በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ስብከት፤ ምሥራቹን መስበክ

ስብከት፤ ምሥራቹን መስበክ

ሁሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች እምነታቸውን በይፋ መናገር ያለባቸው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ከስብከቱ ሥራ ጋር በተያያዘ ምን ምሳሌ ትቷል?

ሉቃስ 8:1፤ ዮሐ 18:37

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 4:42-44—ኢየሱስ ወደ ምድር የተላከው ለመስበክ መሆኑን ተናግሯል

    • ዮሐ 4:31-34—ኢየሱስ የስብከቱ ሥራ ለእሱ እንደ ምግብ መሆኑን ገልጿል

ምሥራቹን የመስበክ ኃላፊነት ያለባቸው በጉባኤ ውስጥ አመራር የሚሰጡ ወንዶች ብቻ ናቸው?

መዝ 68:11፤ 148:12, 13፤ ሥራ 2:17, 18

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ነገ 5:1-4, 13, 14, 17—አንዲት እስራኤላዊት ልጅ የይሖዋ ነቢይ ስለሆነው ስለ ኤልሳዕ ለሶርያዊት እመቤቷ ነግራታለች

    • ማቴ 21:15, 16—የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ቤተ መቅደሱ ውስጥ ሕፃናት ኢየሱስን ሲያወድሱ በመስማታቸው አልተደሰቱም፤ ኢየሱስ ግን ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት እርማት ሰጥቷቸዋል

ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች ምሥራቹን በመስበክና ሌሎችን በማስተማር ረገድ ምን ድርሻ አላቸው?

ይሖዋና ኢየሱስ የስብከቱን ሥራ ለማከናወን የሚረዱን እንዴት ነው?

2ቆሮ 4:7፤ ፊልጵ 4:13፤ 2ጢሞ 4:17

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 16:12, 22-24፤ 1ተሰ 2:1, 2 —ሐዋርያው ጳውሎስና ጓደኞቹ እንግልት ቢደርስባቸውም በአምላክ እርዳታ በድፍረት መስበካቸውን ቀጥለዋል

    • 2ቆሮ 12:7-9—በስብከቱ ሥራ ደከመኝ ሰለቸኝ የማያውቀው ሐዋርያው ጳውሎስ ‘ሥጋውን የሚወጋ እሾህ’ ነበረበት፤ ይህም የጤና እክል ሳይሆን አይቀርም፤ ያም ሆነ ይህ ይሖዋ በስብከቱ ሥራ ለመቀጠል የሚያስችል ብርታት ሰጥቶታል

አንድ ክርስቲያን የመስበክ ብቃት የሚያገኘው ከማን ነው?

1ቆሮ 1:26-28፤ 2ቆሮ 3:5፤ 4:13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዮሐ 7:15—ኢየሱስ የረቢዎች ትምህርት ቤት ሳይገባ እንዲህ ያለ እውቀት ማግኘቱ የአገሩን ሰዎች አስገርሟቸዋል

    • ሥራ 4:13—የኢየሱስ ሐዋርያት ያልተማሩና ተራ ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው ይታዩ ነበር፤ ሆኖም ቀናተኛና ደፋር ሰባኪዎች ነበሩ

ይሖዋ በስብከቱና በማስተማሩ ሥራ ሌሎችን እንድናሠለጥን እንደሚፈልግ እንዴት እናውቃለን?

ማር 1:17፤ ሉቃስ 8:1፤ ኤፌ 4:11, 12

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢሳ 50:4, 5—መሲሑ ሰው ከመሆኑ በፊት ከይሖዋ አምላክ በግል ሥልጠና አግኝቷል

    • ማቴ 10:5-7—ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ደቀ መዛሙርቱ የስብከቱን ሥራ እንዲያከናውኑ በትዕግሥት አሠልጥኗቸዋል

ምሥራቹን ለመስበኩ ሥራ ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል?

አንድ ክርስቲያን በስብከቱ ሥራ መካፈሉ ምን ስሜት ይፈጥርበታል?

የስብከቱ ሥራችን የትኞቹን መልእክቶች ያካተተ ነው?

ክርስቲያኖች የሐሰት ትምህርቶችን የሚያጋልጡት ለምንድን ነው?

