በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ውይይት መጀመር

ምዕራፍ 5

ዘዴኛነት

ዘዴኛነት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ንግግራችሁ ምንጊዜም . . . ለዛ ያለው ይሁን።”—ቆላ. 4:6

ጳውሎስ ምን አድርጓል?

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም የሐዋርያት ሥራ 17:22, 23ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1.   ሀ. ጳውሎስ በአቴንስ ከተማ ያለውን የሐሰት አምልኮ ሲያይ ምን ተሰማው?—የሐዋርያት ሥራ 17:16ን ተመልከት።

  2.  ለ. የአቴንስ ሰዎችን ከማውገዝ ይልቅ የሚያምኑበትን ነገር መሠረት በማድረግ ምሥራቹን በዘዴ የሰበከላቸው እንዴት ነው?

ከጳውሎስ ምን እንማራለን?

2. ምን እንደምንናገር እንዲሁም እንዴትና መቼ እንደምንናገር በጥንቃቄ ማሰባችን ሰሚ ጆሮ ለማግኘት ይረዳናል።

ጳውሎስን ምሰል

3. የምትጠቀምባቸውን ቃላት በጥንቃቄ ምረጥ። ለምሳሌ የክርስትናን እምነት የማይከተል ሰው ስታነጋግር፣ መጽሐፍ ቅዱስን በምታስተዋውቅበት ወይም ኢየሱስን በምትጠራበት መንገድ ላይ ለውጥ ማድረግ ሊያስፈልግህ ይችላል።

4. ለማረም አትቸኩል። ሐሳቡን በነፃነት እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ጋር የሚጋጭ ነገር ቢያነሳ እንኳ ‘ትክክል አይደለህም’ ለማለት አትቸኩል። (ያዕ. 1:19) አዳምጠው፤ አመለካከቱን መረዳት የምትችለው እንዲህ ካደረግክ ነው።—ምሳሌ 20:5

5. የሚቻል በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ሐሳቡን ተጋራ እንዲሁም አመስግነው። ግለሰቡ ሃይማኖቱ ትክክል እንደሆነ ከልቡ ያምን ይሆናል። በቅድሚያ በሚያስማሟችሁ ነገሮች ላይ ማተኮሩ የተሻለ ነው፤ ከዚያም ቀስ በቀስ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት እንዲገነዘብ እርዳው።