በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ፦ ሕይወትህ ትርጉም ያለው ሊሆን ይችላል?

ትርጉም ያለው ሕይወት መኖር ይቻላል?

ትርጉም ያለው ሕይወት መኖር ይቻላል?

“ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እርሱም በመከራና በሐዘን የተሞላ ነው።”መዝሙር 90:10 የ1980 ትርጉም

ይህ ጥቅስ እውነታውን ቁልጭ አድርጎ ይገልጻል! በዚህ ዓለም ላይ ሕይወታችን አብዛኛውን ጊዜ “በመከራና በሐዘን” የተሞላ ነው። ምናልባት አንተም ‘በአሁኑ ጊዜ እውነተኛ ትርጉም ያለው ሕይወት መኖር ይቻላል?’ ብለህ ጠይቀህ ታውቅ ይሆናል።

የማርያን ሁኔታ እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ማርያ ደከመኝ የማያውቁ ጠንካራ ሴት የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን በ84 ዓመታቸው ከቤት መውጣት አቅቷቸዋል። አእምሯቸው በደንብ የሚሠራ ቢሆንም ሰውነታቸው ግን እንደልብ አይታዘዝላቸውም። ታዲያ እኚህ አረጋዊት እንዲህ ያለ ሕይወት ትርጉም እንዳለው እንዴት ሊሰማቸው ይችላል?

አንተስ ምን ትላለህ? ሕይወትህ ትርጉም ያለው ስለመሆኑ የጠየቅክበት ጊዜ ሳይኖር አይቀርም። የምትሠራው ሥራ ድግግሞሽ እንደሆነ ሊሰማህ እንዲሁም አድካሚና አሰልቺ ሊሆንብህ ይችላል። ጥረትህና ልፋትህ እውቅና ሳያገኝ ቀርቶ ይሆናል። በተወሰነ መጠን ስኬታማ ብትሆንም እንኳ የወደፊቱን ጊዜ ስታስብ ስጋት ያድርብህ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜም የብቸኝነት ወይም የጭንቀት ስሜት ሊሰማህ አሊያም ደግሞ የቤተሰብ ሕይወትህ ግጭትና ጭቅጭቅ የበዛበት ሊሆን ይችላል። ወይም የምትወደውን ሰው በሞት አጥተህ ይሆናል። ለምሳሌ፣ አንድሬ ከአባቱ ጋር በጣም ይቀራረብ ነበር፤ ይሁንና አባቱ በድንገት ታሞ ሞተ። በዚህ ጊዜ የተሰማው ሐዘን በጣም የጎዳው ከመሆኑም ሌላ ባዶነት ተሰማው። አንድሬ ያደረበትን ድንጋጤና ሐዘን መቋቋም እንደሚችል ሆኖ አልተሰማውም ነበር።

ያጋጠመን መከራ ምንም ይሁን ምን አንድ ልናውቀው የሚገባ ነገር ያለ ሲሆን ይህም ‘ትርጉም ያለው ሕይወት መኖር ይቻላል?’ ለሚለው ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ነው። ከዛሬ 2,000 ዓመታት ገደማ በፊት በዚህች ምድር ላይ የኖረ አንድ ሰው ይኸውም ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳለፈውን ሕይወት በመመርመር የዚህን ጥያቄ መልስ ማግኘት እንችላለን። ኢየሱስ የተለያዩ እንቅፋቶች ቢያጋጥሙትም እንኳ እውነተኛ ትርጉም ያለው ሕይወት ኖሯል። እኛም የእሱን ምሳሌ ከተከተልን ትርጉም ያለው ሕይወት መኖር እንችላለን።