በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“አክብሮት ሊቸረው የሚገባ የተቃውሞ ድምፅ”

“አክብሮት ሊቸረው የሚገባ የተቃውሞ ድምፅ”

“አክብሮት ሊቸረው የሚገባ የተቃውሞ ድምፅ”

የጀርመን መራሄ መንግሥት የነበረው አዶልፍ ሂትለር ብዙ ጥፋት ባስከተለው የግዛት ዘመኑ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ደብዳቤዎች ደርሰውት ነበር። በ1945 ሩሲያውያን በበርሊን ዙሪያ ያለውን አካባቢ ከተቆጣጠሩ በኋላ ከእነዚህ ደብዳቤዎች ውስጥ አብዛኞቹ ወደ ሞስኮ ተወስደው በዚያ ተቀመጡ። ታሪክ ጸሐፊው ሄንሪክ ኤበሌ ለሂትለር ደብዳቤ የጻፉት እነማን እንደሆኑና የጻፉበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ በሞስኮ ቤተ መዛግብት ውስጥ ከተቀመጡት ከእነዚያ ደብዳቤዎች መካከል በሺዎች በሚቆጠሩት ላይ ጥናት አካሂደው ነበር። ሄንሪክ የደረሱባቸውን ድምዳሜዎች ብሪፈ አን ሂትለር (ለሂትለር የተጻፉ ደብዳቤዎች) የሚል ርዕስ ባለው መጽሐፍ አሳትመውታል።

ዶክተር ሄንሪክ እንዲህ ብለዋል፦ “አስተማሪዎችና ተማሪዎች፣ መነኮሳትና ቀሳውስት፣ ሥራ አጥ የሆኑ ሰዎችና ታላላቅ ነጋዴዎች፣ የባሕር ኃይል ከፍተኛ አዛዦችና ተራ የናዚ ወታደሮች ለሂትለር ደብዳቤ ጽፈዋል። . . . አንዳንዶቹ ዳግም የተወለደው መሲሕ ነው ብለው ሲያሞካሹት ሌሎቹ ግን ዓይነተኛ የክፋት መገለጫ እንደሆነ አድርገው ገልጸውታል።” ለመሆኑ ብሔራዊ ሶሻሊስቶች ወይም ናዚዎች ይፈጽሟቸው የነበሩትን ዘግናኝ ድርጊቶች በተመለከተ ከቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣናት የተቃውሞ ደብዳቤዎች ለሂትለር ደርሰውት ነበር? የተወሰኑ ደብዳቤዎች ደርሰውታል፤ ይሁንና ያን ያህል ከቁጥር የሚገቡ አልነበሩም።

ይሁን እንጂ ሄንሪክ በሞስኮ በነበሩት ቤተ መዛግብት ውስጥ በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች የናዚዎችን ተግባር በመቃወም ለሂትለር የላኳቸውን በርካታ ደብዳቤዎች የያዘ አንድ ፋይል አግኝተዋል። እንዲያውም 50 ከሚያህሉ አገሮች የተውጣጡ የይሖዋ ምሥክሮች፣ የእምነት ባልንጀሮቻቸው የሚደርስባቸውን እንግልት አስመልክተው ተቃውሟቸውን ያሰሙባቸውን 20,000 የሚሆኑ ደብዳቤዎችና የቴሌግራም መልእክቶች ለሂትለር ልከዋል። በወቅቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የይሖዋ ምሥክሮች በናዚዎች ታስረዋል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተገድለዋል አሊያም በደረሰባቸው እንግልት የተነሳ ሕይወታቸው አልፏል። ዶክተር ሄንሪክ በመደምደሚያቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦ “በናዚ አገዛዝ ሕይወታቸውን ካጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አንጻር [ለሞት የተዳረጉት የይሖዋ ምሥክሮች] ቁጥር ትንሽ ሊመስል ይችላል። ያም ቢሆን እነዚህ ሰዎች በአንድነት ሆነው በአቋማቸው በመጽናት አክብሮት ሊቸረው የሚገባ የተቃውሞ ድምፅ እንዳሰሙ ምሥክር ይሆናል።”