በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታማኝ የሆኑ ጓደኞች ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ታማኝ የሆኑ ጓደኞች ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ለታዳጊ ወጣቶች

ታማኝ የሆኑ ጓደኞች ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ዮናታን፣ ዳዊት እና ሳኦል

ታሪኩ በአጭሩ፦ ዳዊት ጎልያድን ከገደለ በኋላ ዮናታንና ዳዊት በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ሆኑ።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—1 ሳሙኤል 17:57 እስከ 18:11⁠ን፤ 19:1⁠ን፤ 20:1-17, 41, 42ን አንብብ።

ሳኦልን በአእምሮህ ስትስለው ምን ዓይነት ቁመና ያለው ሰው ይመስልሃል? (ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 10:20-23⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

ዳዊት ከዮናታን ጋር ሲገናኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሳይሆን አይቀርም። ታዲያ ዳዊትን በአእምሮህ ስትስለው ምን ዓይነት ቁመና ያለው ልጅ ይመስልሃል? (ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 16:12, 13⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

በአንደኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 20 ወደ መጨረሻው አካባቢ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ዳዊትና ዮናታን ሲሰነባበቱ ስሜታቸውን እንዴት የገለጹ ይመስልሃል?

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ታሪኩ “የዮናታን ነፍስ ከዳዊት ነፍስ ጋር ተቈራኘች” ይላል። ኮንቴምፖራሪ ኢንግሊሽ ቨርዥን ይህን ጥቅስ “ዳዊትና ዮናታን በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ሆኑ” በማለት አስቀምጦታል። (1 ሳሙኤል 18:1) ዮናታን ዳዊትን የወደደው ዳዊት ምን ዓይነት ባሕርያት ስላሉት ሊሆን ይችላል? (ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 17:45, 46⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

ዳዊትና ዮናታን በመካከላቸው በግምት የ30 ዓመት ልዩነት አላቸው። በመካከላቸው የዕድሜ ልዩነት ቢኖርም “በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች” እንዲሆኑ የረዳቸው ምን ይመስልሃል?

․․․․․

በጣም ደስ ከሚለው ከዚህ ታሪክ መረዳት እንደሚቻለው እውነተኛ ጓደኛሞች ሊኖሯቸው የሚገቡት አንዳንድ ባሕርያት የትኞቹ ናቸው? (ፍንጭ፦ ምሳሌ 17:17⁠ን እና 18:24⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

ዮናታን ከገዛ አባቱ ይልቅ ለዳዊት ታማኝ የሆነው ለምንድን ነው?

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ጓደኝነት።

․․․․․

ታማኝነት።

․․․․․

በዕድሜ ከሚበልጡን ሰዎች ጋር ጓደኝነት መመሥረት።

․․․․․

በጣም ጥሩ ጓደኛ ለማግኘት ምን ማድረግ ትችላለህ?

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምን እንዲህ አልክ?

․․․․․

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።