በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የአምላክ ስም ማን ነው?

የቤተሰባችን አባላት በሙሉ የየራሳቸው ስም አላቸው። የቤት እንስሶች እንኳ ስም ይወጣላቸዋል! ታዲያ አምላክስ ስም ያለው መሆኑ ምክንያታዊ አይደለም? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አምላክ በርካታ የማዕረግ ስሞች እንዳሉት ተጠቅሷል፤ ከእነዚህም መካከል ኤልሻዳይ፣ ሉዓላዊ ጌታ፣ ፈጣሪ እና ሌሎችም ይገኙበታል። ይሁንና አምላክ የራሱ መጠሪያ ስም አለው።ዘፀአት 6:3ን አንብብ።

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በመዝሙር 83:18 ላይ የአምላክን የግል ስም አስፍረዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም (እንግሊዝኛ) ላይ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ “ይህም ሰዎች፣ ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣ በመላው ምድር ላይ አንተ ብቻ ከሁሉ በላይ እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ነው።”

በአምላክ ስም መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው?

አምላክ በግል ስሙ እንድንጠቀም ይፈልጋል። የቅርብ ጓደኞቻችንን ጨምሮ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ስናወራ የምናነጋግራቸው ስማቸውን እየጠራን ነው። ከአምላክ ጋር ስንነጋገርስ እንዲህ ማድረግ አይኖርብንም? ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክ ስም እንድንጠቀም አበረታትቶናል።ማቴዎስ 6:9ን እና ዮሐንስ 17:26ን አንብብ።

ይሁን እንጂ የአምላክ ወዳጅ ለመሆን ስሙን ማወቅ ብቻውን በቂ አይደለም። ለምሳሌ ያህል፣ ስለ አምላክ ማንነት እንዲሁም ወደ እሱ መቅረብ ይቻል እንደሆነ ማወቅ ይኖርብናል። ስለ እነዚህ ጉዳዮች ከመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ማግኘት ትችላለህ።