በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ሰይጣን ከሰማይ የተባረረው መቼ ነው?—ራእይ 12:1-9

የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው የራእይ መጽሐፍ ሰይጣን ከሰማይ የተባረረበትን ጊዜ ለይቶ ባይናገርም መቼ እንደተባረረ ለመገመት የሚያስችሉንን ተከታትለው የተፈጸሙ ክንውኖች ይጠቅሳል። የመሲሐዊው መንግሥት መወለድ ከእነዚህ ክንውኖች መካከል የመጀመሪያው ነው። ከዚያ ቀጥሎ ‘በሰማይ ጦርነት ተነሳ’፤ በኋላም ሰይጣን በጦርነቱ ድል ተደርጎ ከሰማይ ተባረረ።

ቅዱሳን መጻሕፍት “የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት” ያበቁትና መንግሥቱ የተቋቋመው በ1914 መሆኑን በግልጽ ያሳያሉ። * (ሉቃስ 21:24) ይሁንና ሰይጣን ከሰማይ እንዲባረር ምክንያት የሆነው ጦርነት የተነሳው መንግሥቱ ከተቋቋመ ምን ያህል ጊዜ ቆይቶ ነው?

ራእይ 12:4 እንዲህ ይላል፦ “ዘንዶውም [ሰይጣን] በምትወልድበት ጊዜ ልጇን ለመዋጥ ፈልጎ ልትወልድ በተቃረበችው ሴት ፊት ቆሞ ይጠብቅ ነበር።” ይህ ደግሞ ሰይጣን አዲስ የተወለደውን መንግሥት በተቻለ መጠን እንደተቋቋመ ለማጥፋት መፈለጉን ያሳያል። ይሖዋ ጣልቃ በመግባቱ ሰይጣን ክፉ ዓላማውን መፈጸም አልቻለም፤ ሆኖም አዲስ በተወለደው መንግሥት ላይ ጉዳት ለማድረስ ቆርጦ የተነሳ ከመሆኑም በላይ ይህን ዓላማውን ለማሳካት የማያቋርጥ ጥረት አድርጓል። “ሚካኤልና መላእክቱ” በመንግሥቱ ላይ አንዳች ጉዳት እንዳይደርስ ‘ዘንዶውንና መላእክቱን’ ከሰማይ ለማስወገድ ሳይዘገዩ እርምጃ የወሰዱት ለዚህ ነው። ይህ ደግሞ ሰይጣን በጦርነቱ የተሸነፈውና ከሰማይ የተባረረው መንግሥቱ ከተወለደበት ከ1914 ብዙም ሳይቆይ እንደሆነ ይጠቁማል።

ሌላው ልንመለከተው የሚገባን ነገር ደግሞ የቅቡዓን ክርስቲያኖችን ትንሣኤ ነው፤ ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚጠቁሙት የቅቡዓኑ ትንሣኤ የጀመረው የአምላክ መንግሥት ከተቋቋመ ብዙም ሳይቆይ ነው። * (ራእይ 20:6) ኢየሱስ ከዘንዶውና ከመላእክቱ ጋር ሲዋጋ፣ የክርስቶስ ቅቡዓን ወንድሞች በጦርነቱ እንደተካፈሉ ስላልተጠቀሰ የክርስቶስ ወንድሞች ትንሣኤ በጀመረበት ጊዜ በሰማይ የተደረገው ጦርነት አብቅቶ እንዲሁም ሰይጣንና አጋንንቱም ከሰማይ ተባረው መሆን አለበት።

ከዚህ ለመመልከት እንደሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰይጣንና አጋንንቱ ከሰማይ መቼ እንደተባረሩ ትክክለኛውን ጊዜ ለይቶ አይናገርም። ሆኖም ይህ ሁኔታ የተከሰተው በ1914 ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ ንጉሥ ሆኖ ከተሾመ ብዙም ሳይቆይ እንደሆነ ግልጽ ነው።

[የግርጌ ማስታወሻዎች]