በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘የተወሰነው ጊዜ’ ቀርቧል

‘የተወሰነው ጊዜ’ ቀርቧል

‘የተወሰነው ጊዜ’ ቀርቧል

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ልክ እንደ ነቢዩ ዕንባቆም መከራና ሥቃይ የሚጠፋበትን ጊዜ ለማየት ይናፍቁ ነበር። የአምላክ መንግሥት በምድር ላይ ያሉትን ችግሮች እንደሚያስተካክል ሲማሩ ኢየሱስን “እስቲ ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የመገኘትህና የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ምልክትስ ምንድን ነው?” በማለት ጠይቀውት ነበር። (ማቴዎስ 24:3) በዚህ ጊዜ ኢየሱስ መንግሥቱ ምድርን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው መቼ እንደሆነ በትክክል የሚያውቀው ይሖዋ አምላክ ብቻ እንደሆነ ገለጸላቸው። (ማቴዎስ 24:36፤ ማርቆስ 13:32) ይሁን እንጂ ኢየሱስም ሆነ ሌሎች ሰዎች ጊዜው መቅረቡን የሚጠቁሙ ክስተቶች እንደሚፈጸሙ ትንቢት ተናግረዋል።— በስተቀኝ ያለውን ሣጥን ተመልከት።

በዛሬው ጊዜ እነዚህ ነገሮች በስፋት እየተፈጸሙ ነው ቢባል አትስማማም? በተጨማሪም ኢየሱስ በምድር ዙሪያ የማስተማር ሥራ እንደሚካሄድ ትንቢት ተናግሮ ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለሕዝቦች ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።”—ማቴዎስ 24:14

በዛሬው ጊዜ ይህ ሥራ ልክ ኢየሱስ እንዳለው በመከናወን ላይ ይገኛል። ሥራውን የሚያከናውኑት የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው። ከሰባት ሚሊዮን የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች 236 በሚያህሉ አገሮች ይህ መንግሥት ወደፊት የሚያከናውነውን ነገር ለሰዎች እየተናገሩ ነው፤ እንዲሁም መከራንና ሥቃይን የሚያስወግደው አምላክ ካወጣቸው የጽድቅ መሥፈርቶች ጋር የሚስማማ ሕይወት መምራት እንዲችሉ ሰዎችን እየረዱ ነው። አንተም ስለ አምላክ መንግሥት መማርህን ከቀጠልክ መከራ በማይኖርበት ዓለም ውስጥ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ይኖርሃል።

[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

 ስለ መጨረሻዎቹ ቀኖች የሚናገሩ ጥቅሶች

ማቴዎስ 24:6, 7፤ ራእይ 6:4

• ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ጦርነት

ማቴዎስ 24:7፤ ማርቆስ 13:8

• ታላላቅ የምድር ነውጦች

• የምግብ እጥረት

ሉቃስ 21:11፤ ራእይ 6:8

• ቸነፈር

ማቴዎስ 24:12

• እየበዛ የሚሄድ ክፋት

• የፍቅር መቀዝቀዝ

ራእይ 11:18

• ሰዎች ምድርን ማበላሸታቸው

2 ጢሞቴዎስ 3:2

• ፍቅረ ንዋይ

• ልጆች ለወላጆች አለመታዘዛቸው

• ሰዎች ከመጠን በላይ ራሳቸውን መውደዳቸው

2 ጢሞቴዎስ 3:3

• ተፈጥሯዊ ፍቅር መጥፋቱ

• ሰዎች ለመስማማት ፈቃደኞች አለመሆናቸው

• በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ራሳቸውን መግዛት አለመቻላቸው

• ሰዎች ጥሩ የሆነውን ነገር አለመውደዳቸው

2 ጢሞቴዎስ 3:4

• ሰዎች ከአምላክ ይልቅ ደስታን መውደዳቸው

2 ጢሞቴዎስ 3:5

• ግብዝ የሆኑ ብዙ ሰዎች ክርስቲያን እንደሆኑ መናገራቸው

ማቴዎስ 24:5, 11፤ ማርቆስ 13:6

• ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት መነሳታቸው

ማቴዎስ 24:9፤ ሉቃስ 21:12

• እውነተኛ ክርስቲያኖች መሰደዳቸው

ማቴዎስ 24:39

• ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ማስጠንቀቂያዎች ችላ ማለታቸው

[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በምድር ዙሪያ የይሖዋ ምሥክሮች ለሰዎች ስለ አምላክ መንግሥት ያስተምራሉ