በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንጹሕ አቋም

ንጹሕ አቋም

ንጹሕ አቋም ምንድን ነው?

መዝ 18:23-25፤ 26:1, 2፤ 101:2-7፤ 119:1-3, 80

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘሌ 22:17-22—ይሖዋ፣ እስራኤላውያን የሚያቀርቡት የእንስሳ መሥዋዕት “እንከን የሌለበት” ወይም ሙሉ እንዲሆን አዟል፤ “እንከን የሌለበት” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል “ንጹሕ አቋም” ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር የቅርብ ዝምድና አለው፤ ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው ንጹሕ አቋም ሲባል ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ ያደሩ መሆን ማለት ነው

    • ኢዮብ 1:1, 4, 5, 8፤ 2:3—የኢዮብ ሕይወት እንደሚያሳየው ንጹሕ አቋሙን የሚጠብቅ ሰው ለይሖዋ ጥልቅ አክብሮት አለው፣ በሙሉ ልቡ ያገለግለዋል እንዲሁም በይሖዋ ዓይን ክፉ ከሆነው ነገር ሁሉ ይርቃል

ንጹሕ አቋማችንን መጠበቅ የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

ንጹሕ አቋማችንን ለመጠበቅ የሚያነሳሳን ምንድን ነው?

1ዜና 29:17፤ ምሳሌ 2:7

በተጨማሪም ምሳሌ 27:11፤ 1ዮሐ 5:3⁠ን ተመልከት

ንጹሕ አቋም ማዳበርና አቋማችንን ጠብቀን መመላለስ የምንችለው እንዴት ነው?

ኢያሱ 24:14, 15፤ መዝ 101:2-4

በተጨማሪም ዘዳ 5:29፤ ኢሳ 48:17, 18⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 31:1-11, 16-33—ኢዮብ ከሥነ ምግባር ብልግና በመራቅ እንዲሁም ሌሎችን በደግነትና በአክብሮት በመያዝ ሕይወቱን በሙሉ ንጹሕ አቋሙን ጠብቋል። ለይሖዋ የሚያቀርበው አምልኮ ከጣዖት አምልኮ የጸዳ እንዲሆን አድርጓል፤ አኗኗሩም ከፍቅረ ንዋይ ነፃ ነበር

    • ዳን 1:6-21—ዳንኤልና ሦስቱ ጓደኞቹ ይሖዋን በማያመልኩ ሰዎች መሃል ቢሆኑም በምግብ ምርጫቸው እንኳ ንጹሕ አቋማቸውን ጠብቀዋል

አንድ ሰው በተደጋጋሚ ከባድ ስህተት ቢሠራ ንጹሕ አቋሙን መልሶ ማግኘት ይችላል?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ነገ 9:2-5፤ መዝ 78:70-72—ንጉሥ ዳዊት ከኃጢአቱ ንስሐ ገብቷል፤ የይሖዋን ይቅርታም አግኝቷል፤ በመሆኑም ይሖዋ የሚያስታውሰው በንጹሕ አቋም ጠባቂነቱ ነው

    • ኢሳ 1:11-18—ይሖዋ፣ ሕዝቡን በግብዝነታቸውና በኃጢአታቸው ብዛት አውግዟቸዋል፤ ንስሐ ከገቡና አካሄዳቸውን ካስተካከሉ ግን ሙሉ በሙሉ ንጹሕ እንደሚያደርጋቸው ቃል ገብቷል