በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአምላክ ስም በሩሲያ ሙዚቃ ውስጥ

የአምላክ ስም በሩሲያ ሙዚቃ ውስጥ

የአምላክ ስም በሩሲያ ሙዚቃ ውስጥ

1877 ሞደስት ሙሶርግስኪ የተባለው ታዋቂ የሩሲያ የሙዚቃ ደራሲ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሱ አገሮች በተከናወኑ ታሪኮች ላይ ተመሥርቶ በኅብረት የሚዘመር ሙዚቃ አሳተመ። ሙሶርግስኪ ለአንድ ጓደኛው እንዲህ ብሎ ጽፎ ነበር:- “ጂሰስ ናቪነስ [ኢያሱ] የተባለ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ሙዚቃ ጽፌያለሁ፤ ይህን ሙዚቃ ያዘጋጀሁት ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመሥርቼ ሲሆን ናቪነስ [ማለትም ኢያሱ] በከነዓን ድል እየተቀዳጀ ያደረጋቸውን ጉዞዎች ሳይቀር አስፍሬያለሁ።” ሙሶርግስኪ “የሰናክሬብ መጥፋት” የሚለውን ጨምሮ በሌሎች የሙዚቃ ድርሰቶቹ ላይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦችንና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሰዎችን ተጠቅሟል።

የሚገርመው ነገር ሙሶርግስኪ “ጂሰስ ናቪነስ” በተባለውም ሆነ በ1874 ባሳተመው “የሰናክሬብ መጥፋት” በተሰኘው የሙዚቃ ድርሰቱ ላይ በሩሲያኛ አጠራር የአምላክን ስም ተጠቅሟል፤ ይህ ስም በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ יהוה [የሐወሐ] በሚሉት አራት ተነባቢ ፊደላት የተጻፈ ሲሆን ወደ 7,000 ጊዜ ያህል ይገኛል።

ከሙሶርግስኪ የድርሰት ሥራዎች እንደምንረዳው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ይሖዋ የሚለው የአምላክ ስም ከ20ኛው ምዕተ ዓመት መባቻ አስቀድሞ በሩስያ ማኅበረሰብ ዘንድ በስፋት ይታወቅ ነበር። ይሖዋ ራሱ ለሙሴ “ስሜም ለዘለዓለም ይኸው ነው፤ ወደፊት በተከታታይ በሚነሣው ትውልድ ሁሉ የምታሰበው በዚህ ስም ነው” በማለቱ ይህ መሆኑ ተገቢ ነው።—ዘፀአት 3:15

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በጽሑፍ የሰፈረው የሙሶርግስኪ ሙዚቃ የተቀመጠበት የሴንት ፒተርስበርግ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በ1913

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

Sheet music: The Scientific Music Library of the Saint-Petersburg State Conservatory named after N.A. Rimsky-Korsakov; street scene: National Library of Russia, St. Petersburg