በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ገንዘብ

ገንዘብ

ገንዘብን መውደድ አደገኛ የሆነው ለምንድን ነው?

ፍቅረ ንዋይ” የሚለውን ተመልከት

ቤተሰብን ለማስተዳደር የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት መሥራት ምንም ስህተት እንደሌለው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳየው እንዴት ነው?

መክ 7:12፤ 10:19፤ ኤፌ 4:28፤ 2ተሰ 3:10፤ 1ጢሞ 5:8, 18

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 31:38-42—ያዕቆብ ቤተሰቡን ለማስተዳደር ሲል ለአማቱ ለላባ በሐቀኝነት ሠርቷል፤ ላባ አግባብ ያልሆነ ነገር ቢያደርግበትም ይሖዋ ድካሙን አይቶ ያዕቆብን ባርኮታል

    • ሉቃስ 19:12, 13, 15-23—ኢየሱስ ከተናገረው ምሳሌ እንደምንረዳው ትርፍ ለማግኘት ገንዘብን ሥራ ላይ ማዋል በዘመኑ የተለመደ ነገር ነበር

ገንዘብ ከመበደርና ከማበደር ጋር በተያያዘ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች መመሪያ ይሆኑናል?

አላስፈላጊ ዕዳ ውስጥ አለመግባት የተሻለ የሆነው ለምንድን ነው?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ነህ 5:2-8—በአገረ ገዢው ነህምያ ዘመን የነበሩ አበዳሪዎች በተበዳሪዎቻቸው ላይ ግፍ ይፈጽሙ ነበር

    • ማቴ 18:23-25—ከኢየሱስ ምሳሌ እንደምንረዳው ብድር መመለስ ያልቻለ ተበዳሪ ቅጣት ሊደርስበት ይችላል

አንድ ክርስቲያን፣ ከማያምን ሰውም ሆነ ከእምነት ባልንጀራው ሌላው ቀርቶ ከቤተሰቡ አባል ጋር የንግድ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ምን ጥንቃቄዎች መውሰድ አለበት?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 23:14-20—አብርሃም ለሣራ መቃብር እንዲሆን ዋሻ ያለው እርሻ በገዛ ጊዜ ግዢውን በምሥክሮች ፊት ፈጽሟል፤ ይህን ያደረገው ወደፊት ሊከሰት የሚችል አለመግባባትን ወይም ግጭትን ለማስቀረት ብሎ ሳይሆን አይቀርም

    • ኤር 32:9-12—ነቢዩ ኤርምያስ ከአጎቱ ልጅ መሬት ሲገዛ ውልና ግልባጭ አዘጋጀ፤ ከዚያም ግዢውን በምሥክሮች ፊት ፈጸመ

በጀት ማውጣት ጥበብ የሆነው ለምንድን ነው?

ክርስቲያኖች ከገንዘብ ጋር የተያያዙ አለመግባባቶች በጉባኤው ውስጥ ክፍፍል እንዲፈጥሩ መፍቀድ የሌለባቸው ለምንድን ነው?

1ቆሮ 6:1-8

በተጨማሪም ሮም 12:18፤ 2ጢሞ 2:24⁠ን ተመልከት

እውነተኛ ደስታ የምናገኘው ገንዘባችንን እንዴት ብንጠቀምበት ነው?