በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥበብ

ጥበብ

እውነተኛ ጥበብ ለማግኘት የግድ አስፈላጊ የሆነው ነገር ምንድን ነው?

እውነተኛ ጥበብ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

ጥበብ እንዲሰጠን ወደ አምላክ መጸለይ ተገቢ ነው?

ቆላ 1:9፤ ያዕ 1:5

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 1:8-12—ወጣቱ ንጉሥ ሰለሞን፣ የእስራኤልን ብሔር ጥሩ አድርጎ ለማስተዳደር የሚያስችል ጥበብ እንዲሰጠው ጸልዮአል፤ ይሖዋም በጠየቀው ነገር ስለተደሰተ ጥበብን ሰጥቶታል

    • ምሳሌ 2:1-5—ጥበብ፣ ማስተዋልና ጥልቅ ግንዛቤ ልንፈልገው ከሚገባ የተሸሸገ ሀብት ጋር ተመሳስለዋል፤ ይሖዋ ይህንን ውድ ሀብት ተግተው የሚፈልጉ ሰዎችን ይባርካቸዋል

ይሖዋ ጥበብ የሚሰጠን በማን በኩል እና በምን አማካኝነት ነው?

ኢሳ 11:2፤ 1ቆሮ 1:24, 30፤ 2:13 ኤፌ 1:17፤ ቆላ 2:2, 3

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ምሳሌ 8:1-3, 22-31—ጥበብ በሰውኛ ዘይቤ ተገልጻለች፤ ለጥበብ የተሰጠው መግለጫ የፍጥረታት በኩር የሆነውን የአምላክ ልጅ ያመለክታል

    • ማቴ 13:51-54—ከኢየሱስ አድማጮች ብዙዎቹ ኢየሱስ በእነሱ መካከል አድጎ እንዲህ ያለ ታላቅ ጥበብ ከየት ሊያገኝ እንደቻለ ግራ ገብቷቸዋል

የአምላካዊ ጥበብ አንዳንድ መገለጫዎች ምንድን ናቸው?

ጥበብ ለሕይወታችን መሪና ጠባቂ የሚሆንልን እንዴት ነው?

ከአምላክ የሚገኘው ጥበብ ምን ያህል ውድ ነው?

ምሳሌ 3:13, 14፤ 8:11

በተጨማሪም ኢዮብ 28:18⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 28:12, 15-19—ኢዮብ ሐዘን፣ ሥቃይና መከራ ውስጥ በነበረበት ጊዜም እንኳ መለኮታዊ ጥበብ ያለውን የላቀ ዋጋ በአድናቆት ተናግሯል

    • መዝ 19:7-9—ንጉሥ ዳዊት፣ የይሖዋ ሕግና ማሳሰቢያ ተሞክሮ የሌለውን እንኳ ጥበበኛ እንደሚያደርግ ገልጿል

አምላክን ከግምት የማያስገባው ዓለማዊ ጥበብ ለጉዳት የሚዳርገን እንዴት ነው?