በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጴጥሮስ ኢየሱስን ስለመካዱ የሚናገረው ታሪክ

ጴጥሮስ ኢየሱስን ስለመካዱ የሚናገረው ታሪክ

ለወጣት አንባቢያን

ጴጥሮስ ኢየሱስን ስለመካዱ የሚናገረው ታሪክ

መመሪያ:- ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳልና ሌላው ቀርቶ ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማት ሞክር። እንዲሁም የባለ ታሪኮቹን ስሜት ለመረዳት ጥረት አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ማቴዎስ 26:31-35, 69-75ን አንብብ።

በወቅቱ በቦታው ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል?

․․․․․

ጴጥሮስን ያነጋገሩት ሰዎች ወዳጃዊ በሆነ መንገድ የቀረቡት ይመስልሃል? የማወቅ ጉጉትስ ነበራቸው? በቁጣ የተሞሉ ነበሩ ወይስ ሌላ ዓይነት ስሜት ነበራቸው?

․․․․․

ጴጥሮስ ጥያቄ ሲቀርብለት ምን የተሰማው ይመስልሃል?

․․․․․

ጴጥሮስ ኢየሱስን የካደው ለምንድን ነው? ፍቅር ስላልነበረው ነው ወይስ በሌላ ምክንያት?

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።ሉቃስ 22:31-34፤ ማቴዎስ 26:55-58 እና ዮሐንስ 21:9-17ን አንብብ።

ከልክ በላይ በራስ መተማመን ጴጥሮስ ስህተት እንዲፈጽም የበኩሉን ድርሻ ያበረከተው እንዴት ነው?

․․․․․

ኢየሱስ፣ ጴጥሮስ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እንደሚሰናከል ቢያውቅም በእሱ ላይ የመተማመን ስሜት እንዳለው ያሳየው እንዴት ነበር?

․․․․․

ጴጥሮስ ኢየሱስን ቢክደውም እንኳ ከሌሎቹ ደቀ መዛሙርት የበለጠ ድፍረት ያሳየው በምን መንገድ ነው?

․․․․․

ኢየሱስ ጴጥሮስን ይቅር እንዳለው ያሳየው እንዴት ነበር?

․․․․․

ኢየሱስ ጴጥሮስን “ትወደኛለህን?” በማለት ሦስት ጊዜ የጠየቀው ለምን ይመስልሃል?

․․․․․

ጴጥሮስ ከኢየሱስ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ምን የተሰማው ይመስልሃል? ለምንስ?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት በጥሩ መንገድ ተጠቀምበት። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ:-

ሰውን ስለ መፍራት።

․․․․․

ደቀ መዛሙርቱ ቢሳሳቱም እንኳ ኢየሱስ ለእነሱ ስለነበረው ርኅራኄ።

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ አንተን በጣም የነካህ የትኛው ሁኔታ ነው? ለምን?

․․․․․