በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

3 አምላክ ተበቃይ ነው​—ይህ እውነት ነው?

3 አምላክ ተበቃይ ነው​—ይህ እውነት ነው?

3 አምላክ ተበቃይ ነው​—ይህ እውነት ነው?

እንዲህ ሲባል ሰምተህ ይሆናል፦ “አምላክ ሰዎች የፈጸሙትን እያንዳንዱን ኃጢአት ተከታትሎ በገሃነመ እሳት ለዘላለም ይቀጣቸዋል።”

“አምላክ ኃጢአተኞችን በተፈጥሮ አደጋ ይቀጣቸዋል።”

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል? ሁለተኛ ጴጥሮስ 3:9 ይሖዋ “ሁሉ ለንስሐ እንዲበቃ እንጂ ማንም እንዲጠፋ [እንደማይፈልግ]” ይናገራል። አምላክ በምንፈጽማቸው ስህተቶች ላይ ከማተኮር ይልቅ በጠንካራ ጎኖቻችን ላይ ያተኩራል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “በፍጹም ልባቸው የሚታመኑበትን ለማበርታት የእግዚአብሔር ዐይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይመለከታሉ።”​—2 ዜና መዋዕል 16:9

መጽሐፍ ቅዱስ ገሃነመ እሳት እንዳለ አያስተምርም፤ ደግሞም ዘላለማዊ ሥቃይ የሚለው ሐሳብ በአምላክ ዘንድ እጅግ የተጠላ ነው። አምላክ ክፉዎችን የሚቀጣበት የመጨረሻው ትልቁ ቅጣት ሞት ነው። (ኤርምያስ 7:31፤ ሮም 6:7) በሌላ በኩል ደግሞ በሰዎች ላይ በጅምላ ጥፋት የሚያስከትል የተፈጥሮ አደጋ፣ አምላክ የሚያመጣው ቅጣት ሳይሆን በማንም ሰው ላይ ሊደርስ የሚችል ያልተጠበቀ ክስተት ነው።​—መክብብ 9:11 NW

እውነቱን ማወቅህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው? አምላክ “ይቅር ባይ” እንደሆነ እንዲሁም በሰው ላይ ለመፍረድ እንደማይቸኩል ማወቃችን ይበልጥ ወደ እሱ ለመቅረብ ያነሳሳናል። (መዝሙር 86:5) የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶን ወይም ቅጣት እንዳይደርስብን በሚል ፍራቻ አምላክን ማገልገል የለብንም። ከዚህ ይልቅ ከሁሉ የተሻለ ዓላማ በመያዝ ይኸውም ለይሖዋ ባለን ፍቅር ላይ እምነታችንን መገንባት እንችላለን። እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር እሱን ለማስደሰት አቅማችን የሚፈቅደውን ሁሉ እንድናደርግ የሚያነሳሳ ኃይል ይሆንልናል።​—ማቴዎስ 22:36-38፤ 1 ዮሐንስ 5:3

አምላክ ሁሉም ሰው ጥሩ ነገር እንዲያደርግ የሚፈልግ ቢሆንም ብዙዎች እንዲህ እንደማያደርጉ ያውቃል። ክፉ ነገሮች በማድረግ ለመቀጠል በወሰኑ ሰዎች ላይ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ሕግ ቢያወጣም ሕጉን ማስከበር ከማይችል ገዥ የማይለይ ያደርገዋል፤ እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ደግሞ ኢፍትሐዊነትና መከራ እስከ ወዲያኛው እንዲንሰራፉ ያደርጋል። (መክብብ 8:11) አምላክ ክፋትን ለዘላለም እንደማይታገሥ ማወቃችን የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ ጠንካራ ተስፋ ይሰጠናል። አምላክ መጀመሪያ በነበረው ዓላማ መሠረት “ገሮች” በምድር ላይ ለዘላለም መኖር እንዲችሉ በክፉ ድርጊታቸው ለመቀጠል የወሰኑትን ሰዎች እንደሚያጠፋ ቃል ገብቷል።​—መዝሙር 37:10, 11, 29 *

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.7 አምላክ ምድርን ወደ ገነትነት የሚለውጣት እንዴት እንደሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 3 እና 8 ተመልከት።

[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

አምላክ ቅጣት ፈርተን እንድናመልከው ይፈልጋል?

[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Engravings by Doré