በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ተመላልሶ መጠየቅ

ምዕራፍ 8

ትዕግሥት

ትዕግሥት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ፍቅር ታጋሽ . . . ነው።”—1 ቆሮ. 13:4

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ዮሐንስ 7:3-5ን እና 1 ቆሮንቶስ 15:3, 4, 7ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1.   ሀ. የኢየሱስ ወንድሞች መጀመሪያ ላይ ለመልእክቱ ምን ምላሽ ሰጥተው ነበር?

  2.  ለ. ኢየሱስ በወንድሙ በያዕቆብ ላይ ተስፋ እንዳልቆረጠ የሚያሳየው ምንድን ነው?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. አንዳንዶች ምሥራቹን ለመቀበል ከሌሎች ረዘም ያለ ጊዜ ስለሚወስድባቸው ታጋሽ መሆን ያስፈልገናል።

ኢየሱስን ምሰል

3. የተለየ አቀራረብ ሞክር። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ካቅማማ አትጫነው። የሚቻል ከሆነ፣ ቪዲዮዎች ወይም አንዳንድ ርዕሶች ተጠቅመህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ ምን እንደሚመስል እንዲሁም እሱን እንዴት እንደሚጠቅመው አስገንዝበው።

4. አታወዳድር። የእያንዳንዱ ሰው ሁኔታ ይለያያል። የቤተሰብህ አባል ወይም ተመላልሶ መጠየቅ የምታደርግለት ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመጀመር ካቅማማ ወይም አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መቀበል ከከበደው ምክንያቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስብ። በጣም የሚወደውን ሃይማኖታዊ ትምህርት መተው ከብዶት ይሆን? ዘመዶቹ ወይም ጎረቤቶቹ ጫና እያደረጉበት ነው? ስለተነጋገራችሁበት ነገር እንዲያስብበትና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ያለውን ጥቅም እንዲረዳ ጊዜ ስጠው።

5. ስለ ግለሰቡ ጸልይ። ምንጊዜም አዎንታዊና ዘዴኛ ለመሆን እንዲረዳህ ይሖዋን ጠይቀው። ግለሰቡ ፍላጎት ከሌለውና ውይይቱን ማቋረጥ የሚያስፈልግህ ከሆነ ይህን ማስተዋል እንድትችል ጸልይ።—1 ቆሮ. 9:26