በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ወላጆች

ወላጆች

ይሖዋ ጋብቻን ካቋቋመባቸው ምክንያቶች አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው?

ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ሊያዩአቸው ይገባል?

መዝ 127:3-5፤ 128:3

በተጨማሪም “ልጆች፤ ወጣቶች” የሚለውን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 33:4, 5—ያዕቆብ ልጆቹን ከይሖዋ ያገኛቸው በረከቶች አድርጎ ተመልክቷቸዋል

    • ዘፀ 1:15, 16, 22፤ 2:1-4፤ 6:20—የሙሴ ወላጆች የሆኑት አምራምና ዮካቤድ እሱን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲሉ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለዋል

ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በተያያዘ ምን ኃላፊነት አለባቸው?

ዘዳ 6:6, 7፤ 11:18, 19፤ ምሳሌ 22:6 2ቆሮ 12:14፤ 1ጢሞ 5:8

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 1:1-4—ሕልቃና ልጆቹ በሙሉ በይሖዋ አምልኮ እንዲሳተፉ ስለፈለገ በበዓላት ወቅት መላ ቤተሰቡን ወደ ሴሎ ይዞ ይሄድ ነበር

    • ሉቃስ 2:39, 41—ዮሴፍና ማርያም የፋሲካ በዓልን ለማክበር ልጆቻቸውን ይዘው ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም የመሄድ ልማድ ነበራቸው

ልጆችን በይሖዋ መንገድ ማሠልጠን ምን ጥቅም አለው?

ምሳሌ 1:8, 9፤ 22:6

በተጨማሪም 2ጢሞ 3:14, 15⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 2:18-21, 26፤ 3:19—የሳሙኤል ወላጆች በማደሪያው ድንኳን እንዲያገለግል ልጃቸውን ሰጥተዋል፤ ይሁንና አዘውትረው እየሄዱ ይጠይቁት እንዲሁም የሚያስፈልገውን ነገር ይወስዱለት ነበር፤ ሳሙኤል ካደገ በኋላ መንፈሳዊ ሰው ሊሆን ችሏል

    • ሉቃስ 2:51, 52—ኢየሱስ፣ ፍጹም ባይሆኑም እንኳ ለወላጆቹ ሁልጊዜ ይገዛ ነበር

ወላጆች ልጆቻቸውን ለማሳደግ የሚረዳ መመሪያ ከየት ማግኘት ይችላሉ?

ዘዳ 6:4-9፤ ኤፌ 6:4፤ 2ጢሞ 3:14-17

በተጨማሪም መዝ 127:1፤ ምሳሌ 16:3⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መሳ 13:2-8—ማኑሄ፣ ሚስቱ በተአምር ልጅ እንደምትወልድ ሲነገረው ልጁን ማሳደግ ስለሚችሉበት መንገድ ተጨማሪ መመሪያ እንዲሰጠው ጠይቋል

    • መዝ 78:3-8—ይሖዋ፣ ወላጆች ከቅዱሳን መጻሕፍት ያገኙትን እውቀት ለልጆቻቸው እንዲያስተምሩ ይፈልጋል

አንድ ልጅ አምላክን በሚወድ ቤተሰብ ውስጥ አድጎም እንኳ ይሖዋን ማገልገሉን ሊተው የሚችለው ለምንድን ነው?

ሕዝ 18:1-13, 20

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 6:1-5፤ ይሁዳ 6—አንዳንድ የአምላክ መንፈሳዊ ልጆች ከይሖዋ ጋር ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ዘመናት አብረው ቢኖሩም በእሱ ላይ ለማመፅ መርጠዋል

    • 1ሳሙ 8:1-3—ሳሙኤል ታማኝና ጻድቅ ነቢይ ቢሆንም ልጆቹ አጭበርባሪዎችና ምግባረ ብልሹዎች ሆነዋል

ወላጆች የአምላክን መንገዶች ለልጆቻቸው ማስተማር መጀመር ያለባቸው መቼ ነው?

