በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ተጨማሪ መረጃ ሐ

ለዘላለም በደስታ ኑር! ተጠቅመን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት—እንዴት?

ለዘላለም በደስታ ኑር! ተጠቅመን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት—እንዴት?

ለዘላለም በደስታ ኑር! የተዘጋጀው በጸሎት ብዙ ታስቦበትና ምርምር ተደርጎበት ነው። ጥናት ስትመራ ይህንን ጽሑፍ ጥሩ አድርገህ ለመጠቀም ከታች ያሉትን ሐሳቦች ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ።

ከጥናቱ በፊት

  1. 1. በደንብ ተዘጋጅ። የምታስጠናው ሰው የሚያስፈልገውን ነገር፣ ያለበትን ሁኔታና አመለካከቱን እያሰብክ ተዘጋጅ። ለመረዳት ወይም ተግባራዊ ለማድረግ ይቸገራል ብለህ የምታስባቸውን ነጥቦች ለመለየት ጥረት አድርግ። “ምርምር አድርግ” በሚለው ክፍል ሥር የተዘረዘሩት ነገሮች ተማሪውን ይጠቅሙት እንደሆነ አስብ፤ ያስፈልገዋል የምትለው ሐሳብ ካገኘህ በጥናቱ ላይ እንዴት እንደምትጠቀምበት ተዘጋጅ።

በጥናቱ ወቅት

  1. 2. የምታስጠናው ሰው ፈቃደኛ እስከሆነ ድረስ ስትጀምሩም ሆነ ስትደመድሙ ጸልዩ።

  2. 3. ብዙ አታውራ። ምዕራፉ ላይ ካለው ሐሳብ አትውጣ፤ ተማሪው ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።

  3. 4. ወደ አዲስ ክፍል ስትሸጋገሩ፣ “ፍሬ ሐሳብ” የሚለውን አንብቡ፤ በክፍሉ ሥር ከተዘረዘሩት ምዕራፎች አንዳንዶቹን ጠቀስ አድርገህ እለፍ።

  4. 5. በአንድ ክፍል ሥር ያሉትን ምዕራፎች አጥንታችሁ ስትጨርሱ ለክፍሉ የተዘጋጀውን ክለሳ ተጠቅመህ የተማራቸውን እውነቶች እንዲያስታውስ እርዳው።

  5. 6. እያንዳንዱን ምዕራፍ ስታጠኑ፦

    1. ሀ. በመግቢያው ላይ ያሉትን አንቀጾች አንብቡ።

    2. ለ. “አንብቡ” የተባለባቸውን ጥቅሶች ሁሉ አንብቡ።

    3. ሐ. ሌሎች ጥቅሶችንም እንደ አስፈላጊነቱ አንብቡ።

    4. መ. “ተመልከቱ” የተባለባቸውን ቪዲዮዎች ሁሉ ተመልከቱ (የሚቻል ከሆነ)።

    5. ሠ. ተማሪውን እያንዳንዱን ጥያቄ ጠይቀው።

    6. ረ. “ጠለቅ ያለ ጥናት” በሚለው ክፍል ሥር ያሉትን ሥዕሎች ተመልከቱ፤ ተማሪው ሐሳብ እንዲሰጥባቸው ጠይቀው።

    7. ሰ. የምታስጠናው ሰው መንፈሳዊ እድገቱን መከታተል እንዲችል “ግብ” የሚለውን ሣጥን ተጠቅመህ እርዳው። እዚያ ላይ የተጠቀሰውን ግብ እንዲያወጣ ወይም ሌላ የራሱን ግብ እንዲያስብ አሊያም ሁለቱንም እንዲያደርግ አበረታታው።

    8. ሸ. ተማሪው ምዕራፉን ሲዘጋጅ “ምርምር አድርግ” ከሚለው ክፍል ላይ የወደደው ርዕስ ወይም ቪዲዮ ካለ ጠይቀው።

    9. ቀ. አንድ ምዕራፍ በአንድ የጥናት ክፍለ ጊዜ ለመሸፈን ጥረት አድርጉ።

ከጥናቱ በኋላ

  1. 7. ስለምታስጠናው ሰው ማሰብህን ቀጥል። ይሖዋ፣ የሚያደርገውን እድገት እንዲባርክለት፣ ለአንተም እሱን የምትረዳበት ጥበብ እንዲሰጥህ ጸልይ።