በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ደቀ መዛሙርት ማድረግ

ምዕራፍ 11

በቀላሉ የሚገባ

በቀላሉ የሚገባ

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ከአንደበታችሁ የሚወጣው ቃል በቀላሉ የሚገባ [ይሁን]።”—1 ቆሮ. 14:9

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ማቴዎስ 6:25-27ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1.   ሀ. ኢየሱስ ይሖዋ የሚያደርግልንን እንክብካቤ በምሳሌ ያስረዳው እንዴት ነው?

  2.  ለ. ኢየሱስ ስለ ወፎች ብዙ ነገር ቢያውቅም በየትኛው ቀላል ነጥብ ላይ አተኩሯል? ይህስ ውጤታማ የሆነው ለምንድን ነው?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. ቀላል በሆነ መንገድ የምናስተምር ከሆነ ሰዎች ትምህርቱን ለማስታወስ አይቸገሩም፤ ልባቸውም ይነካል።

ኢየሱስን ምሰል

3. ብዙ አታውራ። ስለ አንድ ርዕስ የምታውቀውን ነገር ሁሉ ከማውራት ይልቅ ማጥኛ ጽሑፉ ውስጥ ባለው ሐሳብ ላይ አተኩር። የምታስጠናውን ሰው አንድ ጥያቄ ከጠየቅኸው በኋላ መልስ እስኪሰጥህ በትዕግሥት ጠብቀው። መልሱን ካላወቀው ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ ሐሳብ ከተናገረ፣ ተጨማሪ ጥያቄዎች ተጠቅመህ ጉዳዩን በደንብ እንዲያስብበት እርዳው። ዋናው ነጥብ ከገባው ወደ ቀጣዩ ነጥብ እለፍ።

4. አዳዲስ ትምህርቶችን ቀድሞ ከተማረው ነገር ጋር እንዲያዛምድ እርዳው። ለምሳሌ ስለ ትንሣኤ የምታጠኑበት ምዕራፍ ላይ ደርሳችኋል እንበል፤ የሞቱ ሰዎች ስለሚገኙበት ሁኔታ የተማረውን ነገር በአጭሩ በመከለስ መጀመር ትችላለህ።

5. ምሳሌዎችን በጥንቃቄ ምረጥ። አንድ ምሳሌ ከመጠቀምህ በፊት ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  1.   ሀ. ‘ምሳሌው ያልተወሳሰበ ነው?’

  2.  ለ. ‘የማስጠናው ሰው በቀላሉ ይረዳዋል?’

  3.  ሐ. ‘ምሳሌውን ብቻ ሳይሆን ዋናውን ነጥብም ማስታወስ ይችላል?’