በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገኘው በርሜል ውኃ የመያዝ አቅሙ ምን ያህል ነበር?

አንደኛ ነገሥት 7:26 (የ1954 ትርጉም) በርሜሉ ‘ሁለት ሺህ የባዶስ መስፈሪያ’ እንደሚይዝ ሲናገር 2 ዜና መዋዕል 4:5 ላይ የሰፈረው ተመሳሳይ ዘገባ ደግሞ “ሦስት ሺህ የባዶስ መስፈሪያ” እንደሚይዝ ይናገራል። አንዳንዶች እንዲህ ያለው የቁጥር ልዩነት የተፈጠረው ሁለተኛ ዜና መዋዕልን የገለበጠው ሰው በመሳሳቱ ነው ብለው ይናገራሉ።

ይሁን እንጂ የአዲስ ዓለም ትርጉም ሁለቱም ጥቅሶች ትክክል መሆናቸውን እንድንረዳ ያስችለናል። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በ1 ነገሥት 7:26 ላይ በርሜሉ “ሁለት ሺህ የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበርበማለት ሲናገር 2 ዜና መዋዕል 4:5 ደግሞ “ሦስት ሺህ የባዶስ መስፈሪያ መያዝ ይችል ነበርይላል። ስለዚህ 2 ዜና መዋዕል 4:5 የሚናገረው ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገኘው በርሜል ያለውን የመያዝ አቅም ሲሆን 1 ነገሥት 7:26 ግን አብዛኛውን ጊዜ በበርሜሉ ውስጥ የሚጨመረውን የውኃ መጠን የሚያመለክት ነው። በሌላ አባባል በርሜሉ ከአፍ እስከ ገደፉ ግጥም ተደርጎ አይሞላም ነበር ማለት ነው። ከዚህ ይልቅ አብዛኛውን ጊዜ ውኃ የሚሞላበት፣ የበርሜሉ ሁለት ሦስተኛ ክፍል ብቻ ይመስላል።

ኢየሱስና ጴጥሮስ ለቤተ መቅደሱ ግብር አንድ ሳንቲም ብቻ የከፈሉት ለምንድን ነው?

በኢየሱስ ዘመን ከ20 ዓመት በላይ የሆናቸው ወንድ አይሁዳውያን በሙሉ ለዓመታዊው የቤተ መቅደስ ግብር ሁለት ዲናር ወይም አንድ ዳይድራክማ የመክፈል ግዴታ ነበረባቸው። ይህም ለሁለት ቀን ሥራ ከሚከፈል ደሞዝ ጋር ይመጣጠናል። ኢየሱስ ግብር ከመክፈል ጋር የተያያዘ ጥያቄ በተነሳ ጊዜ፣ ጴጥሮስን “ሄደህ መንጠቆህን ወደ ባሕር ጣል፤ መጀመሪያ የምትይዘውን ዓሣ አፉን ስትከፍት የምታገኘውን አንድ እስታቴር በእኔና በአንተ ስም ክፈል” በማለት አዘዘው።—ማቴዎስ 17:24-27

ብዙ ምሑራን እዚህ ጥቅስ ላይ የተጠቀሰው እስታቴር፣ ቴትራድራክማ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ይህ ሳንቲም ደግሞ የአራት ዲናር ያህል ዋጋ ያለው ሲሆን ለሁለት ሰዎች የቤተ መቅደስ ግብር መክፈል ይችላል። በወቅቱ ከዳይድራክማ ይልቅ በጣም የተለመደውና እንደ ልብ የሚገኘው ቴትራድራክማ ነበር። ዘ ኒው ባይብል ዲክሽነሪ “አይሁዳውያን ብዙውን ጊዜ ጥንድ ሆነው የቤተ መቅደሱን ግብር የመክፈል ልማድ የነበራቸው ይመስላል” በማለት ሐሳብ ሰጥቷል።

በተጨማሪም ብቻውን ግብር መክፈል የሚፈልግ ሰው ድፍን ሳንቲም ይዞ ከሄደ ሳንቲሙን ለመዘርዘር የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ወጪ ራሱ መክፈል ይኖርበታል። ይህ ክፍያ ደግሞ እስከ ስምንት በመቶ ሊደርስ ይችላል። ሁለት ሰዎች አንድ ላይ የሚከፍሉ ከሆነ ግን እንዲህ ካለው ተጨማሪ ወጪ ይድናሉ። ይህ ጥቂት ዝርዝር ሐሳብ የማቴዎስ ዘገባ በኢየሱስ ዘመን ከነበረው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጋር እንደሚስማማ ያሳያል።

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ቴትራድራክማ ጎላ ተደርጎ ሲታይ