በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

2. አስተሳሰብህን ሰፋ አድርገህ አንብበው

2. አስተሳሰብህን ሰፋ አድርገህ አንብበው

መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ምን ማድረግ ትችላለህ?

2. አስተሳሰብህን ሰፋ አድርገህ አንብበው

አንድ ወዳጅህ ስለማታውቀው ሰው መጥፎ ነገር ነግሮህ ያውቃል? በኋላ ላይ ከዚህ ሰው ጋር የመተዋወቅ አጋጣሚ ስታገኝ ወዳጅህ የነገረህ ነገር የግለሰቡን ችሎታዎችና ጥሩ ባሕርያት እንዳትመለከት አድርጎህ ነበር? መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተም ተመሳሳይ ነገር ሊያጋጥም ይችላል።

ሐዋርያው ጳውሎስ፣ መጽሐፍ ቅዱስን የምናነበው አስተሳሰባችንን ጠባብ አድርገን ከሆነ ምን ሊከሰት እንደሚችል ተናግሯል። ጳውሎስ በዘመኑ የነበሩትን አንዳንድ አይሁዶች አስመልክቶ ሲናገር “ለአምላክ ቅንዓት እንዳላቸው እመሠክርላቸዋለሁ” ብሏል፤ ይሁን እንጂ ቅንዓታቸው “በትክክለኛ እውቀት ላይ የተመሠረተ [አይደለም]” ሲል ተናግሯል።—ሮም 10:2

የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን የሚያሳዩ ግልጽ ማስረጃዎችን የያዙ ቢሆንም በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት አንዳንድ አይሁዶች ይህን እውነት ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም። የናዝሬቱ ኢየሱስ በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የተገለጹትን መሲሑ እንዲያሟላቸው የሚጠበቁበትን ነገሮች በሙሉ ያሟላ ሲሆን ስለ እሱ የተነገሩትን ትንቢቶችም አንድም ሳይቀር ፈጽሟል። ይሁንና በዘመኑ የነበሩት በርካታ አይሁዳውያን፣ ቀደም ሲል የነበራቸውን አመለካከት ለመለወጥ ፈቃደኛ አለመሆናቸው የአምላክን ቃል እንዳይረዱ አግዷቸዋል።

ታዲያ እኛ ከዚህ ዘገባ ምን እንማራለን? መጽሐፍ ቅዱስን አስተሳሰባችንን ሰፋ አድርገን ማንበባችን አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ቀደም ሲል አእምሯችን ውስጥ ያስገባነው የተሳሳተ አመለካከት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዳንረዳ እንቅፋት ሊሆንብን ይችላል።

በሰሜን ካሮላይና፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ጥናት ያካሄዱ አንድ ፕሮፌሰር የተናገሩትን ነገር እንደ ምሳሌ እንውሰድ፦ “[መጽሐፍ ቅዱስ] የሰዎች መጽሐፍ ሲሆን በውስጡ የያዘውም ሰብዓዊ አስተሳሰብን ነው፤ አብዛኞቹ ሐሳቦች አንዳቸው ከሌላው የማይስማሙ ከመሆናቸውም ሌላ አንዳቸውም ቢሆኑ እንዴት መኖር እንዳለብን የሚገልጽ ትክክለኛ መመሪያ አይሰጡም።” አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነበው “የሰዎች መጽሐፍ” አንደሆነ አድርጎ እያሰበ ከሆነ ለእሱ የማይስማሙትን መመሪያዎች ወይም መሠረታዊ ሥርዓቶች ገሸሽ ለማድረግ አይገፋፋም?

ከዚህ በተቃራኒ መጽሐፍ ቅዱስ፣ በውስጡ የያዘውን ሐሳብ በትጋት እንድናጠና ያበረታታናል። በጳውሎስ ዘመን የነበሩትን የቤርያ ሰዎች በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “የሰሙት ነገር ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ በየዕለቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ በመመርመር ቃሉን በታላቅ ጉጉት ተቀብለዋል።” (የሐዋርያት ሥራ 17:11) እንደ ቤርያ ሰዎች ሁሉ አንተም በአእምሮህ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም ዓይነት የተሳሳተ አስተሳሰብ በማስወገድ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ይኖርብህ ይሆናል። አምላክ ሊያስተላልፍ የፈለገውን አስደሳች መልእክት ለመረዳት ጉጉት በማሳደር አስተሳሰብህን ሰፋ አድርገህ መጽሐፍ ቅዱስን አንብብ።