በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ውይይት መጀመር

ምዕራፍ 6

ድፍረት

ድፍረት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “የአምላክን ምሥራች ለእናንተ ለመንገር በአምላካችን እርዳታ እንደ ምንም ብለን ድፍረት አገኘን።”—1 ተሰ. 2:2

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ሉቃስ 19:1-7ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1.   ሀ. አንዳንድ ሰዎች ከዘኬዎስ ጋር መሆን የማይፈልጉት ለምን ሊሆን ይችላል?

  2.  ለ. ኢየሱስ ግን ለዚህ ሰው ምሥራቹን እንዲሰብክ ያነሳሳው ምንድን ነው?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. የመንግሥቱን መልእክት ሳናዳላ ለሁሉም ሰው ለመስበክ ድፍረት ያስፈልገናል።

ኢየሱስን ምሰል

3. የይሖዋን እርዳታ ፈልግ። ኢየሱስ ለመስበክ ኃይል ያገኘው ከአምላክ መንፈስ ነው፤ የአምላክ መንፈስ ለአንተም ኃይል ሊሰጥህ ይችላል። (ማቴ. 10:19, 20፤ ሉቃስ 4:18) ለሚያስፈሩህ ሰዎች ለመስበክ ድፍረት እንዲሰጥህ ይሖዋን ጠይቀው።—ሥራ 4:29

4. ከውጭ አይተህ አትፍረድ። አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ማነጋገር የሚያስፈራን በውጫዊ ገጽታቸው፣ በኑሮ ደረጃቸው፣ በአኗኗር ዘይቤያቸው ወይም በሃይማኖታቸው የተነሳ ሊሆን ይችላል። ይሁንና ይህን አስታውስ፦

  1.   ሀ. ይሖዋና ኢየሱስ የሰዎችን ልብ ማንበብ ይችላሉ፤ እኛ ግን አንችልም።

  2.  ለ. ‘የይሖዋ ምሕረት አይገባውም’ ልንለው የምንችለው ሰው የለም።

5. ድፍረትህ ዘዴኛነትና ጥንቃቄ የታከለበት ይሁን። (ማቴ. 10:16) አተካራ ውስጥ አትግባ። ግለሰቡ ለመስማት ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም ደህንነትህን የሚያሰጋ ነገር እንዳለ ከተሰማህ ውይይቱን በጨዋነት አቋርጥ።—ምሳሌ 17:14