በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኃጢአት

ኃጢአት

ኃጢአት ምንድን ነው? ሁላችንንም የሚነካንስ እንዴት ነው?

ከኃጢአት ዝንባሌዎች ጋር በምናደርገው ትግል እንደሚሳካልን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ዋስትና ይሰጣል?

ሮም 6:12-14

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ሳሙ 11:2-5, 14, 15, 26, 27፤ 12:1-13—ንጉሥ ዳዊት በጣም ከባድ ኃጢአቶች ሠርቷል፤ ጠንካራ ተግሣጽ ተሰጥቶታል፤ አካሄዱን ለማስተካከልም የቻለውን ሁሉ አድርጓል

    • ሮም 7:15-24—በእምነትና ለአምላክ በማደር ግሩም ምሳሌ የሆነው ሐዋርያው ጳውሎስ ከኃጢአት ዝንባሌዎች ጋር እንደሚታገል ገልጿል

ብዙ ሰዎች ባለማወቅና ተታልለው ኃጢአት የሚሠሩት እንዴት ነው?

ሥራ 3:17፤ 17:29, 30፤ 1ጢሞ 1:13 1ጴጥ 1:14

በተጨማሪም ዘኁ 15:27-29⁠ን ተመልከት

ሆን ብሎ ኃጢአትን ልማድ ማድረግ የበለጠ ክብደት የሚሰጠው ለምንድን ነው?

ሰይጣን፣ የአምላክ አገልጋዮች ኃጢአት እንዲፈጽሙ ለማድረግ ምን ማባበያዎች ይጠቀማል?

ምሳሌ 1:10, 11, 15፤ ማቴ 5:28 ያዕ 1:14, 15

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 3:1-6—ሰይጣን በእባብ ተጠቅሞ ሔዋንን አነጋገራት፤ በውስጧ የራስ ወዳድነት ምኞት በመቀስቀስና በይሖዋ ላይ ያላት እምነት እንዲቀንስ በማድረግ ፈተናት

    • ምሳሌ 7:6-10, 21-23—ማስተዋል የጎደለው አንድ ወጣት፣ ምግባረ ብልሹ የሆነች ሴት ላቀረበችለት ማባበያ እንዴት እጅ እንደሰጠ ንጉሥ ሰለሞን ገልጿል

የሰይጣንን ፈተናዎች መቋቋም የምንችለው እንዴት ነው?

ኤፌ 4:27፤ 6:10-18፤ ያዕ 4:7, 8

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ምሳሌ 5:1-14—ንጉሥ ሰለሞን ከፆታ ብልግና መራቅ አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያትና ይህን ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ አባታዊ ምክር ሰጥቷል

    • ማቴ 4:1-11—ኢየሱስ የአምላክን ቃል ተጠቅሞ ለሰይጣን መሠሪ ፈተናዎች መልስ በመስጠት ፍጹም ምሳሌ ትቷል

ክርስቲያኖች ሊርቋቸው የሚገቡ አንዳንድ ከባድ ኃጢአቶች የትኞቹ ናቸው?

መጥፎ ልማዶች” የሚለውን ተመልከት

ኃጢአትን መናዘዝ

ኃጢአታችንን ለመደበቅ መሞከር የሌለብን ለምንድን ነው?

ኃጢአታችንን ሁሉ መናዘዝ ያለብን ለማን ነው?

ስለ እኛ ይሖዋን በመማለድ “ረዳት” የሚሆንልን ማን ነው?

ኃጢአት የሠራ ሰው ንስሐ መግባቱን በተግባሩ ማሳየት ይችላል?

ሥራ 26:20፤ ያዕ 4:8-10

በተጨማሪም “ንስሐ” የሚለውን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፀ 22:1-12—በሙሴ ሕግ መሠረት አንድ ሌባ፣ ለሰረቃቸው ሰዎች ካሳ መክፈል ይጠበቅበት ነበር

    • ሉቃስ 19:8, 9—የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ የሆነው ዘኬዎስ፣ አካሄዱን በማስተካከልና የበደላቸውን ሰዎች በመካስ ንስሐ መግባቱን አሳይቷል

ይሖዋ ይቅር እንደሚለን መተማመን የምንችለው ለምንድን ነው?

ይቅር ባይነት” የሚለውን ተመልከት

አንድ ሰው ከባድ ኃጢአት ሲፈጽም ይሖዋ ግለሰቡን ለመርዳትና ጉባኤውን ለመጠበቅ ምን ዝግጅት አድርጓል?

ያዕ 5:14, 15

በተጨማሪም ሥራ 20:28፤ ገላ 6:1⁠ን ተመልከት

ከባድ ኃጢአት የቤተሰባችንን አባላት አልፎም ጉባኤውን ሊነካ የሚችለው እንዴት ነው?

ዕብ 12:15, 16

በተጨማሪም ዘዳ 29:18⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢያሱ 7:1-13, 20-26—አካን ከባድ ኃጢአት በመፈጸሙና ኃጢአቱን ለመሸፈን በመሞከሩ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ላይ ጥፋት አምጥቷል

    • ዮናስ 1:1-16—ነቢዩ ዮናስ በይሖዋ ላይ በማመፁ መርከቡ ላይ አብረውት የነበሩትን ሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል

    • 1ቆሮ 5:1-7—ሐዋርያው ጳውሎስ በቆሮንቶስ ጉባኤ የተፈጸመንና መላውን ጉባኤ እየጎዳ የነበረን ከባድ ኃጢአት አጋልጧል

ተግሣጽን በመፍራት የሽማግሌዎችን እርዳታ ከመጠየቅ ወደኋላ ማለት የሌለብን ለምንድን ነው?

ቀደም ሲል በሠራነው ኃጢአት ነጋ ጠባ በጥፋተኝነት ስሜት ከመደቆስ ይልቅ አምላክ ይቅር እንዳለን አምነን መቀበል ያለብን ለምንድን ነው?

ይቅር ባይነት” የሚለውን ተመልከት

ከባድ ኃጢአት እንደተፈጸመ ካወቅን ኃጢአተኛው ጉዳዩን ለጉባኤ ሽማግሌዎች እንዲናገር ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?

ዘሌ 5:1

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘዳ 13:6-9፤ 21:18-20—በሙሴ ሕግ መሠረት አንድ ሰው ኃጢአት እንደተፈጸመ ካወቀ ግለሰቡ የቤተሰቡ አባል ወይም የቅርብ ጓደኛው ቢሆን እንኳ ሊያጋልጠው ይገባ ነበር