በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምሕረት

ምሕረት

ምሕረት ምን ያካትታል?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 51:1, 2—ንጉሥ ዳዊት፣ ይሖዋን ምሕረት ሲለምን ይቅር እንዲለውና ከኃጢአቱ እንዲያነጻው መጠየቁ ነው

    • ሉቃስ 10:29-37—ኢየሱስ ለአንድ አይሁዳዊ ደግነትና አሳቢነት ስላሳየ ሳምራዊ ምሳሌ በመናገር ስለ ምሕረት አስተምሯል

ሁሉም የሰው ልጆች ምሕረት የሚያስፈልጋቸው ለምንድን ነው?

መዝ 130:3፤ መክ 7:20፤ 1ዮሐ 1:8

በተጨማሪም 1ነገ 8:46-50⁠ን ተመልከት

ምሕረት በማሳየት ረገድ ይሖዋ ምን ምሳሌ ትቷል?

ዘፀ 34:6፤ ነህ 9:17፤ መዝ 103:8፤ 2ቆሮ 1:3

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 42:1, 2, 6-10፤ ያዕ 5:11—ይሖዋ ለኢዮብ ምሕረት በማሳየት እሱም በበኩሉ መሐሪ እንዲሆን አስተምሮታል

    • ሉቃስ 15:11-32—ኢየሱስ፣ አንድ አባት ንስሐ ገብቶ ወደ ቤቱ የተመለሰ ዓመፀኛ ልጁን እንዴት እንደተቀበለው የሚያሳይ ምሳሌ በመናገር ስለ ይሖዋ ምሕረት አስተምሯል

ይሖዋ ምሕረት የሚያደርግልን ለምንድን ነው?

ሮም 5:8፤ 1ዮሐ 4:9, 10

በተጨማሪም ቲቶ 3:4, 5⁠ን ተመልከት

የኃጢአት ይቅርታ እንድናገኝ የክርስቶስ መሥዋዕት ምን ሚና አለው?

ምሕረት መለመን ያለብን እንዲሁም ይህን ስጦታ አቅልለን ልንመለከተው የማይገባው ለምንድን ነው?

ሉቃስ 11:2-4፤ ዕብ 4:16

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 51:1-4—በኃጢአቱ የተነሳ በበደለኝነት ስሜት የተደቆሰው ንጉሥ ዳዊት፣ ይሖዋ ምሕረት እንዲያደርግለት በትሕትና ለምኗል

    • ሉቃስ 18:9-14—ኢየሱስ፣ ይሖዋ ምሕረት የሚያሳየው ድክመታቸውን በትሕትና አምነው ለሚቀበሉ ሰዎች እንደሆነ በምሳሌ አስረድቷል

ከባድ ኃጢአት የሠሩ ሰዎችም እንኳ ይሖዋ ምሕረት እንደሚያደርግላቸው ተስፋ ማድረግ የሚችሉት ለምንድን ነው?

ዘዳ 4:29-31፤ ኢሳ 55:7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 33:9-13, 15—እጅግ ክፉ የነበረው ንጉሥ ምናሴ ንስሐ ገብቶ ምሕረት ለመነ፤ ወደ ንግሥናው ከተመለሰ በኋላም በእርግጥ ለውጥ ማድረጉን በተግባር አሳይቷል

    • ዮናስ 3:4-10—ጨካኝና ደም አፍሳሽ የነበሩት የነነዌ ሰዎች ንስሐ በመግባታቸው የአምላክን ምሕረት አግኝተዋል

አንድ ኃጢአተኛ መናዘዙና አካሄዱን መቀየሩ የይሖዋን ምሕረት ለማግኘት የሚረዳው እንዴት ነው?

ይሖዋ ምሕረት ስላደረገልን ብቻ ከቅጣት ወይም ኃጢአታችን ከሚያስከትልብን መዘዝ እናመልጣለን ማለት አይደለም

መሐሪ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

ለሌሎች ምሕረት አለማሳየታችን ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድና የሚነካው እንዴት ነው?

ማቴ 9:13፤ 23:23፤ ያዕ 2:13

በተጨማሪም ምሳሌ 21:13⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 18:23-35—ኢየሱስ፣ ምሕረት የማያደርግ ሰው የይሖዋን ምሕረት እንደማያገኝ በምሳሌ አስረድቷል

    • ሉቃስ 10:29-37—በሰፊው የሚታወቅ አንድ የኢየሱስ ምሳሌ እንደሚጠቁመው ይሖዋና ኢየሱስ ምሕረት በማያደርጉ ሰዎች አይደሰቱም፤ እንደ መሐሪው ሳምራዊ ባሉ ሰዎች ግን ይደሰታሉ

ይሖዋ መሐሪ ለሆኑ ሰዎች ምን ያደርግላቸዋል?