ለዘላለም በደስታ መኖር የሚቻል ይመስልሃል?
መልስህ ምንድን ነው?
ይመስለኛል?
አይመስለኝም?
ወይስ ምናልባት?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
“ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።”—መዝሙር 37:29
ይህን ማወቅህ ለአንተ ምን ጥቅም አለው?
ከቤተሰቦችህና ከወዳጆችህ ጋር በደስታና በሰላም የምትኖርበት ጊዜ ይመጣል።—ኤርምያስ 29:11
ለአጭር ጊዜ ሳይሆን ለዘላለም በደስታ ትኖራለህ።—መዝሙር 22:26
መጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጠው ተስፋ ላይ እምነት መጣል እንችላለን?
አዎ! እንዲህ የምንለው ለምን እንደሆነ ለማወቅ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ በሚገኙት ሦስት ምዕራፎች ላይ የቀረበውን ማስረጃ ተመልከት። የምዕራፎቹ ርዕስ የሚከተለው ነው፦