በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስ ፍለጋ

መልስ ፍለጋ

መልስ ፍለጋ

“ሁሉም ሰው ለማለት ይቻላል [ስለ ኢየሱስ] ማንነት የራሱ የሆነ ጽንሰ ሐሳብ አለው። በእሱ ላይ ያለን እምነትም ሆነ ጥርጣሬ ምንም ያህል ቢሆን ‘ይህ ሰው ማን ነው?’ ብለን መጠየቃችን አይቀርም።”​—ደራሲ ስታን ገትሪ

ሰዎች ስለ ኢየሱስ የማወቅ ጉጉት አላቸው። ስለ እሱ የተጻፉ መጻሕፍት በብዛት ተሽጠዋል። በእሱ ሕይወት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ፊልሞችም በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት አትርፈዋል። ያም ሆኖ ብዙ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ አላገኙም። እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ትክክለኛ ማንነት የሚሰጧቸው አስተያየቶች የተለያዩ ናቸው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ሁለት ጋዜጠኞች “ኢየሱስ ማን ነበር?” ለሚለው ጥያቄ ሰዎች በኢንተርኔት መልስ እንዲሰጡ ጋብዘው ነበር። ለጥያቄው ከተሰጡት መልሶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

● “ከሁኔታው ማየት እንደሚቻለው ሕይወቱን የርኅራኄ ተምሳሌት አድርጎ ያቀረበ አንድ የአይሁድ ረቢ (መምህር) ነበር።”

● “አስደናቂ ሕይወት የመራ ተራ ሰው ነበር።”

● “ኢየሱስ በሕይወት የኖረ ሰው ለመሆኑ ማስረጃ የለም።”

● “ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው፤ የተወለደው፣ የሞተውና ከሙታን የተነሳው እኛን ከኃጢአታችን ለማዳን ነው። በአሁኑ ጊዜ በሕይወት ያለ ሲሆን ወደፊትም ዳግመኛ ወደ ምድር ይመጣል።”

● “ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው የአምላክ ልጅ እንዲሁም ፍጹም ሰው፣ ፍጹም አምላክ እንደሆነ አምናለሁ።”

● “ስለ ኢየሱስ የሚገልጹት ታሪኮች በልጆች መጻሕፍት ላይ እንደሚገኙት ተረቶች ናቸው።”

እንደነዚህ ያሉት ሰፊ ልዩነት ያላቸው አመለካከቶች በሙሉ ትክክል ሊሆኑ እንደማይችሉ ግልጽ ነው። ታዲያ ስለ ኢየሱስ ለምናነሳቸው ጥያቄዎች የሚታመን መልስ መስጠት የሚችል አንድ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ ይኖራል? የዚህ መጽሔት አዘጋጆች፣ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል እንደሆነና ስለ ኢየሱስ ትክክለኛና የተሟላ መረጃ ሊሰጠን የሚችለው ይህ መጽሐፍ ብቻ መሆኑን ያምናሉ። *​—2 ጢሞቴዎስ 3:16

ስለ ኢየሱስ ከሚነሱት የተለመዱ ጥያቄዎች መካከል ለአንዳንዶቹ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ በቀጣዩ ርዕስ ላይ እንመለከታለን። ኢየሱስ ራሱ “[በእሱ] እንደሚያምን በተግባር የሚያሳይ ሁሉ” መዳን ማግኘት እንደሚችል ተናግሯል። (ዮሐንስ 3:16) አንተም ለጥያቄዎቹ የተሰጡትን መልሶች እንድትመረምር እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ይበልጥ ማወቅ ያስፈልግህ እንደሆነ ራስህ እንድትወስን እንጋብዝሃለን፤ በተጨማሪም በእሱ ላይ ያለህን እምነት እንዴት በተግባር እንደምታሳይ መማር ትችላለህ።

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.11 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች በተዘጋጀው ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? በተባለው መጽሐፍ ላይ “መጽሐፍ ቅዱስ​—አምላክ ለሰው ልጆች የሰጠው መጽሐፍ” የሚለውን ምዕራፍ 2⁠ን ተመልከት።