሉ በትሕትና ነገራቸው፤ ይህም ቁጣቸውን ያበረደው ከመሆኑም ሌላ ግጭት እንዳይፈጠር አድርጓል

ኢየሱስ ትሕትና ያለውን ትልቅ ዋጋ ያስተማረው እንዴት ነው?

ማቴ 18:1-5፤ 23:11, 12፤ ማር 10:41-45

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢሳ 53:7፤ ፊልጵ 2:7, 8—በትንቢት በተነገረው መሠረት ኢየሱስ ምድር ላይ የተሰጠውን ኃላፊነት በትሕትና ተቀብሏል፤ ተሠቃይቶና ተዋርዶ ለመሞትም እንኳ ፈቃደኛ ሆኗል

    • ሉቃስ 14:7-11—ኢየሱስ ትሕትና ያለውን ጥቅም ለማስረዳት በድግስ ቤት ቦታ ስለሚመርጡ ሰዎች ምሳሌ ተናግሯል

    • ዮሐ 13:3-17—ኢየሱስ ራሱን ዝቅ አድርጎ የሐዋርያቱን እግር በማጠብ ለተከታዮቹ የትሕትና ምሳሌ ትቷል

ስለ ራሳችንም ሆነ ስለ ሌሎች ተገቢውን አመለካከት ማዳበራችን ትሑት ለመሆን የሚረዳን እንዴት ነው?

የውሸት ትሕትና ዋጋ የሌለው ለምንድን ነው?