በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘የመጨረሻው ዘመን’ ምንድን ነው?

‘የመጨረሻው ዘመን’ ምንድን ነው?

‘የመጨረሻው ዘመን’ ምንድን ነው?

አንተም ሆንክ የምትወዳቸው ሰዎች ወደፊት ምን ሊያጋጥማችሁ እንደሚችል ያሳስብሃል? ብዙ ሰዎች የዓለም ሁኔታዎች ሕይወታቸውን እንዴት ሊነኩት እንደሚችሉ ለማወቅ ሲሉ የዜና ማሠራጫዎችን በትኩረት ይከታተላሉ። ይሁን እንጂ በመንፈስ አነሳሽነት ለተጻፈው የአምላክ ቃል ትኩረት መስጠት ትክክለኛ እውቀት እንዲኖረን ይረዳናል። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በአሁኑ ጊዜ እየተከሰቱ ስላሉት ብቻ ሳይሆን ወደፊት ስለሚሆኑት ነገሮችም ጭምር አስቀድሞ ተንብዮአል።

ለምሳሌ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ስለ አምላክ መንግሥት በስፋት ተናግሮ ነበር። (ሉቃስ 4:43) በዚያን ጊዜ ኢየሱስን ያዳምጡ የነበሩት ሰዎች ይህ አስደናቂ መንግሥት መቼ እንደሚመጣ ለማወቅ መፈለጋቸው ምንም አያስገርምም። ኢየሱስ ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ከመገደሉ ከሦስት ቀናት በፊት ደቀ መዛሙርቱ እንዲህ በማለት ጠይቀውት ነበር:- “[በመንግሥት ሥልጣን] የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክትስ ምንድን ነው?” (ማቴዎስ 24:3) ኢየሱስ፣ ይህ መንግሥት ምድርን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠርበትን ትክክለኛ ጊዜ የሚያውቀው ይሖዋ አምላክ ብቻ መሆኑን ነገራቸው። (ማቴዎስ 24:36፤ ማርቆስ 13:32) ይሁን እንጂ ክርስቶስ የመንግሥት ሥልጣን ይዞ መግዛት መጀመሩን የሚያመለክቱ አንዳንድ ለውጦች በምድር ላይ እንደሚከናወኑ ኢየሱስም ሆነ ሌሎች ቀደም ብለው በትንቢት ተናግረዋል።

በዚህ ሥርዓት ‘የመጨረሻ ዘመን’ ውስጥ እንደምንኖር የሚያሳዩ ጉልህ ማስረጃዎችን ከመመልከታችን በፊት በዓይን በማይታየው መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ የተከናወነውን ትልቅ ቦታ የሚሰጠው አንድ ክስተት እንመልከት። (2 ጢሞቴዎስ 3:1) ኢየሱስ ክርስቶስ በ1914 በሰማይ ንጉሥ ሆኗል። a (ዳንኤል 7:13, 14) የመንግሥቱን ሥልጣን እንደያዘ ወዲያውኑ እርምጃ ወስዷል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይነግረናል:- “በሰማይም ጦርነት ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም መልሰው ተዋጓቸው።” (ራእይ 12:7) “የመላእክት አለቃ የሆነው ሚካኤል” በሰማይ ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያመለክታል። b (ይሁዳ 9፤ 1 ተሰሎንቄ 4:16) ዘንዶው ደግሞ ሰይጣን ዲያብሎስ ነው። ታዲያ በተደረገው ውጊያ ሰይጣንም ሆነ አጋንንት ተብለው የሚጠሩት የእርሱ ተከታዮች የሆኑት ክፉ መላእክት ምን ደረሰባቸው? በጦርነቱ የተሸነፉ ሲሆን ከሰማይ ወደ ምድር “ተጣሉ።” (ራእይ 12:9) ይህም ‘ለሰማያት’ እና “በውስጣቸውም የምትኖሩ” ለተባሉት ታማኝ የአምላክ መንፈሳዊ ልጆች ደስታ አስገኝቷል። ይሁንና ሰዎች ይህን የመሰለውን ደስታ አላገኙም። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ “ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ፣ በታላቅ ቊጣ ተሞልቶ ወደ እናንተ ወርዶአል” በማለት ተናግሯል፤ ይህም በምድር ላይ ‘ወዮታ’ አስከትሏል።—ራእይ 12:12

ሰይጣን እጅግ በመቆጣት በምድር ባሉት ላይ ወዮታ ማለትም ሥቃይና መከራ አምጥቷል። ሆኖም ይህ ወዮታ ለአጭር ጊዜ ማለትም ‘ለጥቂት ዘመን’ የሚቆይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጊዜ ‘የመጨረሻው ዘመን’ በማለት ይጠራዋል። በቅርቡ ዲያብሎስ በምድር ላይ የሚያሳድረው ክፉ ተጽዕኖ ከናካቴው እንደሚወገድ ማወቃችን ያስደስተናል። ይሁን እንጂ በመጨረሻው ዘመን እንደምንኖር የሚያረጋግጥ ምን ማስረጃ አለ?

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

b ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ከገጽ 218-219 ተመልከት።

[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

COVER: Foreground: © Chris Stowers/​Panos Pictures; background: FAROOQ NAEEM/​AFP/​Getty Images