በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አንድ ወጣት ያሳየው ድፍረት

አንድ ወጣት ያሳየው ድፍረት

ለወጣት አንባቢያን

አንድ ወጣት ያሳየው ድፍረት

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—1 ሳሙኤል 17:1-11, 26, 32-51ን አንብብ።

የጎልያድ ቁመና እንዲሁም ድምፁ ምን ዓይነት ሊሆን እንደሚችል ግለጽ።

․․․․․

ዳዊት በእስራኤላውያን ጦር ሠራዊት ውስጥ የነበረ ባይሆንም እንኳ ከጎልያድ ጋር በሚደረገው ጦርነት ውስጥ እንዲገባ ያነሳሳው ምን ነበር? (ቁጥር 26⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

ዳዊት፣ ይሖዋ እንደሚረዳው እርግጠኛ እንዲሆን ያደረጉት ምክንያቶች ምንድን ናቸው? (ከ34-37 ያሉትን ቁጥሮች በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ለምርምር የሚረዱ ሌሎች ጽሑፎችን በመጠቀም የሚከተሉትን ለመመለስ ሞክር፦

(1) የጎልያድ ቁመት። (1 ሳሙኤል 17:4)

ከዘጠኝ ጫማ በላይ = ․․․․․

(2) ጎልያድ የለበሰው ጥሩር ክብደት። (1 ሳሙኤል 17:5)

5,000 ሰቅል ናስ = ․․․․․

(3) የጎልያድ የጦሩ ብረት ክብደት። (1 ሳሙኤል 17:7)

600 ሰቅል ብረት = ․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ስለ ድፍረት።

․․․․․

በራስህ ጥንካሬ ከመመካት ይልቅ በይሖዋ ስለ መታመን።

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር።

እንደ ጎልያድ ያለ ምን አስቸጋሪ እንቅፋት ገጥሞሃል?

․․․․․

ይሖዋ አይተወኝም ብለህ እንድታምን ያደረጉህ (የአንተም ሆነ የሌሎች ሰዎች) ተሞክሮዎች አሉ?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․