በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ፍቅር መገለጫ የሆኑት ቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች

የይሖዋ ፍቅር መገለጫ የሆኑት ቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች

ይሖዋ ታላቅ “አስተማሪ” ነው። (ኢሳ. 30:20) ፍቅር ሌሎችን እንዲያስተምርና እንዲያሠለጥን ያነሳሳዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ይሖዋ ኢየሱስን በጥልቅ ስለሚወደው “የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ያሳየዋል።” (ዮሐ. 5:20) ለእኛ ለምሥክሮቹ ያለው ፍቅር ደግሞ እሱን ለማክበርና ሌሎችን ለመርዳት የሚያስችለንን ‘የተማረ ምላስ’ እንዲሰጠን አነሳስቶታል።​—ኢሳ. 50:4 የ1954 ትርጉም

የበላይ አካሉ የትምህርት ኮሚቴ የይሖዋን የፍቅር መንገድ በመከተል፣ የመማር ፍላጎት ያላቸውንና ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸውን ሰዎች ለማሠልጠን አሥር ቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶችን ይጠቀማል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች የይሖዋ ፍቅር መገለጫ እንደሆኑ ይሰማሃል?

በዘመናችን ስላሉት ቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች የተሰጠውን ማብራሪያና በዚያ የተካፈሉ ወንድሞችና እህቶች የሰጡትን አስተያየት እንድትመለከት እንጋብዝሃለን። ከዚያም ‘ከመለኮታዊ ትምህርት ጥቅም ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?’ እያልክ ራስህን ጠይቅ።

ከቲኦክራሲያዊ ሥልጠና ጥቅም ማግኘት

ይሖዋ ‘የፍቅር አምላክ’ እንደመሆኑ መጠን ሕይወታችን ይበልጥ ትርጉም ያለው እንዲሆን የሚረዳንን፣ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን እንድንወጣ የሚያዘጋጀንን እንዲሁም ከአገልግሎታችን እርካታ ለማግኘት የሚያስችለንን ሥልጠና ይሰጠናል። (2 ቆሮ. 13:11) በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበሩት ደቀ መዛሙርት፣ እኛም ኢየሱስ ‘ያዘዘውን ሁሉ እንዲጠብቁ’ ሌሎችን ለመርዳት ብቃቱ አለን።​—ማቴ. 28:20

በሁሉም ትምህርት ቤቶች መካፈል ባንችልም ከተወሰኑት ግን ጥቅም ማግኘት እንችላለን። በተጨማሪም የምናገኘውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጠና በሥራ ላይ ማዋል እንችላለን። እንዲሁም ከይሖዋ ድርጅት ሥልጠና ካገኙ ክርስቲያኖች ጋር አብረን በመሥራት በአገልግሎታችን ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንችላለን።

እንግዲያው ‘ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች በአንዱ ለመሠልጠን ሁኔታዬ ይፈቅድልኛል?’ በማለት ራስህን ጠይቅ።

የይሖዋ አገልጋዮች እነዚህን ትምህርት ቤቶች መደገፋቸውን እንዲሁም በትምህርት ቤቶቹ ገብተው መማራቸውን እንደ መብት ይቆጥሩታል። የምታገኘው ሥልጠና ወደ ይሖዋ ይበልጥ ለመቅረብ እንዲረዳህና እሱ የሰጠህን ኃላፊነት በተለይም ደግሞ አጣዳፊ የሆነውን ምሥራቹን የመስበኩን ሥራ በጥሩ ሁኔታ ለመወጣት እንዲረዳህ ምኞታችን ነው።