2ቆሮ 10:4, 5

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማር 12:18-27—ኢየሱስ፣ ሰዱቃውያን ለትንሣኤ ያላቸው አመለካከት ስህተት መሆኑን ከቅዱሳን መጻሕፍት ጠቅሶ አስረድቷል

    • ሥራ 17:16, 17, 29, 30—ሐዋርያው ጳውሎስ ጣዖት አምልኮ ስህተት መሆኑን ለአቴንስ ሰዎች አስረድቷቸዋል

የስብከቱን ሥራ የምናከናውነው እንዴት ነው?

ሕዝብ በሚገኝባቸው ቦታዎች ምሥክርነት ለመስጠት መሠረት የሚሆነን ምንድን ነው?

ዮሐ 18:20፤ ሥራ 16:13፤ 17:17፤ 18:4

በተጨማሪም ምሳሌ 1:20, 21⁠ን ተመልከት

አገልግሎታችን ትዕግሥትና አለመታከት የሚጠይቀው ለምንድን ነው?

የስብከቱ ሥራችን ምን መልካም ውጤት ያስገኛል?

ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ መመሥከራችን ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?

1ቆሮ 9:23፤ 1ጢሞ 2:4፤ 1ጴጥ 3:15

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዮሐ 4:6, 7, 13, 14—ኢየሱስ ቢደክመውም እንኳ በውኃ ጉድጓድ አጠገብ ላገኛት ሳምራዊት ሴት ምሥራቹን ሰብኳል

    • ፊልጵ 1:12-14—ሐዋርያው ጳውሎስ በእምነቱ ምክንያት ታስሮ እያለም እንኳ አጋጣሚዎችን ተጠቅሞ ምሥክርነት ሰጥቷል እንዲሁም ሌሎችን አበረታቷል

ሁሉም ሰው መልእክታችንን እንደሚሰማ ልንጠብቅ ይገባል?

ዮሐ 10:25, 26፤ 15:18-20 ሥራ 28:23-28

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኤር 7:23-26—ይሖዋ፣ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል እንደገለጸው በነቢያቱ አማካኝነት በተደጋጋሚ ቢነግራቸውም ሕዝቡ ጆሮ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም

    • ማቴ 13:10-16—ኢየሱስ በኢሳይያስ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ብዙዎች መልእክቱን ቢሰሙም ምላሽ እንደማይሰጡ ተናግሯል

ብዙ ሰዎች መልእክታችንን ለመስማት ጊዜ እንደሌላቸው ቢሰማቸው ሊገርመን የማይገባው ለምንድን ነው?

ምሥራቹን የሚሰሙ አንዳንዶች መጀመሪያ ላይ ጥሩ ምላሽ ቢሰጡም በዚያው ላይቀጥሉ እንደሚችሉ የሚያሳየው ምንድን ነው?

አንዳንዶች የስብከቱን ሥራችንን በቀጥታ ቢቃወሙ ልንገረም እንደማይገባ የሚያሳዩት ምሳሌዎች የትኞቹ ናቸው?

የስብከቱን ሥራ በምናከናውንበት ወቅት ተቃውሞ ሲገጥመን ምን ምላሽ ልንሰጥ ይገባል?

አንዳንዶች ለምሥራቹ አዎንታዊ ምላሽ እንደሚሰጡ እርግጠኞች የምንሆነው ለምንድን ነው?

የምሥራቹ ሰባኪዎች በአምላክ ፊት ምን ከባድ ኃላፊነት አለባቸው?

ሥራ 20:26, 27፤ 1ቆሮ 9:16, 17 1ጢሞ 4:16

በተጨማሪም ሕዝ 33:8⁠ን ተመልከት

ሃይማኖት፣ ዘር ወይም ዜግነት ሳንለይ ለሁሉም ሰው መስበክ ያለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 24:14፤ ሥራ 10:34, 35፤ ራእይ 14:6

በተጨማሪም መዝ 49:1, 2⁠ን ተመልከት

ሰንበትን ጨምሮ በማንኛውም ቀን ብንሰብክ ተገቢ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ወይም ሃይማኖት ያላቸውን ሰዎች ጨምሮ ለሁሉም ሰው መስበካችን ተገቢ እንደሆነ የትኞቹ ምሳሌዎች ያሳያሉ?