በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ውይይት መጀመር

ምዕራፍ 1

ስለ ሰዎች ማሰብ

ስለ ሰዎች ማሰብ

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ፍቅር . . . የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም።”—1 ቆሮ. 13:4, 5

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ዮሐንስ 4:6-9ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1.   ሀ. ኢየሱስ ሴትየዋን ከማዋራቱ በፊት ስለ እሷ ምን የታዘበው ነገር አለ?

  2.  ለ. ኢየሱስ “እባክሽ፣ የምጠጣው ውኃ ስጪኝ” አላት። ይህን ማለቱ ውይይት ለመጀመር ውጤታማ እንደነበር ይሰማሃል? ለምን?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. የምናነጋግረውን ሰው ትኩረት የሚስብ ነገር ማንሳታችን፣ ጥሩ ውይይት ለማድረግ መንገድ ይከፍታል።

ኢየሱስን ምሰል

3. እንደሁኔታው ሁን። የግድ እኔ በተዘጋጀሁበት ርዕሰ ጉዳይ ካልተወያየሁ አትበል። በወቅቱ ሰዎች የሚያሳስባቸውን ጉዳይ አንስተህ ውይይት ጀምር። ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  1.   ሀ. ‘ዜና ላይ ምን እየተባለ ነው?’

  2.  ለ. ‘ጎረቤቶቼ፣ የሥራ ባልደረቦቼ ወይም አብረውኝ የሚማሩት ልጆች እያወሩበት ያለው ሰሞንኛ ጉዳይ ምንድን ነው?’

4. ጥሩ አድርገህ ታዘብ። ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  1.   ሀ. ‘ግለሰቡ ምን እያደረገ ነው? ስለ ምን እያሰበ ሊሆን ይችላል?’

  2.  ለ. ‘አለባበሱ፣ ውጫዊ ገጽታው ወይም ቤቱ፣ ስለሚያምንበት ነገር ወይም ስለ ባሕሉ ምን የሚጠቁመው ነገር አለ?’

  3.  ሐ. ‘ግለሰቡን አሁን ባነጋግረው ይመቸዋል?’

5. አዳምጥ።

  1.   ሀ. ብዙ አታውራ።

  2.  ለ. ግለሰቡም እንዲናገር ዕድል ስጠው። የሚቻል ከሆነ ጥያቄ ጠይቅ።