በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከእቶን እሳት ዳኑ!

ከእቶን እሳት ዳኑ!

ለታዳጊ ወጣቶች

ከእቶን እሳት ዳኑ!

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ አብደናጎና ናቡከደነፆር

ታሪኩ በአጭሩ፦ የሦስት ወጣት ዕብራውያን እምነት ተፈተነ።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።​ዳንኤል 3:1-30ን አንብብ።

ከቁጥር 3 እስከ 7 ያለውን ስታነብ “የምትሰማውን” ድምፅ ግለጽ።

․․․․․

የእሳቱ እቶን ምን ሊመስል እንደሚችል ግለጽ።

․․․․․

ናቡከደነፆር የእቶኑ እሳት ቀደም ሲል ከነበረው ሰባት እጥፍ ተደርጎ እንዲነድ ሲያዝዝ ምን ዓይነት የድምፅ ቃና የነበረው ይመስልሃል? (ቁጥር 19 እና 20⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

በእሳቱ እቶን ውስጥ የነበረው አራተኛ ሰው ምን ዓይነት መልክና ቁመና ያለው ይመስልሃል? (ቁጥር 24 እና 25⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ከቁጥር 16 እስከ 18⁠ን ስታነብ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ናቡከደነፆርን ሲያነጋግሩ ምን ዓይነት ባሕርይ እንደነበራቸው አስተውለሃል?

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ምርምር ማድረግ የምትችልባቸውን መሣሪያዎች በመጠቀም አንድ ክንድ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ሞክር፤ ከዚያም ናቡከደነፆር ያሠራው ምስል ከፍታውና ወርዱ ምን ያህል እንደነበረ አስላ። (ቁጥር 1⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ቁጥር 19 እና 20⁠ን ከቁጥር 28 እና 29 ጋር ስታወዳድር ናቡከደነፆር ምን ዓይነት ሰው የነበረ ይመስልሃል?

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

በሥልጣን ላይ ላሉ ሰዎች አክብሮት ስለማሳየት

․․․․․

ለምታምንበት ነገር አቋም መውሰድ አስፈላጊ ስለመሆኑ

․․․․․

በመከራ ወቅት ይሖዋ ስለሚሰጠው ድጋፍ

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር፦

የአንተ እምነት ሊፈተን የሚችልባቸው ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው?

․․․․․

የሲድራቅ፣ የሚሳቅና የአብደናጎ ታሪክ ታማኝነትህን እንድትጠብቅ የሚረዳህ እንዴት ነው?

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።