በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተጠቅመሃል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

• አምላክ ሀብታም የሚያደርግህ በምን ረገድ ነው?

በጥንት ጊዜ ይሖዋ እንደ አብርሃምና ሰለሞን ያሉ አንዳንድ አገልጋዮቹን ቁሳዊ ሀብት በመስጠት ባርኳቸው ነበር። ይሁንና ክርስቲያኖች ከሁሉም በላይ የሚያስፈልጋቸው በእምነት፣ በሰላም፣ በደስታና በመሳሰሉት ነገሮች ረገድ ሀብታም መሆን ነው፤ አምላክም የሚረዳቸው እነዚህን ነገሮች እንዲያገኙ ነው።—9/1 ከገጽ 3-7

• ጴጥሮስ ባሕሩ ውስጥ ሊሰጥም ሲል ኢየሱስ እሱን ለማዳን ከወሰደው እርምጃ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ማቴ. 14:28-31)

አንድ ወንድማችን እምነት እንደጎደለው የሚጠቁም እርምጃ ሲወስድ ብንመለከት በምሳሌያዊ መንገድ እጃችንን ልንዘረጋለትና እምነቱን እንዲያጠናክር ልንረዳው እንችላለን።—9/15 ገጽ 8

• ይሖዋ እኛን ለማዳን ምን ዋጋ ከፍሏል?

ይሖዋ ልጁ ሲሠቃይና የሰዎች መዘባበቻ ሲሆን መመልከት ግድ ሆኖበታል። እንዲሁም ልጁን መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ፈቃደኛ ከሆነው ከአብርሃም ሁኔታ መመልከት እንደሚቻለው ይሖዋ ልጁ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ሲገደል ማየት የሚያስከትልበትን የስሜት ሥቃይ መቋቋም አስፈልጎታል።—9/15 ከገጽ 28-29

• ቫቲካን ኮዴክስ እንደ ውድ ሀብት የሚታየው ለምንድን ነው?

ይህ የግሪክኛ ጽሑፍ የተጻፈው ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ከተጠናቀቀ 300 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው። የዕብራይስጥና የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍትን በሙሉ ይዟል ለማለት ይቻላል። ይህን ጽሑፍ ምሑራን የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳን መጻሕፍት ምን ይዘት እንደነበራቸው ለማወቅ ከሚጠቀሙባቸው ጽሑፎች መካከል አንዱ ነው።—10/1 ከገጽ 18-20

ምሳሌ 24:27 ‘ቤትን ስለመሥራት’ ምን ትምህርት ያስገኝልናል?

ማግባት የሚፈልግ ሰው ትዳር የሚያስከትለውን ኃላፊነት ለመሸከም ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። ይህ ደግሞ ለቤተሰቡ ቁሳዊ ነገሮችን ለማቅረብና የቤተሰቡ መንፈሳዊ ራስ ለመሆን መዘጋጀትን ይጨምራል።—10/15 ገጽ 12

• የይሖዋ ምሥክሮች የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች እንደሆኑ አድርጎ መናገር ተገቢ ያልሆነው ለምንድን ነው?

የፕሮቴስታንት ሃይማኖት የጀመረው በ16ኛው መቶ ዘመን አውሮፓ ውስጥ በሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ ተሃድሶ ለማካሄድ በተደረገው ጥረት ነው። “ፕሮቴስታንት” የሚለው መጠሪያ የተሃድሶውን መርሆና ዓላማ በጥብቅ የሚደግፉ ሰዎችን ለማመልከት ይሠራበታል። የይሖዋ ምሥክሮች ጳጳሱ ያላቸውን ዓለም አቀፋዊ የበላይነት አይቀበሉም፤ እንዲሁም የእውነት ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው በሚለው ሐሳብ ሙሉ በሙሉ ይስማማሉ፤ ሆኖም በፕሮቴስታንት ሃይማኖቶች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን በርካታ ቅዱስ ጽሑፋዊ ያልሆኑ ትምህርቶችንና ልማዶችን አይቀበሉም።—11/1 ገጽ 19

• አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ዕብራይስጥንና ግሪክኛን መማር አለበት?

አይኖርበትም። እነዚህን ቋንቋዎችን ማወቅ በራሱ አንድን ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት የመረዳት ችሎታ እንዲኖረው አያደርገውም። እነዚህን ቋንቋዎች የተማረ ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን ሐሳብ ለመረዳት መዝገበ ቃላቶችንና የሰዋስው መጻሕፍትን መመልከት ያስፈልገዋል። ከሁሉ የሚበልጠው የአምላክ አገልጋይ የተናገረው ሐሳብ በጽሑፍ የተላለፈው እሱ በተጠቀመበት ቋንቋ ሳይሆን በወቅቱ አብዛኛው ሕዝብ በሚገባው ቋንቋ ተተርጉሞ ነው፤ አምላክ የአገልጋዩን ሐሳብ ሰዎች በመንፈስ ተመርተው በዚህ መልክ እንዲተረጉሙት ማድረጉ አንድ ሰው በራሱ ቋንቋ በተዘጋጁ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች እውነትን መረዳት እንደሚችል ያሳያል።—11/1 ከገጽ 20-23

• ይሖዋና ኢየሱስ በመልካም ምግባር ረገድ ምሳሌ የተዉልን እንዴት ነው?

ይሖዋ የመጨረሻው ከፍተኛ ባለሥልጣን ቢሆንም ሰዎችን በደግነትና በአክብሮት ይይዛቸዋል። ይሖዋ አብርሃምንም ሆነ ሙሴን ሲያነጋግራቸው በአንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሶች ውስጥ “እባክህ” ተብሎ የተተረጎመውን የዕብራይስጥ ቃል ተጠቅሟል። (ዘፍ. 13:14፤ ዘፀ. 4:6) በተጨማሪም አምላክ ሰዎችን ያዳምጣል። (ዘፍ. 18:23-32) ኢየሱስም ተመሳሳይ ነገር አድርጓል፤ እርዳታ የሚሹ ሰዎችን ለመርዳት ምንጊዜም ዝግጁና ፈቃደኛ ነበር፤ ብዙውን ጊዜም በስማቸው ይጠራቸው ነበር።—11/15 ገጽ 25

• እውነተኛ ክርስቲያኖች የጨረቃ አዲስ ዓመትን የማያከብሩት ለምንድን ነው?

የጨረቃ አዲስ ዓመት በእስያውያን የቀን አቆጣጠር ትልቅ ግምት የሚሰጠው በዓል ነው። ይህ በዓል በአብዛኛው የሚከበረው መልካም ዕድልን በመመኘትና ለሙታን መናፍስት አክብሮት በማሳየት ነው። ክርስቲያኖች ወላጆቻቸውን የሚያከብሩ ቢሆንም የሞቱ ዘመዶችን ጥበቃ ለማግኘት ወይም የቤተሰብ አማልክትን ለመለማመን ታስበው በሚዘጋጁ ግብዣዎች ላይ አይካፈሉም።—12/1 ከገጽ 20-23