በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምድርን ከጥፋት ሊታደጋት የሚችለው አምላክ ብቻ ነው

ምድርን ከጥፋት ሊታደጋት የሚችለው አምላክ ብቻ ነው

ምድርን ከጥፋት ሊታደጋት የሚችለው አምላክ ብቻ ነው

“ሰማያዊና ነጭ ቀለም ያለው አንጸባራቂ ፈርጥ።” የጠፈር ተመራማሪ የሆኑት ኤድገር ሚቼል፣ ምድርን በጨለማ ከተዋጠው ሕዋ ጋር በማነጻጸር የገለጿት በዚህ መንገድ ነበር።

አምላክ ምድር ለሰው ልጆች ምቹ መኖሪያ እንድትሆን ብዙ ነገሮችን አዘጋጅቷል። የአምላክ የፍጥረት ሥራ መላእክት በደስታ “እልል” እንዲሉ ገፋፍቷቸዋል። (ኢዮብ 38:7) እኛም በዚህች ፕላኔት ላይ ያሉትን አስደናቂ ነገሮች መመርመራችን በአድናቆት እንድንዋጥ ያደርገናል። ውስብስብ የሆነው የምድር ሥነ ምህዳር፣ ሕይወት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ለምሳሌ ያህል፣ አረንጓዴ ተክሎች ፀሐይን፣ ካርቦን ዳይኦክሳይድንና ውኃን ተጠቅመው ምግብ ያዘጋጃሉ። ይህ ሂደት ለሕልውናችን በጣም አስፈላጊ የሆነውን ኦክሲጅንን ያስገኝልናል።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ለሰው ልጅ ምድርን የመንከባከብ ኃላፊነት እንደሰጠው ይናገራል። (ዘፍጥረት 1:28፤ 2:15) ይሁን እንጂ የምድር ሥነ ምህዳር ተጠብቆ እንዲኖር ከተፈለገ የሰው ልጅ ትክክለኛ የሆነ አመለካከት ሊኖረው ይገባል። እንዲያውም ለሚኖርበት ምድር ፍቅር ማዳበር አለበት። የምድርን ውበት ጠብቆ የማቆየት ፍላጎት ሊኖረውም ይገባል። ይሁን እንጂ የሰው ልጅ የመምረጥ ነፃነት ስለተሰጠው የምድርን የተፈጥሮ ሀብት ሊበዘብዝና አላግባብ ሊጠቀምበት ይችላል። ደግሞም ያደረገው ይህንኑ ነው። የሰው ልጅ ግድ የለሽነትና ስግብግብነት በምድር ላይ ይህ ነው የማይባል ችግር አስከትሏል።

ከእነዚህ ችግሮች መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፦ (1) የደን መጨፍጨፍ የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን እንዲጨምር ያደረገ ሲሆን ይህ ደግሞ የምድርን የአየር ንብረት አዛብቶታል። (2) የሰው ልጆች፣ ተባይ ማጥፊያ መድኃኒቶችን ከልክ በላይ መጠቀማቸው ተክሎችን ማዳቀልን ጨምሮ ለምድር ሥነ ምህዳር አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን የሚያከናውኑትን ትናንሽ ነፍሳት እያጠፋቸው ይገኛል። (3) ዓሦችን ከመጠን በላይ ማጥመድ እንዲሁም የባሕርና የወንዝ መበከል የዓሦች ቁጥር እንዲመናመን አድርጓል። (4) የሰው ልጅ በስግብግብነት የምድርን የተፈጥሮ ሀብት ከልክ በላይ መጠቀሙ ለመጪዎቹ ትውልዶች ሊውል የሚችለውን ሀብት እያሟጠጠው ከመሆኑም ሌላ የምድር ሙቀት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሎ ይታመናል። አንዳንድ የአካባቢ ጥበቃ ባለሞያዎች በአርክቲክና በአንታርክቲካ ያሉ ግግር በረዶዎች መጠናቸው እየቀነሰ መሄዱና የበረዶ ዐለቶች መሰባበራቸው የምድር ሙቀት እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ ማስረጃ እንደሆነ ይናገራሉ።

አንዳንድ ሰዎች፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መሄዳቸው የሰው ልጅ ምድርን በማበላሸቱ የዘራውን እያጨደ ነው ብለው እንዲያምኑ አድርጓቸዋል። አምላክ በምድር ላይ በነፃ እንድንኖር ፈቅዶልናል። የሰው ልጅ በምድር ላይ ለመኖር ምንም ክፍያ አይጠየቅም። (ዘፍጥረት 1:26-29) ይሁንና በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ከሚታዩት ሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው አብዛኞቹ ሰዎች ውብ መኖሪያቸውን ለመንከባከብ ምንም ፍላጎት የላቸውም። ከዚህ ይልቅ የሰው ልጅ የራስ ወዳድነት ፍላጎቱን ለማርካት ሲሯሯጥ ይታያል። ሰዎች በነፃ እንዲኖሩባት የተሰጠቻቸውን ምድር በአግባቡ ከመያዝ ይልቅ በራእይ 11:18 ላይ አስቀድሞ እንደተነገረው “ምድርን እያጠፉ” ይገኛሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት እንደሚያሳየው ለሕይወት በጣም አስፈላጊ የሆነውን የምድር ሥነ ምህዳር የፈጠረው ሁሉን ቻይ አምላክ ይሖዋ፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ክፉ ሰዎችን የሚያጠፋበት ጊዜ ቀርቧል። (ሶፎንያስ 1:14፤ ራእይ 19:11-15) ሰዎች ምድርን ልታንሰራራ በማትችልበት መንገድ ከማበላሸታቸው በፊት በቅርቡ አምላክ እርምጃ ይወስዳል። * (ማቴዎስ 24:44) በእርግጥም ምድርን ከጥፋት ሊታደጋት የሚችለው አምላክ ብቻ ነው።

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.7 የጊዜውን አጣዳፊነት በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ነቅተህ ጠብቅ! የተባለውን ብሮሹር ተመልከት።