በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዘሌዋውያን ምዕራፍ 25 ላይ የተገለጸው የኢዮቤልዩ ዓመት ለምን ነገር ምሳሌ  ነው?

የሙሴ ሕግ “በሰባተኛው ዓመት ግን ምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት ታድርግ” በማለት ያዝዝ ነበር። ይህን ዓመት በተመለከተ እስራኤላውያን የሚከተለው መመሪያ ተሰጥቷቸዋል:- “በዕርሻህ ላይ አትዝራ፤ ወይንህንም አትግረዝ። ሳይዘራ የበቀለውን አትጨደው፤ ካልተገረዘው የወይን ተክልህ ፍሬ አትሰብስብ። ምድሪቱ የአንድ ዓመት ዕረፍት ታድርግ።” (ዘሌዋውያን 25:4, 5) በመሆኑም በየሰባት ዓመቱ ምድሪቱ የሰንበት ዕረፍት ታደርግ ነበር። እንዲሁም በየ50 ዓመቱ ማለትም ከሰባተኛው የሰንበት ዓመት በኋላ ያለው ዓመት ኢዮቤልዩ ነበር። በዚህ ዓመት ምን ይደረጋል?

ይሖዋ በሙሴ በኩል እስራኤላውያንን እንዲህ ብሏቸው ነበር:- “አምሳኛውን ዓመት ቀድሱ፤ በምድሪቱ ሁሉ ላሉ ነዋሪዎች በሙሉ ነጻነት ዐውጁ፤ ይህም ኢዮቤልዩ ይሁንላችሁ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ ወደ ቤተ ሰቡ ርስት፣ ወደ ወገኑም ይመለስ። የአምሳኛው ዓመት ኢዮቤልዩ ይሁንላችሁ፤ አትዝሩ፤ ሳትዘሩት የበቀለውን አትጨዱ፤ ካልተገረዘውም የወይን ሐረግ ፍሬ አትሰብስቡ።” (ዘሌዋውያን 25:10, 11) በኢዮቤልዩ ዓመት ምድሪቱ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የሰንበት ዕረፍት ታደርጋለች። ነዋሪዎቿ ደግሞ ነጻነት ያገኛሉ። በባርነት ተሽጦ የነበረ ማንኛውም እስራኤላዊ ነጻ ይወጣል። አንድ እስራኤላዊ ከቤተሰቡ በውርስ የተላለፈለትን ርስት ለመሸጥ ተገድዶ ከነበረ በኢዮቤልዩ ዓመት ርስቱ ለቤተሰቡ ይመለሳል። በጥንቷ እስራኤል ኢዮቤልዩ ነገሮች ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው የሚመለሱበትና ነጻነት የሚገኝበት ዓመት ነበር። የኢዮቤልዩ ዓመት ለክርስቲያኖች ምን ትርጉም አለው?

የመጀመሪያው ሰው አዳም በአምላክ ላይ ማመጹ የሰው ዘር በኃጢአት ባርነት ሥር እንዲወድቅ አደረገ። አምላክ የሰውን ዘር ከኃጢአት ቀንበር ለማላቀቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት እንዲሆን ዝግጅት አደረገ። a (ማቴዎስ 20:28፤ ዮሐንስ 3:16፤ 1 ዮሐንስ 2:1, 2) ክርስቲያኖች ከኃጢአት ሕግ ነጻ የሚወጡት መቼ ነው? ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ለተቀቡት ክርስቲያኖች “የሕይወት መንፈስ ሕግ በክርስቶስ ኢየሱስ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶአችኋል” ብሏቸዋል። (ሮሜ 8:2) በሰማይ የመኖር ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ሲቀቡ ይህንን ነጻነት ይጎናጸፋሉ። ሥጋዊ አካል የለበሱና ፍጽምና የጎደላቸው ቢሆኑም አምላክ እንደ ጻድቃን በመቁጠር መንፈሳዊ ልጆቹ አድርጎ ተቀብሏቸዋል። (ሮሜ 3:24፤ 8:16, 17) በቡድን ደረጃ ለቅቡዓኑ የክርስቲያኖች ኢዮቤልዩ የጀመረው በ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ በጰንጠቆስጤ ዕለት ነው።

በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ለተዘረጋላቸው ‘ሌሎች በጎችስ’ ኢዮቤልዩ የሚጀምረው መቼ ነው? (ዮሐንስ 10:16) ለሌሎች በጎች የክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ነገሮች ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው የሚመለሱበትና ነጻነት የሚያገኙበት ጊዜ ይሆንላቸዋል። በዚህ የሺህ ዓመት ኢዮቤልዩ ወቅት ኢየሱስ በቤዛዊ መሥዋዕቱ የሚያምኑ የሰው ልጆች ከዚህ ዝግጅት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ ሲሆን ኃጢአት ያመጣቸውን ችግሮች ያስወግዳል። (ራእይ 21:3, 4) የክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ሲያበቃ የሰው ዘር ወደ ፍጽምና ደረጃ የሚደርስ ከመሆኑም በላይ ከአዳም ከወረሰው ኃጢአትና ሞት ሙሉ በሙሉ ነጻ ይወጣል። (ሮሜ 8:21) ይህ ከሆነ በኋላ የክርስቲያኖች ኢዮቤልዩ ያበቃል።

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

a ኢየሱስ ወደ ምድር የተላከው ‘ለምርኮኞች ነጻነት እንዲያውጅ’ ሲሆን እርሱም መንፈሳዊ ነጻነት አውጆአል።—ኢሳይያስ 61:1-7፤ ሉቃስ 4:16-21

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የሺህ ዓመቱ ኢዮቤልዩ ‘ለሌሎች በጎች’ ነገሮች ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው የሚመለሱበትና ነጻ የሚወጡበት ጊዜ ይሆናል