በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንስሐ

ንስሐ

የሰው ልጆች ሁሉ ንስሐ መግባትና ይሖዋ ይቅር እንዲላቸው መጠየቅ የሚያስፈልጋቸው ለምንድን ነው?

ሮም 3:23፤ 5:12፤ 1ዮሐ 1:8

በተጨማሪም ሥራ 26:20⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 18:9-14—ኢየሱስ ኃጢአታችንን መናዘዝና አምላክ እንዲረዳን መጸለይ የግድ እንደሚያስፈልገን የሚያሳይ ምሳሌ ተናግሯል

    • ሮም 7:15-25—ጳውሎስ፣ ሐዋርያ እና ግሩም የእምነት ምሳሌ ቢሆንም በሚታገለው የኃጢአት ዝንባሌ የተነሳ ይረበሽ ነበር

ይሖዋ ንስሐ ለሚገቡ ሰዎች ስላለው ስሜት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሕዝ 33:11፤ ሮም 2:4፤ 2ጴጥ 3:9

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 15:1-10—ኢየሱስ፣ አንድ ኃጢአተኛ ንስሐ ሲገባ ይሖዋና መላእክት ምን ያህል እንደሚደሰቱ የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ተናግሯል

    • ሉቃስ 19:1-10—የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ የሆነው ዘኬዎስ ቀደም ሲል ከሰዎች በመቀማት ለፈጸመው ድርጊት ንስሐ ገብቷል፤ አካሄዱንም አስተካክሏል፤ ይህም ይቅርታና መዳን አስገኝቶለታል

ከልብ ንስሐ እንደገባን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ከልቡ ንስሐ የገባ ሰው ትክክለኛ እውቀት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

ሮም 12:2፤ ቆላ 3:9, 10፤ 2ጢሞ 2:25

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 17:29-31—ሐዋርያው ጳውሎስ ጣዖት አምልኮ፣ ሰዎች ባለማወቅ የሚያደርጉት ነገር እንደሆነ ካብራራ በኋላ የአቴንስ ሰዎችን ንስሐ እንዲገቡ አሳስቧል

    • 1ጢሞ 1:12-15—ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛ እውቀት ከማግኘቱ በፊት ባለማወቅ አስከፊ ኃጢአቶች ፈጽሟል

ንስሐ መግባት ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

ብዙ ጊዜ ኃጢአት ብንሠራም እንኳ ንስሐ ከገባን ይሖዋ ይቅር እንደሚለን እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?

ይሖዋ ኃጢአታቸውን ለሚናዘዙና አካሄዳቸውን ለሚያስተካክሉ ሰዎች ምን ያደርግላቸዋል?

መዝ 32:5፤ ምሳሌ 28:13፤ 1ዮሐ 1:9

በተጨማሪም “ምሕረት” የሚለውን ተመልከት

ንስሐ መግባት እንዲሁ ‘አጥፍቻለሁ’ ከማለት ወይም ከተራ የጸጸት ስሜት ያለፈ ነገር እንደሚጠይቅ እንዴት እናውቃለን?

2ዜና 7:14፤ ምሳሌ 28:13፤ ሕዝ 18:30, 31፤ 33:14-16፤ ማቴ 3:8፤ ሥራ 3:19፤ 26:20

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 33:1-6, 10-16—ንጉሥ ምናሴ ለረጅም ጊዜ ክፉ ድርጊት ቢፈጽምም እውነተኛ የንስሐ ዝንባሌ አሳይቷል፤ ራሱን ዝቅ አድርጓል፤ ደጋግሞ ጸልዮአል እንዲሁም አካሄዱን አስተካክሏል

    • መዝ 32:1-6፤ 51:1-4, 17—ንጉሥ ዳዊት ይሖዋን በመበደሉ ከልቡ በመጸጸት፣ ኃጢአቱን በመናዘዝና በመጸለይ ንስሐ ገብቷል

የበደሉን ሰዎች መጸጸታቸውን ካሳዩ ይቅር ልንላቸው የሚገባው ለምንድን ነው?

ማቴ 6:14, 15፤ 18:21, 22፤ ሉቃስ 17:3, 4

በተጨማሪም “ይቅር ባይነት” የሚለውን ተመልከት