በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አረጋውያን፤ እርጅና

አረጋውያን፤ እርጅና

ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ምን ይከሰታል?

መዝ 71:9፤ 90:10

በተጨማሪም “ማጽናኛ—በሕመም ወይም በእርጅና ምክንያት አቅማችን ሲገደብ” የሚለውን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መክ 12:1-8—ንጉሥ ሰለሞን በእርጅና ምክንያት የሚመጡ አንዳንድ እክሎችን በዘይቤ ገልጿል፤ ለምሳሌ የዓይን መድከም (“በመስኮት የሚያዩ ወይዛዝርትም ይጨልምባቸዋል”) እና የጆሮ መድከም (“ሴቶች ልጆችም ሁሉ ዝግ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ”)

አረጋውያን በእርጅና ምክንያት የሚመጡ ችግሮች እያሉም እንዲሁም አቅማቸው ቢደክምም ደስታቸውን ጠብቀው መኖር ይችላሉ?

2ቆሮ 4:16-18፤ ያዕ 1:2-4

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 12:2, 23—አረጋዊው ነቢይ ሳሙኤል ለይሖዋ ሕዝቦች መጸለዩን መቀጠሉ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ተገንዝቧል

    • 2ሳሙ 19:31-39—ንጉሥ ዳዊት አረጋዊው ቤርዜሊ ላሳየው ታማኝነትና ላደረገለት ድጋፍ አመስጋኝ ነበር፤ ቤርዜሊም ዳዊት ያቀረበለትን ግብዣ ለመቀበል አቅሙ እንደማይፈቅድለት በመግለጽ ልኩን እንደሚያውቅ አሳይቷል

    • መዝ 71:9, 18—ንጉሥ ዳዊት ካረጀ በኋላ በይሖዋ ዘንድ ጠቃሚነቱን እንዳያጣ ሰግቶ ነበር፤ በመሆኑም ‘አትጣለኝ’ ብሎ ይሖዋን ለምኖታል፤ ለቀጣዩ ትውልድ ስለ እሱ ለመናገር ብርታት እንዲሰጠውም ጠይቋል

    • ሉቃስ 2:36-38—መበለት የነበረችው አረጋዊቷ ነቢዪት ሐና፣ ለአምላክ ያደረች በመሆኗ እና እሱን በታማኝነት በማገልገሏ ተባርካለች

ይሖዋ አረጋውያንን ከፍ አድርጎ እንደሚመለከታቸው ያረጋገጠላቸው እንዴት ነው?

መዝ 92:12-14፤ ምሳሌ 16:31፤ 20:29 ኢሳ 46:4፤ ቲቶ 2:2-5

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 12:1-4—ይሖዋ ለአብርሃም ሕይወቱን የሚቀይር ተልእኮ የሰጠው የ75 ዓመት ሰው ሳለ ነው

    • ዳን 10:11, 19፤ 12:13—አንድ መልአክ በ90ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለውን ዳንኤልን አነጋግሮታል፤ በይሖዋ ዘንድ የተወደደ እንደሆነና ለታማኝነቱ ወሮታ እንደሚያገኝ ገልጾለታል

    • ሉቃስ 1:5-13—ይሖዋ አረጋውያኑን ዘካርያስንና ኤልሳቤጥን በተአምር ዮሐንስን እንዲወልዱ በማድረግ ባርኳቸዋል

    • ሉቃስ 2:25-35—ይሖዋ፣ መሲሕ የሚሆነውን ሕፃን እንዲያይ በማድረግ አረጋዊውን ስምዖንን ባርኮታል፤ ስምዖን በመንፈስ መሪነት ስለ መሲሑ ትንቢት ተናግሯል

    • ሥራ 7:23, 30-36—ነቢዩ ሙሴ የይሖዋ ሕዝብ የሆኑትን እስራኤላውያንን እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው በ80 ዓመቱ ነው

ታማኝ የሆኑ አረጋውያንን እንዴት ልንይዛቸው ይገባል?

ዘሌ 19:32፤ 1ጢሞ 5:1

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 45:9-11፤ 47:12—ዮሴፍ አረጋዊው አባቱ ያዕቆብ ወደ እሱ እንዲመጣ አድርጓል፤ እስከ ዕለተ ሞቱም ተንከባክቦታል

    • ሩት 1:14-17፤ 2:2, 17, 18, 23—ሩት አረጋዊቷን ናኦሚን በንግግርም ሆነ በተግባር ደግፋታለች

    • ዮሐ 19:26, 27—ኢየሱስ እንጨት ላይ ተሰቅሎ እያጣጣረ በነበረበት ወቅት እናቱን እንዲንከባከብለት የሚወደውን ሐዋርያ ዮሐንስን አደራ ብሎታል

ክርስቲያኖች በጉባኤ ውስጥ ያሉ አረጋውያንን ማገዝ የሚችሉባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?