በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትንቢት 2. ረሃብ

ትንቢት 2. ረሃብ

ትንቢት 2. ረሃብ

“የምግብ እጥረት ይከሰታል።”​—ማርቆስ 13:8

● አንድ ሰው ሕይወቱን ለማቆየት ሲል በኒጀር ወደምትገኘው ወደ ኩዋራተጂ መንደር ተሰደደ። የቅርብ ዘመዶቹን ጨምሮ ወንድሞቹና እህቶቹ ከረሃብ ለመሸሽ ሲሉ ርቆ ከሚገኝ የአገሪቱ ክፍል ወደዚህ መንደር መጥተዋል። ሆኖም ይህ ሰው መሬት ላይ አንጥፎ ብቻውን ተኝቷል። ለመሆኑ ከዘመዶቹ ተነጥሎ ብቻውን የሆነው ለምንድን ነው? “[ቤተሰቡን] መመገብ ስላልቻለ ዓይናቸውን ማየት ከብዶት ነው” በማለት ሲዲ የተባሉት የመንደሩ አለቃ ገልጸዋል።

እውነታው ምን ያሳያል? በመላው ዓለም ከ7 ሰዎች መካከል 1ዱ ለማለት ይቻላል በየቀኑ የሚበላው በቂ ምግብ አያገኝም። ከሰሃራ በታች ባለው የአፍሪካ ክፍል ደግሞ ሁኔታው የከፋ ነው፤ በእነዚህ አገራት ከ3 ሰዎች መካከል 1ዱ ለረዥም ጊዜ በረሃብ እየተሠቃየ እንደሚኖር ይታሰባል። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት አባት፣ እናትና አንድ ልጅ ያሉበትን ቤተሰብ በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። ያላቸው ምግብ ለሁለት ሰው ብቻ የሚበቃ ከሆነ ወላጆቹ በቅድሚያ ልጃቸው በልቶ እንዲያድር ያደርጉ ይሆናል፤ ጥያቄው ግን ከሁለቱ ጦሙን የሚያድረው ማን ነው የሚለው ነው። አባትየው ወይስ እናትየው? እንዲህ ያሉ ቤተሰቦች በየዕለቱ ይህን የመሰለ ምርጫ ለማድረግ ይገደዳሉ።

በተደጋጋሚ የሚሰነዘረው የተቃውሞ ሐሳብ ምንድን ነው? ምድር ለሁሉም ሰው የሚሆን ከበቂ በላይ የሆነ ምግብ ታመርታለች። የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር የምድርን ሀብት በአግባቡ መጠቀም ብቻ ነው።

ይህ የተቃውሞ ሐሳብ ትክክል ነው? በእርግጥ ገበሬዎች በታሪክ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ብዙ ምግብ ማምረትና ምርታቸውን ወደ ተለያዩ ቦታዎች ማጓጓዝ ችለዋል። በመሠረቱ ሰብዓዊ መንግሥታት ረሃብን ለማስቀረት የምድርን የምግብ አቅርቦት በተሳካ መንገድ ማስተዳደር መቻል ነበረባቸው። ሆኖም ለብዙ አሥርተ ዓመታት ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

ምን ይመስልሃል? ማርቆስ 13:8 በመፈጸም ላይ እንደሆነ ይሰማሃል? ቴክኖሎጂ ከፍተኛ እመርታ ቢያሳይም የምግብ እጥረት አሁንም የሰው ልጆችን እያሠቃየ ያለ ዓለም አቀፋዊ ችግር እንደሆነ ይሰማሃል?

ብዙ ጊዜ የምድር ነውጥንና ረሃብን ተከትሎ የሚመጣ አንድ ችግር ያለ ሲሆን ይህም የመጨረሻዎቹ ቀኖች ምልክት ሌላ ገጽታ ነው።

[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

“በሳንባ ምች፣ በተቅማጥና በሌሎች በሽታዎች ከሚሞቱት ሕፃናት መካከል ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆኑት በቂ ምግብ ቢያገኙ ኖሮ ሕይወታቸው ሊተርፍ ይችል ነበር።”​—አን ቬነመን፣ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት የቀድሞ ዳይሬክተር

[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

© Paul Lowe/Panos Pictures