2ጢሞ 3:15

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘዳ 29:10-12, 29፤ 31:12፤ ዕዝራ 10:1 —የይሖዋን መንገዶች ለመማር ከሚሰበሰበው ሕዝብ መካከል ልጆችም ይገኙበታል

    • ሉቃስ 2:41-52—ዮሴፍና ማርያም የፋሲካ በዓል በሚከበርበት ወቅት ኢየሱስን ጨምሮ ልጆቻቸውን በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መቅደስ የመውሰድ ልማድ ነበራቸው

ወላጆች ልጆቻቸውን ሊጎዷቸው ከሚችሉ ሰዎች እንዲጠብቁ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ትምህርት ይሆኗቸዋል?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፀ 19:4፤ ዘዳ 32:11, 12—ይሖዋ ጫጩቶቿን ከምትሸከም፣ ከምትጠብቅና ከምትንከባከብ ንስር ጋር ራሱን አመሳስሏል

    • ኢሳ 49:15—ይሖዋ አገልጋዮቹን ለመንከባከብና ለመጠበቅ ቃል ገብቷል፤ ይህ የይሖዋ ርኅራኄ የምታጠባ እናት ለልጇ ካላት ስሜትም እንኳ የላቀ ነው

    • ማቴ 2:1-16—ሰይጣን፣ አረማውያን ኮከብ ቆጣሪዎችን ወደ ክፉው ንጉሥ ሄሮድስ በመምራት ሕፃኑን ኢየሱስን ሊያስገድለው ሞክሯል፤ ይሖዋ ግን ዮሴፍ ቤተሰቡን ይዞ ወደ ግብፅ እንዲሄድ በመንገር ልጁን ጠብቆታል

    • ማቴ 23:37—ኢየሱስ፣ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር በመሰብሰብ እንደምትጠብቃቸው ሁሉ እሱም ሕዝቡን መርዳት እንደሚፈልግ ተናግሯል

ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ፆታ ማስተማር ያለባቸው ለምንድን ነው?

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘሌ 15:2, 3, 16, 18, 19፤ ዘዳ 31:10-13—የሙሴ ሕግ ስለ ፆታ ጉዳዮች በግልጽ ይናገራል፤ ይህ ሕግ ለሕዝቡ በሚነበብበት ወቅት ደግሞ ልጆችም እንዲገኙ ይሖዋ አዟል

    • መዝ 139:13-16—መዝሙራዊው ዳዊት የመራባት ሥርዓትን ጨምሮ የሰው አካል ስለተፈጠረበት አስደናቂ መንገድ ይሖዋን አወድሶታል

    • ምሳሌ 2:10-15—ከይሖዋ የሚገኘው እውቀትና ጥበብ ክፉና ተንኮለኛ ከሆኑ ሰዎች ይጠብቀናል

ተግሣጽ በፍቅር ሊሰጥ የሚገባው ለምንድን ነው?

ምሳሌ 13:24፤ 29:17፤ ኤር 30:11፤ ኤፌ 6:4

በተጨማሪም መዝ 25:8፤ 145:9፤ ቆላ 3:21⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 32:1-5—ንጉሥ ዳዊት የይሖዋ ተግሣጽ ከብዶታል፤ ሆኖም ይሖዋ ከኃጢአታቸው ልባዊ ንስሐ የሚገቡ ሰዎችን ይቅር እንደሚል ማወቁ አጽናንቶታል

    • ዮናስ 4:1-11—ነቢዩ ዮናስ፣ ይሖዋን በቁጣና አክብሮት በጎደለው መንገድ አነጋግሮታል፤ ሆኖም ይሖዋ ምሕረት ስለማሳየት በትዕግሥት አስተምሮታል

ተግሣጽ የፍቅር መግለጫ ተደርጎ ሊታይ የሚገባው ለምንድን ነው?

ምሳሌ 3:11, 12፤ 13:24

በተጨማሪም ምሳሌ 15:32፤ ራእይ 3:19⁠ን ተመልከት