በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ተጨማሪ መረጃ ሀ

ለማስተማር የምንጓጓቸው እውነቶች

ለማስተማር የምንጓጓቸው እውነቶች

ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች የእውነትን መልእክት ገና ሲሰሙት እንደሚያውቁት ኢየሱስ ተናግሯል። (ዮሐ. 10:4, 27) ስለዚህ ከሰዎች ጋር ስንነጋገር መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ልናካፍላቸው እንፈልጋለን። አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለማስተዋወቅ አጭር ጥያቄ መጠቀም ትችላለህ፤ ለምሳሌ “አምላክ በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን መከራ ሁሉ በቅርቡ የሚያስወግድ ይመስልሃል?” ወይም “አምላክ ስም እንዳለው ሰምተህ ታውቃለህ?” ብለህ መጠየቅ ትችላለህ። ከዚያም ለርዕሰ ጉዳዩ የሚስማማ ጥቅስ (ጥቅሶች) ተጠቅመህ ያንን እውነት አብራራ። መሠረታዊ የሆነ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንኳ የእውነት ዘር በሰውየው ልብ ውስጥ እንዲዘራ ሊያደርግ ይችላል! ይህን ዘር ደግሞ አምላክ ያሳድገዋል።—1 ቆሮ. 3:6, 7

 የወደፊቱ ጊዜ

  1. 1. ዛሬ በዓለም ላይ የሚታዩ ክስተቶችና የሰዎች ባሕርይ መበላሸት ለውጥ እየመጣ እንደሆነ ይጠቁማሉ።—ማቴ. 24:3, 7, 8፤ ሉቃስ 21:10, 11፤ 2 ጢሞ. 3:1-5

  2. 2. ምድር ፈጽሞ አትጠፋም።—መዝ. 104:5፤ መክ. 1:4

  3. 3. የተበላሸው የምድር ሥነ ምህዳር ይስተካከላል።—ኢሳ. 35:1, 2፤ ራእይ 11:18

  4. 4. ሁሉም ሰው ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ይሆናል።—ኢሳ. 33:24፤ 35:5, 6

  5. 5. በምድር ላይ ለዘላለም መኖር ትችላለህ።—መዝ. 37:29፤ ማቴ. 5:5

 ቤተሰብ

  1. 6. ባል “ራሱን እንደሚወድ ሁሉ ሚስቱንም [መውደድ]” አለበት።—ኤፌ. 5:33፤ ቆላ. 3:19

  2. 7. ሚስት ባሏን በጥልቅ ልታከብር ይገባል።—ኤፌ. 5:33፤ ቆላ. 3:18

  3. 8. ባልና ሚስት ለትዳራቸው ታማኝ መሆን አለባቸው።—ሚል. 2:16፤ ማቴ. 19:4-6, 9፤ ዕብ. 13:4

  4. 9. ወላጆቻቸውን የሚያከብሩና የሚታዘዙ ልጆች ይሳካላቸዋል።—ምሳሌ 1:8, 9፤ ኤፌ. 6:1-3

NASA, ESA and the Hubble Heritage Team (STScI/AURA)-ESA/Hubble Collaboration. Licensed under CC BY 4.0. Source.

 አምላክ

  1. 10. አምላክ ስም አለው።—መዝ. 83:18፤ ኤር. 10:10

  2. 11. አምላክ ሐሳቡን ገልጾልናል።—2 ጢሞ. 3:16, 17፤ 2 ጴጥ. 1:20, 21

  3. 12. አምላክ ፍትሐዊ ነው፤ ፈጽሞ አያዳላም።—ዘዳ. 10:17፤ ሥራ 10:34, 35

  4. 13. አምላክ ሊረዳን ይፈልጋል።—መዝ. 46:1፤ 145:18, 19

 ጸሎት

  1. 14. አምላክ ወደ እሱ እንድንጸልይ ይፈልጋል።—መዝ. 62:8፤ 65:2፤ 1 ጴጥ. 5:7

  2. 15. መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት መጸለይ እንዳለብን ያስተምረናል።—ማቴ. 6:7-13፤ ሉቃስ 11:1-4

  3. 16. አዘውትረን መጸለይ አለብን።—ማቴ. 7:7, 8፤ 1 ተሰ. 5:17

 ኢየሱስ

  1. 17. ኢየሱስ ታላቅ አስተማሪ ነው፤ ምክሩ መቼም መሬት ጠብ አይልም።—ማቴ. 6:14, 15, 34፤ 7:12

  2. 18. ኢየሱስ ዛሬ በዓለም ላይ ስለምናያቸው ክስተቶች አስቀድሞ ተናግሯል።—ማቴ. 24:3, 7, 8, 14፤ ሉቃስ 21:10, 11

  3. 19. ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው።—ማቴ. 16:16፤ ዮሐ. 3:16፤ 1 ዮሐ. 4:15

  4. 20. ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ አይደለም።—ዮሐ. 14:28፤ 1 ቆሮ. 11:3

Based on NASA/Visible Earth imagery

 የአምላክ መንግሥት

  1. 21. አምላክ በሰማይ መንግሥት አቋቁሟል።—ዳን. 2:44፤ 7:13, 14፤ ማቴ. 6:9, 10፤ ራእይ 11:15

  2. 22. የአምላክ መንግሥት የሰዎችን መንግሥታት አጥፍቶ በምትካቸው ይገዛል።—መዝ. 2:7-9፤ ዳን. 2:44

  3. 23. የሰው ልጆችን ችግሮች የሚፈታው የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው።—መዝ. 37:10, 11፤ 46:9፤ ኢሳ. 65:21-23

 መከራ

  1. 24. መከራ የሚያመጣብን አምላክ አይደለም።—ዘዳ. 32:4፤ ያዕ. 1:13

  2. 25. ይህን ዓለም የሚገዛው ሰይጣን ነው።—ሉቃስ 4:5, 6፤ 1 ዮሐ. 5:19

  3. 26. አምላክ ችግር ሲደርስብህ ያዝናል፤ ሊረዳህም ይፈልጋል።—መዝ. 34:17-19፤ ኢሳ. 41:10, 13

  4. 27. አምላክ በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን መከራ በቅርቡ ያስወግዳል።—ኢሳ. 65:17፤ ራእይ 21:3, 4

 ሞት

  1. 28. የሞቱ ሰዎች ምንም አያውቁም፤ እየተሠቃዩም አይደሉም።—መክ. 9:5፤ ዮሐ. 11:11-14

  2. 29. የሞቱ ሰዎች ሊረዱንም ሆነ ሊጎዱን አይችሉም።—መዝ. 146:4፤ መክ. 9:6, 10

  3. 30. በሞት ያጣናቸው ቤተሰቦቻችንና ወዳጆቻችን ከሞት ይነሳሉ።—ኢዮብ 14:13-15፤ ዮሐ. 5:28, 29፤ ሥራ 24:15

  4. 31. “ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም።”—ራእይ 21:3, 4፤ ኢሳ. 25:8

 ሃይማኖት

  1. 32. አምላክን የሚያስደስቱት ሁሉም ሃይማኖቶች አይደሉም።—ኤር. 7:11፤ ማቴ. 7:13, 14, 21-23

  2. 33. አምላክ ግብዝነትን ይጠላል።—ኢሳ. 29:13፤ ሚክ. 3:11፤ ማር. 7:6-8

  3. 34. ፍቅር የእውነተኛው ሃይማኖት መለያ ነው።—ሚክ. 4:3፤ ዮሐ. 13:34, 35