በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታዛዥነት

ታዛዥነት

ታዛዥነት ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

ዘፀ 19:5፤ ዘዳ 10:12, 13፤ መክ 12:13 ያዕ 1:22

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 15:17-23—ነቢዩ ሳሙኤል፣ የይሖዋን ትእዛዝ በመጣሱ ንጉሥ ሳኦልን ገሥጾታል፤ ከዚያም ሳሙኤል የታዛዥነትን አስፈላጊነት አበክሮ ነግሮታል

    • ዕብ 5:7-10—ኢየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊትም ፍጹም የአምላክ ልጅ ነው፤ ሆኖም ምድር ላይ ከደረሰበት መከራ መታዘዝን ተምሯል

አንድ ክርስቲያን፣ አንድ ባለሥልጣን የይሖዋን ትእዛዝ እንዲጥስ ቢጠይቀው ምን ማድረግ ይኖርበታል?

ሥራ 5:29

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዳን 3:13-18—ሦስት ታማኝ ዕብራውያን፣ ሕይወታቸውን ሊያሳጣቸው እንደሚችል ቢያውቁም ንጉሥ ናቡከደነጾር ላቆመው ምስል ለመስገድ ፈቃደኛ አልሆኑም

    • ማቴ 22:15-22—ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሚታዘዙት የይሖዋን ትእዛዝ የሚያስጥስ ነገር እስካልጠየቋቸው ድረስ እንደሆነ ተናግሯል

    • ሥራ 4:18-31—ሐዋርያት መስበካቸውን እንዲያቆሙ ሥልጣን ላይ ካሉ ሰዎች ቢነገራቸውም በድፍረት መስበካቸውን ቀጥለዋል

ምንጊዜም ለይሖዋ ታዛዥ ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?

ዘዳ 6:1-5፤ መዝ 112:1፤ 1ዮሐ 5:2, 3

በተጨማሪም መዝ 119:11, 112፤ ሮም 6:17⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዕዝራ 7:7-10—ታማኙ ካህን ዕዝራ፣ ግንባር ቀደም ሆኖ የአምላክን ሕግ መታዘዝ እንዲሁም ለሌሎች ማስተማር እንዲችል ልቡን አዘጋጅቷል

    • ዮሐ 14:31—ኢየሱስ ልክ አባቱ እንዳዘዘው የሚያደርገው ለምን እንደሆነ ተናግሯል

ይሖዋንና ኢየሱስን ለመታዘዝ የሚያነሳሳን ምንድን ነው?

መታዘዝ የእምነታችንን መጠን የሚያሳየው እንዴት ነው?

ሮም 1:5፤ 10:16, 17፤ ያዕ 2:20-23

በተጨማሪም ዘዳ 9:23⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 6:9-22፤ ዕብ 11:7—ኖኅ፣ ይሖዋ መርከብ እንዲሠራ ባዘዘው መሠረት “ልክ እንደዚሁ” በማድረግ እምነቱን አሳይቷል

    • ዕብ 11:8, 9, 17—አብርሃም ዑርን ለቅቆ እንዲወጣ ብቻ ሳይሆን የገዛ ልጁን መሥዋዕት እንዲያደርግ ይሖዋ የሰጠውን ትእዛዝ በመጠበቅ እምነት እንዳለው አሳይቷል

ይሖዋ ታዛዥነትን የሚባርከው እንዴት ነው?

ኤር 7:23፤ ማቴ 7:21፤ 1ዮሐ 3:22

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘሌ 26:3-6—ይሖዋ እሱን የሚታዘዙትን እንደሚባርካቸውና እንደሚንከባከባቸው ቃል ገብቷል

    • ዘኁ 13:30, 31፤ 14:22-24—ካሌብ የታዛዥነት መንፈስ አሳይቷል፤ በመሆኑም ይሖዋ ባርኮታል

አለመታዘዝ ምን ያስከትላል?

ሮም 5:19፤ 2ተሰ 1:8, 9

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 2:16, 17፤ 3:17-19—አዳምና ሔዋን ይሖዋን ባለመታዘዛቸው ከገነት ተባረሩ፤ ፍጽምናቸውንና የዘላለም ሕይወት አጡ

    • ዘዳ 18:18, 19፤ ሥራ 3:12, 18, 22, 23—ይሖዋ፣ ከሙሴ የሚበልጥ ነቢይ እንደሚነሳ ትንቢት በተናገረበት ወቅት ይህን ነቢይ አለመታዘዝ ከባድ መዘዝ እንደሚያስከትል ጠቁሟል

    • ይሁዳ 6, 7—የዓመፀኞቹ መላእክት እንዲሁም የሰዶምና ገሞራ ነዋሪዎች አለመታዘዝ የይሖዋን ቁጣ ቀስቅሶታል

ኢየሱስ ክርስቶስን መታዘዝ ያለብን ለምንድን ነው?

ዘፍ 49:10፤ ማቴ 28:18

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዮሐ 12:46-48፤ 14:24—ኢየሱስ የእሱን ቃል የማይታዘዙ ሰዎች እንደሚፈረድባቸው ተናግሯል

ክርስቲያኖች በጉባኤ ውስጥ ለበላይ ተመልካቾች መታዘዝ ያለባቸው ለምንድን ነው?

ክርስቲያን ሚስት ለባሏ መገዛት ያለባት ለምንድን ነው?

ልጆች ለወላጆቻቸው የሚታዘዙት ለምንድን ነው?

ምሳሌ 23:22፤ ኤፌ 6:1፤ ቆላ 3:20

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 37:3, 4, 8, 11-13, 18—ወጣቱ ዮሴፍ ወንድሞቹ እንደሚጠሉት እያወቀም አባቱ ወደ እነሱ እንዲሄድ የሰጠውን ትእዛዝ አክብሯል

    • ሉቃስ 2:51—ፍጹም የሆነው ኢየሱስ፣ ፍጹም ላልሆኑት ወላጆቹ ለዮሴፍና ለማርያም ሁልጊዜ ይገዛላቸው ነበር

ከሌሎች እይታ ውጭ በምንሆንበት ጊዜም እንኳ አሠሪያችንን መታዘዝ ያለብን ለምንድን ነው?

ክርስቲያኖች ለመንግሥታት የሚታዘዙት ለምንድን ነው?